ቅድስት | ![]() | ![]() |
በዲያቆን መስፍን ኃይሌ
መጋቢት 4 ቀን 2008 ዓ.ም
የቤተክርስትያናችንን መዝሙር ንባቡን ከዜማው አስማምቶ አጠናክሮ ያስተላለፈልንኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ በጾመ ድጓው በዓቢይ ጾም ለሚገኙትን እሑዶች ሁሉ የተለየመዝሙር ስለሠራላቸው እያንዳንዱ እሑድ በመዝሙሩ ስም ይጠራል ። በዚህም መሰረት የዚህታላቅ ጾም ሁለተኛው እሑድ ቅድስት ተብሎ ተሰይሟል። ቅድስት የሚለው ቃል ግሱ"ቀደሰ"ሲሆን ለየ አከበረ መረጠ የሚል ትርጉም ይይዛል። ቅድስት ማለት የተየች የተመረጠች የከበረችማለት ነው። ቅዱስ የሚለው ቃል እንደ የአገባቡ ለፈጣሪም ለፍጡርም ያገለግላል። ለፈጣሪሲነገር እንደ ፈጣሪነቱ ትርጉሙ ይሰፋል ይጠልቃል ለፍጡር ሲነገር ደግሞ እንደ ፍጡርነቱ እናእንደ ቅድስናው ደረጃ ትርጉሙ ሊወሰን ይችላል። እግዚአብሔርን ቅዱስ ስንል የባህሪይው የሆነ፣ኃጢአት የማይስማማው ፣ለቅድስናው ተወዳዳሪ ተፎካካሪ የሌለው፣ ወደር የማይወጣለት፣ዘለዓለማዊ የሆነ ማለታችን ሲሆን ፍጡራንን ግን ቅዱሳን ስንል ቅድስናቸው የጸጋ የሆነ፤ከእግዚአብሔር ያገኙት ፤እንደነጭ ልብስ ጽድቁም ኃጢአቱም እንደ ዝንባሌአቸውየሚስማማቸው፤ ለቅድስናቸው ማዕረግ ደረጃ የሚወጣለት እንደ ገድል ትሩፋታቸው መጠንሊጨምርም ሊጎድልም የሚችል ማለታችን ነው። ከፍጡራን መካከል ለእግዚአብሔር የተለዩ ሁሉበጸጋ የቅድስናው ተሳታፊ ሊሆኑ ይችላሉ። መላእክት፣ ሰዎች፣ መካናት፣ ዕለታት ፣አልባሳት፣ንዋያት ሁሉ ለእግዚአብሔር እስከ ተለዩ ድረስ ከቅድስናው በረከት ይሳተፋሉ እንደ የደረጃቸውቅዱሳን ተብለው ይጠራሉ።
በዚህ ዕለት ስለ ቅድስና እንዲሁም ዘወትር በዕለተ ሰንበት ከሌሎች ቀናት በተለየ ሁኔታ ለጽድቅስራ እንድንበረታ፣ ለቅድስና እራሳችንን እንድንለይ ስለ ዕለተ ሰንበት ቅድስና ይሰበካል ይነገራል።የሚዘመረውም መዝሙር " ግነዩ ለእግዚአብሔር ወጸውዑ ስሞ ወንግርዎሙ ለአሕዛብ ምግባሮሀቡ ስብሐተ ለስሙ አክብሩ ሰንበተ ተገበሩ ጽድቀ ዝግቡ ለክሙ መዝገበ ዘበሰማያት ኀበ ፃፄኢያማስኖ ወኢይረክቦ ሰራቂ ድልዋኒክሙ ንበሩ ዘበላዕሉ ጸልዩ ኀበ ሀሎ ክርስቶስ" ትርጉም፦"ለእግዚአብሔር ተገዙ ስሙንም ጥሩ ሥራውንም ለአሕዛብ ንገሯቸው ለስሙም ምስጋናንአቅርቡ ሰንበትን አክብሩ እውነትንም አድርጉ ብል የማያበላሸው ሌባም የማያገኘው በሰማያት ያለመዝገብን ለእናንተ ሰብስቡ፤ ተዘጋጅታችኹም ተቀመጡ ክርስቶስ ወዳለበት ወደላይ አስቡ፡፡"
በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝቶ ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ያሬድ እንደ ዘመረልን በተለይ ሰንበት ነገረእግዚአብሔር በተለየ ሁኔታ የሚዘከርባት፤ ኅሊናችን ከምድራዊው ሃሳብ ወጥቶ ወደ ሰማይያዊውየሚነጠቅባት፤ ለቅድስና የተለየች ቅድስት ዕለት መሆኗን ይጠቁማል። በቅዱስ መጽሐፍም"የሰንበትን ቀን ትቀድሰው ዘንድ አስብ" ዘፀ. 20፥8 ተብሏል የሰንበትን ቀን አስቀድሞ የቀደሰየባረከ እራሱ እግዚአብሔር ነው" እግዚአብሔርም ሰባተኛውን ቀን ባረከውቀደሰውምእግዚአብሔር ሊያደርገው ከፈጠረው ሥራ ሁሉ በእርሱ ዐርፎአልና"ዘፍ.2፥3 እንግዲህ"የሰንበትን ቀን ትቀድሰው ዘንድ አስብ " የተባለው እግዚአብሔር አስቀድሞ የባረከውንየቀደሰውን እኛ ድጋሚ የምንቀድስ የምንባርክ ሆነን ሳይሆን በዕለተ ሰንበት እራሳችንን በተለየሁኔታ ለቅዱስ ተግባር እንድንለይ ለሥጋችን ከምንፈጽማቸው ተግባራት ይልቅ ለተግባረ ነፍስእንድናደላ ያስረዳናል። ምንም እንኳን ለስጋችን ስንባክን ጊዜ ቢያጥረን በዕለተ ሰንበት ግን ቅዳሴከማስቀድስ ቅዱስ ቃሉን ከመስማት ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ከመቀበል እንዳናስታጉልበስርዓተ ቤተክርስትያን ታዘናል።
ሊቃውንቱ በፍትሐ ነገሥት «ተጋብኡ ኩሎ ዕለት ኀበ ቤተ ክርስቲያን ወፈድፋደሰ በዕለተ ሰንበትወበበዓላት ወበዕለተ ትንሣኤ ዘውእቱ ዕለተ እሑድ፡፡" ትርጉም፦ " ሁልጊዜ በቤተ ክርስቲያንተሰብሰቡ፤ ይልቁንም በዕለተ እሑድ፣ በዕለተ ቀዳሚት፣ በጌታ በዓላት ወደ ቤተ ክርስቲያንተሰብሰቡ፡፡" /ፍትሐ ነገሥት ገጽ 254/ ብለው ለመንፈሳዊ ሕይወታችን ከሌሎች ቀናት በተለየሁኔታ ትኩረት የምንሰጥበት የምንቀደስበት ዕለት ቅድስት ሰንበት እንደሆነች ተናግረዋል ።ሐዋርያዊው ቅዱስ አትናቴዎስም በቅዳሴው ላይ ሰንበት የተቀደስች እና ሕይወታችንእንዲቀደስባት የተለየች ቀን መሆኗን ሲያስረዳ እንዲህ ይላል "ወንበል ዛቲ ዕለት እንተ ገብረእግዚአብሔር ንትፈሣሕ ወንትሐሰይ ባቲ" ትርጉም "ይህች ዕለት እግዚአብሔር የሠራት ያከበራትዕለት ናትና በእርሷ ፈጽሞ ደስ ይበለን" ሰንበት ለክርስትያኖች ለመንፈሳዊ ደስታ የተለየች ቀን ናት። የመንፈሳዊ ደስታ ምንጩ በነፍስ የሚገኝ መንፈሳዊ በረከት ነው ። ሰው የኃጢአትን ሸክምበንስሃ ሲያራግፍ፤ ነፍሱ በጸጋ እግዚአብሔር ስትቃኝ የሚሰማውን ደስታ በሌላ በምንም መንገድሊያገኘው አይችልም። ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ ሰንበት ቅድስትና ለቅድስና የተለየች ቀንመሆኗን ያስተማረን አስቀድሞ በነብያት ትንቢት ያናግር የነበረ መንፈስ ቅዱስ አነሳስቶት ነው ።
ስለ ሰንበት መለየትና መቀደስ እንዲሁም የመንፈሳዊ ሐሴት ቀን ለመሆኗ ነቢዩ ቅዱስ ዳዊትመዝሙሩ እንዲህ ብሎ ነበር "እግዚአብሔር የሠራት ቀን ይህች ናት፤ ሐሤትን እናድርግ፥በእርስዋም ደስ ይበለን።" መዝ. 117፥24 ቅዱስ ዮሐንስም ራእዩ ሰንበት የጌታ ቀን ስለመሆኗእንዲህ ይላል "በጌታ ቀን በመንፈስ ነበርሁ" ራእ. 1፥10 ሰንበት የእኛ ቀን ሳትሆን ለጌታችንየምንሰራባት የምንለይባት ፣የምንቀደስባት፣ ነገረ እግዚአብሔርን የምንዘከርባት የጌታ ቀን ናት ።ለቅድስና የተለየች ቅድስት ቀን ናት ። በተለይ የክርስቲያን ሰንበት እሑድ "በኵረ በዓላት"ትባላለች በኵር ታላቅ እና መጀመርያ ማለት ነው የመዳናችን መሰረት የተወጠነባት የጌታ የጽንሰቱቀን ዕለተ ሰንበት ናት ፤የመዳናችን ማረጋገጫ ፣የእምነታችን መሰረት ፣የበዓላት ሁሉ ዓቢይትንሳኤው የተፈጸመው በዕለተ ሰንበት ነው። እንግዲህ በዚች ቅድስት ዕለት፥-ለቅድስና በተለየችዕለትስ ሥጋውንም ነፍሱንም በሚያርያረክስ ተግባር የተሰማራስ ለነፍሱ ምን ዋስትና ይኖረዋል?
ቅድስት በተባለች በሰንበት እሑድ ማንም በምንም ምክንያት ወደ ቤተ እግዚአብሔር ከመሄድእንዳያስታጉል በስርአተ ቤተክርስትያን ተቀምጦልናል። ሌላው ቀርቶ በዕዳ በብድር በቀረጥበግብር በአስራት በበኩራት ይሉንኝታ ፈርቶ ማንም ቅድስት በምትባል በእሑድ ሰንበት ቅዳሴእንዳያስታጉል ማንም ማንንም በዚህች ቅድስት ዕለት ምንም አይነት እዳ እንዳይጠይቅ ታዟል።"ወኢይኅሥሥ መኑሂ በይእቲ ዕለት ንዋዮ እምካልኡ ወኢይጽሐቅ አሐዱሂ እምእመናን በእንተኃሥሠ ዕዳ ። አው ተጻልኦ አው በዘይመስሎ ለዝንቱ። ወይሑሩ ቦቱ ኩሉሙ ሰብእ ኀበ ቤተክርስቲያን ወይምጽኡ ኲሉ ለለ ፩ ፩ እምእመናን ኅቤሃ በንጽሕ ወበትህትና ዘእንበለ ፍርሃት እምነመኮንን ወእም በዓለ ዕዳ አው እምፈታሒ አው ዘይመስሎ። ወእመሰ ተሀበለ ፩ሂ ክርስቲያንምክዕቢተ ይፍዲ " ትርጉም፦ "ከምእመናን ወገን አንድስ እንኳ በእሑድ ቀን ለገንዘብ መትጋት፤ገንዘቤን አምጣ ብሎ መጣላት፣ ዋስ መያዝ አይገባውም ። ሁሉም ምእመናን ወደ ቤተክርስቲያንበንጽሕና በትሕትና ሆነው ይምጡ እንጂ ። ዳኛ ግብሬን፣ አበዳሪ ብድሬን ፣ኤጲስቆጶስ ዐሥራትበኵራት ፣ ነጋ ድራስ ቀረጥ አምጡ ይሉናል ብለው ሳይፈሩ ይምጡ። ከነጋድራሶች አንዱ እንኳወደ ቤተክርስትያን ከሚሄዱ ሰዎች ቀረጥ ይቀበል ዘንድ የድፍረት ሥራ የሠራ ቢሆን እጽፍአድርጎ ይክፈል። " ፍትሐ ነገሥት ገጽ 258-259።
ቅድስት ቤተክርስቲያን ይህን ያህል ጥንቃቄ የምታደርገው ሰዎች በተለያየ ምክንያት ከቤተእግዚአብሔር እንዳይርቁ ከዛም አልፎ ተበዳይም ሆነ በዳይ ፣በዕዳ የሚጠየቅም ሆነ የሚጠይቅሁለቱም በአንድነት ቅዱስ ቃሉን ሲሰሙ ዋሽቶ የሰው ዕዳ ያልከፈለውም ተጸጽቶ ይክሳል ወራትብሶበት ቀን ጥሎት መክፈል ላልቻለውም ምህረት ይቅርታ እንዲያገኝ ቅዱስ ቃሉ ጸሎቱምክንያት ይሆነዋል ። በዚህም የተነሳ ሁለቱም ወገኖች በክፉ ከመፈላለግ ይልቅ የይቅርታየምህረት ሰዎች ይሆናሉ። እንግዲህ በዚህች በኵረ በዓላት በምትሆን በቅድስት በዕለተ ሰንበትየምእመናን መንፈሳዊ ሕይወት ይባረካል ይቀደሳል በዚህ ታሳቢነት ዕለቱም ዕለተ ቅድስና መሆኑንለማጠየቅ ቅድስት ተብሏል ።
ቅድስና የተፈቀደልን ብቻ ሳይሆን የታዘዝነውም ጭምር ነው "እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁቅዱስ ነኝና እናንተ ቅዱሳን ሁኑ" ዘሌ.19፥2 በዚህ ኃይለ ቃል ውስጥ ቅድስና እንደ ፈቃድምእንደ ትእዛዝም ሆኖ ተሰጥቶናል እግዚአብሔር ያልፈቀደውን ነገር አድርጉ ሁኑ ብሎ አያዝም ።የቅድስና ሕይወት መሰረቱ የእግዚአብሔር ፈቃድና ትእዛዝ ሆኖ ሳለ ለመቀደስ የእኛ መሻትመፈለግ ዝንባሌም ወሳኝ ነው። ለዚህም ነው ሐዋርያው እንዲህ ሲል የጻፈልን "ትቀደሱም ዘንድፈልጉ፥" ዕብ 12፥14 ምንም እንኳን ቅድስና የተፈቀደና የታዘዘ ቢሆንም የውዴታ እና የነጻፈቃድ ውጤት እንጂ የምንገደድበት አይደለም። እግዚአብሔር ፍቅሩ ገብቶን ወደን እና ፈቅደንበፈቃዱ እና በትእዛዙ ስንመራ ያስደስተዋል እንጂ ተገደን ፈርተን ተንቀጥቅጠን እንድንገዛለትአይወድም ።
ወደ ቅደመ ነገራችን ስንመለስ ዕለተ ሰንበትም ቅድስት መባሏ ከላይ ያብራራነውን መሰረታዊሃሳብ በተከተለ መልኩ ነው። ዕለቲቱ ቅድስት መባሏ ዋና ዓላማ በሰዎች እና በእግዚአብሔርመካከል ለቅድስና ሕይወት ምልክት ማስታወሻ እንድትሆን ነው። በባህሪው ቅዱስ የሆነ አምላክዓለምን የማዳን ስራውን የጀመረበትን ጽንሰቱን እንዲሁም የማዳን ስራውም አጠናቆ ሙስናመቃብርን አጥፍቶ ዘላለማዊ ሕይወትን ያበሰረበትን ትንሳኤውን የምናስብበት በመሆኑ የዕለቱቅድስና የፈጣሪን ቅዱስ ተግባር የምናደንቅበት ከማንኛውም የሥጋ ሥራ ተለይተን የዋለልን ሁለታከፍ ከፍ እያድረግን እርሱን የምናመሰግንበት ዕለት ነው። ይህም እኛን ወደ በለጠ የቅድስናሕይወት የሚያሸጋግረን ከመሆኑም በላይ የእግዚአብሔርን ጥልቅ ፍቅር በየጊዜው እንድናስብናበፍቅሩም እንድንኖር ያግዘናል።
ከጾሙ በረከት ያሳትፈን!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር።
|
No comments:
Post a Comment