Friday, 18 December 2015
Sunday, 13 December 2015
‹‹ኢየሱስ የሚወደው ደቀ መዝሙር›
‹‹ኢየሱስ የሚወደው ደቀ መዝሙር››
በዮሐንስ ወንጌል በብዙ ቦታ አንድ ደቀ መዝሙር ያለ ስም፣ ‹‹ኢየሱስ የሚወደው ደቀ መዝሙር›› የሚል ሐረግ እናገኛለን፤ (ንጽ. ዮሐ 1፡ 35-40፤ 13፡ 23-26፤ 18፡ 15-16፤ 19፡ 26-27፤ 20፡ 2-8፤ 21፡ 2፣7፣20-24)፡፡
- እርሱ እውነትን እየፈለገ ያለ ደቀ መዝሙር ነው፡፡ እርሱ አጥማቂው ዮሐንስን መከተል ጀምሮ ነበር፡፡ አጥማቂው ዮሐንስ ‹‹እነሆ የእግዚአብሔር በግ›› ሲል በሰማ ጊዜ ክርስቶስን ተከተለ፡፡ እርሱ ሄዶ አየና ከእርሱ ጋር ቆየ፡፡ (ንጽ. ዮሐ 1፡ 35-40)
- እርሱ በመጨረሻ እራት በኢየሱስ ጎን የተቀመጠና ራሱን ወደ ኢየሱስ ልብ አስጠግቶ የነበረ ደቀ መዝሙር ነው፡፡ እርሱ ኢየሱስን አሳልፎ የሰጠው የይሁዳ ተቃራኒ ነበር፡፡ እርሱ የኢየሱስ ልብ ያውቅ ነበር፡፡ በኢየሱስና በእርሱ መሐል ትልቅ ቅርበት፣ እምነት፣ ፍቅር፣ መረዳዳትና ስምምነት ነበራቸው፡፡ (ንጽ. ዮሐ 13፡ 23-26)፡፡
- እርሱ ኢየሱስን በሕማማቱ ጊዜ እንደ ጴጥሮስና እንደ ሌሎች ደቀ መዛሙርት ሳይክዳው በጀግንነት ይከተለው የነበረ ደቀ መዝሙር ነው (ንጽ. ዮሐ 18፡ 15-16)፡፡
- ለእርሱ ኢየሱስ ‹‹ይህችውልህ እናትህ›› አለ (ዮሐ 19፡ 27)
- እርሱ ማርያምን ወደ ቤቱ ወሰዳት፡፡ (ዮሐ 19፡ 27)
- እርሱ ስለ ኢየሱስ ሞት ምስክር ነበር፡፡ (ዮሐ 19፡ 30)
- እርሱ ፋጥኖ የሮጠና ቀድሞ ወደ መቃብሩ ደርሶ ጴጥሮስን የጠበቀ ደቀ መዝሙር ነው፡፡ ጴጥሮስ ወደ መቃብር ገብቶ ካየ በኋላ እርሱም ገብቶ አየና አመነ፡፡ (ዮሐ 20፡ 2-8)
- እርሱ ከሞት የተሳውን ኢየሱስን ያወቀ፣ ኢየሱስ እስኪመጣ የጠበቀና ስለ ክርስቶስ የመሰከረ ደቀ መዝሙር ነው (. ዮሐ 21፡ 2፣7፣20-24)
ኢየሱስ ይወደው የነበረው ደቀ መዝሙር የእወነተኛ ተምሳሌትና ኢየሱስን የተቀበለና በስሙ ያመነ አርአያ የሚሆን ደቀ መዝሙር ሲሆን (. ዮሐ 1፡ 12-13) ሁል ጊዜ ለኢየሱስ ታማኝ ሆኖ እስከ መጨረሻ የተከተለና ለእርሱ ምስክርነት የሰጠ ነው፣ ለዚህ ደቀ መዝሙር (ለእያንዳንዱ ክርስቲያን) ኢየሱስ እናቱን ሰጠ እና እውነተኛ ደቀ መዝሙር ስለሆነ እርሷን ወደ ቤቱና ወደ ልቡ ወሰደ፡፡ እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እዚህ ጋ የደቀ መዝሙር (የክርስቶስ አካል)፣ የቤተ ክርስቲያን እናት ትሆናለች፡፡
ዮሐንስ በወንጌሉ ‘lambanin’ (‹‹ላምባነይን›› መቀበል) የሚለውን የግሪክ ቃል ሦስት ጊዜ ይጠቀማል፡፡
እውነተኛ ደቀ መዝሙር፤
ኢየሱስን (ቃል ሥጋ የሆነውን) ይቀበላል (ዮሐ 1፡ 12)
እናታችን ማርያምን ይቀበላል (ዮሐ 19፡ 27)
እናም መንፈስ ቅዱስን ይቀበላል (ዮሐ 20፡ 22)፡፡
እውነተኛ ደቀ መዛሙር ኢየሱስን ይቀበላል፣ እስከ መስቀሉ ይከተለዋል፣ ስለ እርሱም ይመሰክራል፣ መንፈስ ቅዱስን ይቀበላል፣ እመቤታችን ቅድስተ ድንግል ማርያምንም እንደ እናት ይቀበላል፡፡
ኢየሱስ የሚወደውን ደቀ መዝሙር መምሰል እንድንችል እናታችን ድንግል ማርያም እንድትረዳን እንለምናት

Wednesday, 9 December 2015
እግዚአብሔር ለምን ዝም ይላል?
እግዚአብሔር ለምን ዝም ይላል?
+ 1.00 ሁሉን በጊዜው ሰለሚያከናውን።መክ3:1 ዕብ 2:3
+ 2.00 የሚበልጠውን ልሰጠን።ኤፌ3:20ኤር29:11ሕዝ 36:11
+ 3.00 በሕይወታችን ሊስተካከል የሚገባውን እያስተካከለ ስለሆነ።1ጴጥ 5:7ያዕ 1:19መዝ65:18 ዮሐ 9:31 አሳ 49:14
+ 4.00 ያላሰብነውን ልፈጽምልን። ኤር 33:3 ኤፌ 3:20
+ 5.00 ፈቃዱ አለመሆኑን ለመግለጽ። ማቴ 20:23 2ቆሮ 12:9
+ 6.00 በተሳሳተ መንገድ እና በእምነት ስለማንጸልይእንዲሁም ጸሎታችንን እስኪናስተካክለል።ሉቃ 18:11 ያዕ 4:1_3 ዮሐ 9:31 ማር 9:23;11:24 ማቴ5:15 ምሳ 3:5
+ 7.00 ሁሉ የእርሱ ድርሻ ስለሆነ። ኤር 29:11 ዕብ 6:17
+ 8.00 እኛ የተጠየቅነውን ተግባራዊ እስኪናደርግ።ዘዳ28:45 1ዮሐ 3:22 2ዜና 7:14
+ 9.00 ንጽሕና ስለሚጎለን። ዕብ 12:14 1ጴጥ 1:16 መዝ 65:18
+ 10.00 ንሰሃ ግቡ ሲለን።ራእ 2:5 ማቴ 3:2;3:8የሐዋ 2:39;17:03_31 ምሳ 28:13 2ተሰ 1:8_12
+ 11.00 ከእርሱ እና ከሌሎች ጋር እስኪንታረቅ። 2ቆሮ 5:20 ሮሜ 2:4_5;5:10_11;12:18 ኢዮ 22:21 ሉቃ 13:3 ቈላ1:21_22 1ጢሞ 2:8 ገላ 5:15
+ 12.00 አንታዘዝም ስንል።ኢሳ1:19 1ዮሐ3:22 ራእ 3:8
+ 13.00 የሚያመሰግን ልብ እንዲኖረን።1ተሰ 5:17_18 ዕብ 13:15 ሆሴ 14:2 ኤፌ 5:20
+ 14.00 የትዕግስት ጽናት ይገለጥ ዘንድ።2ጴጥ3:9 ዘፍ16:1_6 ኢያ1:1_11 መዝ 39:1 ሉቃ 18:1_7
ስለዚህ ሁላችንም እግዚአብሔር ለምን ዝም አለኝ? ብለን ራሳችንን ልንጠይቅ ያስፈልጋል።ለምጠቅም ወይም ለማይጠቅ መቸኮል ጥሩ አይደለም።መክ8:3"የወደደውን ሁሉ የደርጋልና ከፊቱ ትወገድ ዘንድ አትቸኩል ክፉንም በማድረግ አትጽና" ይለናል። ሁሌም በጸሎታችን እንደ ቅዱስ ዳዊት"ዝም አትበለኝ ወደ ጉድጓድ እንደምወርዳት እንዳልመስል አንተ አምላኬ ዝም አትበለኝ"መዝ27:1 እንበለ!
እግዚአብሔር ማስተዋሉን ያድለን!!!

ኅዳር 25 የቅዱስ መርቆሬዎስ በዓለ ዕረፍት
ኅዳር 25 የቅዱስ መርቆሬዎስ በዓለ ዕረፍት
ከመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ
የዚኽ ቅዱስ ሰማዕት ወላጆቹ ክርስቲያኖች ሲኾኑ ስሙን ፒሉፓዴር ብለውታል ትርጓሜውም “የአብ ወዳጅ” ማለት ሲኾን በመንፈሳዊ ትምህርት አጠንክረው አሳድገውታል፤ “ወተውህቦ ኀይል ዐቢይ ለቅዱስ መርቆሬዎስ ወተሰምዐ ዜናሁ በኲሉ ወተለዐለ እምሰብአ ቤተ መንግሥት” ይላል ታላቅ የድል አድራጊነት ኀይል ተሰጥቶት ዜናው በኹሉ ቦታ ሲሰማ ከቤተ መንግሥት ሰዎችን ይልቅ ከፍ ከፍ ብሏል፤ በዚኽ ምክንያት በጊዜው በነበረው ንጉሥ በዳኬዎስ ዘንድ ባለሟልነት አግኝቷል፡፡ ከዚያም በሮም ላይ የበርበር ሰዎች ተነሥተው የዳኬዎስን መንግሥት ሊወጉት መጡ፤ እጅግ ብዙዎችም ነበሩና ንጉሡ እጅግ ፈራ፤ ቅዱስ መርቆሬዎስ ግን “እግዚአብሔር ያጠፋቸው ዘንድ አለውና አትፍራ” አለው፡፡

“ወእምዝ ርእዮ ቅዱስ መርቆሬዎስ ለመልአከ እግዚአብሔር በውስተ ቀትል ወሰይፍ በሊኅ ውስተ እዴሁ” ይላል፤ የእግዚአብሔር መልአክ በውጊያው ውስጥ የተሳለ ሰይፍ በእጁ ይዞ ተገልጦለት ሰይፉን በመስጠት “ጠላቶችኽን ድል ባደረግኽ ጊዜ ፈጣሪኽ እግዚአብሔርን ዐስበው” ብሎ ሰጥቶታል፤ አንዱ ራሱ ለውጊያ የያዘው ሰይፍ ኹለተኛም ከመልአኩ የተቀበለው ሰይፍ ነበርና በዚኽ ምክንያት “አበ አስይፍት” (የሰይፎች አባት) ተብሏል፡፡
ከዚኽ በኋላ ንጉሡ ዳኬዎስ ለጣዖታት ዕጣን ሊያቀርብና በዓልን ሊያደርግ ወደዶ በዓልን ባደረገ ጊዜ ቅዱስ መርቆሬዎስ ግን ከርሱ ጋር አልወጣም፤ በዚኽ ምክንያት ንጉሡ አስጠርቶት “ለአማልክት ዕጣን ለማሳረግ ከእኔ ጋር ያልወጣኽ የእኔንስ ፍቅር ለምን ተውኽ” ብሎ ጠየቀው፤ በዚኽ ጊዜ ቅዱስ መርቆሬዎስ በንጉሡ ፊት ትጥቁንና ልብሱን ወርውሮ “እኔ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስን አልክደውም ለረከሱ ጣዖታትም አልሰግድም” በማለት መለሰለት፡፡
ንጉሡም እጅግ ተቈጥቶ ርጥብ በኾኑ የሽመል በትሮችና እንዲደበደብና ከላም ቆዳ በተሠራ ጅራፍ እንዲገረፍ አዘዘ፡፡ ቅዱስ መርቆሬዎስ ካለው ተወዳጅነት የተነሣ ሰዎች እንዳይነሡበት በመፍራት የቀጶዶቅያና የእስያ ክፍል ወደ ኾነች ወደ ቂሳርያ በብረት ማሠሪያ ታሥሮ እንዲላክ አድርጎ ብዙዎች ሥቃያትን አደረሱበት፤ ከዚያም ኅዳር ኻያ ዐምስት ክብር ይግባውና ጌታችን አምላካችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገልጦለት ስን ለሚጠራ መታሰቢያውን ለሚያደርግ የምሕረትን ቃል ኪዳን ከገባለት በኋላ ራሱን በተሳለ ሰይፍ ቈርጠውት የሰማዕትነትን አክሊልን ተቀዳጀ፤ የሰማዕታት ዘመን ካለፈም በኋላ በመላው ዓለም አብያተ ክርስቲያናት ታንጸውለታል፤ በተለይ በእስክንድርያ እና በኢትዮጵያ በስፋት ይከበራል፡፡
ኢትዮጵያዊዉ ሊቅ አርከ ሥሉስም የቅዱስ መርቆሬዎስን ተጋድሎ በማዘከር፡-
“ሰላም ለከ መርቆሬዎስ ዘሮም
መስተጽዕነ ፈረስ ጸሊም
አመ አንደዱ ታሕቴከ ውሉደ መርገም
እምቅሡፍ አባልከ እንተ ውኅዘ ደም
አርአያ ዝናም ብዙኅ አጥፍኦ ለፍሕም”
(በጥቊር ፈረስ ላይ የተቀመጥኽ የሮም ሰው ለኾንኸው ለመርቆሬዎስ ሰላምታ ይገባኻል፤ የመርገም ልጆች ከሥርኽ እሳትን ባነደዱ ጊዜ ከተገረፈው ሰውነትኽ በብዙ ዝናብ አምሳል የፈሰሰው ደም ፍሙን አጠፋው) እያለ መስክሮለታል፡፡

ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫም በተአምኆ ቅዱሳን መጽሐፉ ላይ፡-
“ሰላም ለመርቆሬዎስ ሰማዕት ንጹሕ ድንግል
ፈጻሜ ቃለ ወንጌል”፡፡
(የወንጌል ቃል የፈጸመ ለኾነ ለንጹሕ ድንግል ሰማዕት መርቆሬዎስ ሰላምታ ይገባል) በማለት አመስግኖታል፡፡
ምንጭ፡- አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ የደረሰው ተአምኆ ቅዱሳን መጽሐፍ ንባቡና ትርጓሜው የሚለው መጽሐፌ
ከመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ
የቅዱስ መርቆሬዎስ በረከት ይደርብን፡፡

Subscribe to:
Posts (Atom)