በማለዳ መያዝ ፦ምእራፍ -አንድ 1✿የክፉ መንፈሶች ድርጊት
በስመ አብ
ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን ፡፡
✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿
"የዘመኑንስ ምልክት መለየት አትችሉምን">>ማቴ.16÷3
የክፉ መንፈስ ድርጊት ማለት ፤ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ፤በሰው አማካይነት ፤ሌሎችን ለመጉዳት
ተብሎ ፤ ከአጋንንት ጋር የሚመሰረትና የሚደረግ ግንኙነት ማለት ነው፡፡ ክፉ መንፈሶች
በሕይወታችን ፣በኑሯችንና በዘመናችን ውስጥ ጣልቃ በመግባት ፤ጉዳት የሚያደርሱ
አደገኞች ይሁኑ እንጂ ፤የእግዚአብሔር አምላክ ጥበቃ እስካለ ድረስ ፤ የጥፋት አቅምና ኃይላቸው ፍጹም ውሱን
የሚሆነው የእምነትና የአምልኮት ጥንካሬ ሲኖር ብቻ ነው፡፡ ዛሬ የክፉ መናፍስቱ ጥቃት ከመቼውም ጌዜ በበለጠ
የተስፋፋና የተመቻቸ ፤ጉዳት የማድረስ ችሎታቸው ፤የዚያኑ ያህል የተጠናከረ ከመሆኑም በላይ ፤የህብረተሰብን ማህበራዊ
አኗኗርን በመለማመድና በመመሳሰል የክፉ መንፈስ ጥቃት የረቀቀ ሥልታዊ ሆኖአል፡፡ ለእነዚህ የሰው ልጆች ጠላቶች
ፍጹም መጠናከር ፤ ከፍተኛ ርዳታና እገዛ ያደረጉት ደግሞ ፤በሚያስገርም ሁኔታ ፤ ራሳቸው ሰዎች ናቸው ፡፡ እንዴት ?
እስቲ ሁሉንም በዝርዝር እንመልከት ፦
<<እግዚአብሔር የደሚወዱትን ሁሉ ይጠብቃል ፤>> መዝ.144(145)20 1.1 የዛር መንፈስ ፤
✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿
ዛር የሚባለው ከዘር የተወረሰ ፤ከዘር የመጣ ፤በዘር የሚሄድ ማለት ሲሆን
፤ትርጉሙም ፤ለሰው ዘር ተመሳሳይ ተፈጥሯዊ ባህርይ ያላቸው ሁሉ ፤በዘር ውስጥ ማለፋቸውን የሚያሳይ ምልክት
ነው፡፡የዛር አጋንንትና ሰይጣን በቤተሰብ ውስጥ ሲመለክና ሲገበር ቆይቶ ፤ከአምላኪዎቹ የሚወለዱት ልጆች ሁሉ
፤መንፈሱ አብሯቸው ተወልዶና አድጎ ፤መጨረሻ ላይ ፤የኔ ዘር ናቸው በማለት በኃይል ያርፍባቸዋል፡፡ በዚህ ረገድ
ዲያቢሎስ ልዩ የሆኑ በአራት የተከፈሉ ዕቅዶች አሉት ፡፡
☞የሰውን ሕይወት ሙሉ ለሙሉ
መቆጣጠርና መምራት ፤የሚሔድበትን አቅጣጫ መለየት ፤
☞በከፍተኛ ፍጥነትና ግፊት ዕቅዱን ተግባራዊ ማድረግ ፤ ☞የጥቃት አድማሱን ማስፋፋትና መገምገም ፤
☞ለጊዜው በአጥቂነት የሚጠቀምባቸውን ሰዎች መሳሪያዎቹ በማድረግ ፤የኢኮኖሚ አቅም ማጎልበት ፤ክብርና ዝናን
ማጎናፀፍ ፤ሌሎች ብዙዎች የሚጠፉበትን መንገድ ማመቻቸት እና በተግባር መፈጸሙን ማረጋገጥ ነው፡፡
እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት
የሳጥናኤል እቅዶች ሲሆኑ በአፈጻጸም ሂደት ውስጥ ለሰብአዊ ፍጡር መረጃ እንዲያገኝ ምንም አይነት ፍንጭ አይሰጥም
፡፡ የክፉ መንፈሶች የገሐዱ ዓለም ላይ በተጨባጭ ገጽታ አለመታየታቸው ብዙዉን የሰው ልጅ የትውልድ ህልውናን
ሲፈታተኑ፤ ከመኖራቸውም በላይ እግዚአብሔር ለሰው ልጅ የሰጠውን ተስፋ ክብር ጸጋና በረከትና ምገስን እንዳያገኝ
ለመፋለም የራሳቸውን ክፋትና ጥፋት መፈጸሚያ በማድረግ ሲጠቀሙበት ኖረዋል፡፡ይህንንም በቃየን ሕይወት ማየት
ይቻላል፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን የዛር ምልክት ለመጀመሪያ ጊዜ የታየውና ለዘር
መበላሸት ምክንያት የሆነው ሰው ፤ ቃየን ነው፡፡ ቃየን ማለት ፤ከእብራይስጥ ቋንቋ ወደ አማርኛ ሲተረጎም
፤የጦር አበጋዝ ማለት ነው፡፡
የአቤልና የቃየን መስዋዕት በእግዚአብሔር ፊት
✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿
" እግዚአብሔር ወደ አቤልና ወደ መስዋዕቱ ተመለከተ ፤ ወደ ቃየንና ወደ መስዋዕቱ
አልተመለከተም ፡፡" ዘፍ .4÷4-6 ቃየን እጅግ ተናደደ ፤ፊቱም ጠቆረ ፡፡ እግዚአብሔርም ቃየንን አለው
፤"ለምን ተናደድህ? ለምንስ ፊትህ ጠቆረ? መልካም ብታደርግ ፊትህ የሚበራ አይደለምን? መልካም ባታደርግ ግን
ኃጢአት በደጅህ ታደባለች ፤ ፈቃድዋም ወደ አንተ ነው፡፡ ግን በእርስዋ ንገስባት፡፡" አለው፡፡በዚህ
የእግዚአብሔርን ቃል ውስጥ የተገለጸት ፤ ኃጢአት ታደባለች፡፡ ፤ፈቃድዋ እና በእርስዋ ንገስባት የሚሉት ሦስት
ቃላት የሚያመለክቱት ፤የሴት ጾታን ነው፡፡
ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ፤ቃየን የሴት ዛር አጋንንትን በጥፋት መንገድ
እርሱንና ትውልዱን ትመራ ዘንድ ነገሠችበት፡፡
የቃየን መስዋዕት የስስት ፤ የንፉግነትና እግዚአብሔር ን የማይፈራና የማያመልክ
መሆኑን ዲያብሎስ ስለአወቀ ፤እርሱን ለክፋት ፤ለቅናት ፤ለንዴትና ለፊት ማጥቆር እርግማን በመሳሪያነት መግለጫው
በማድረግ ምድራዊ የኃጥያት አሰራርና ምት በይፋ መንገድ አገኘ፡፡ በዚህ የተነሳም ፤ ንጹህ ወንድሙን አቤልን
አለምንም በደል ፤ በጥላቻና በልበ ቂመኘነት ተነሳስቶ ፤ በድንጋይ ወግሮና ደሙን አፍስሶ ገድሎታል ፡፡
ስለዚህ የቃየን መንፈስ ፤የደም አፍሳሽነት ወይም የግድያ ወንጀል ጀማሪ በመሆን ፤ ዲያብሎስን የሰው ልጅ ዘር
አጥፊነትን በገሐዱ አለም ያለ እድሜ መሞትን ማሳያ በማደረግ ተጠቀመበት ፡፡ደጉ፣ ብሩኩና ቅዱሱ ሰው አቤል
በአምልኮቱ ምክንያት ምተ፡፡ አሁን መስዋዕቱን እግዚአብሔር የሚቀበለው ሰው የለም፡፡ ለአምልኮት ክብር የሚሰጠው ሰው
በአጠቃላይ አምላክ የወደደው ሰው ፤ አቤል የለም፡፡ለምድር የቀረው በሕይወት ያለው ቃየን ነው፡፡
ወንድሙን ያሳደደ፤ ደሙን
ያፈሰሰ ፤በድንጋይ ወግሮ የገደለ፣የተረገመው ቃየን አለ፡፡ቅናት ፣ተንኮል ፣ክፋትና ምቀኝነት መሠረታዊ በመሆን
ዕድሉን ያገኙት፤ለመጀመርያ ግዜ በቃየን ሕይወትና ዘመን ውስጥ ነው፡፡
አዳም ከገነት መሸሽ ፣መራቆትና መደበቅ በነበረው አስፈሪና
አሳዛኝ በሆነው ሂደት ላይ የቃየን ተግባር ወንድሙን በመግደል ሲጀመር ለቀጣዩ ትውልድ የግድያ አስተማሪነቱ
ለዲያብሎስ አላማ ልዩ መርሆ ሆኗል፡፡
ይህ አለም ቃየንን ይወዳል ፡፡በዚህ ምድር ስትኖር ፤ስትወጣ ፣ስትገባ ፣ስትሰራ
፣ስትማር ፣ስታገኝ ፣ስትደሰት ሁሉ በመንገድህ ላይ ፤ከግራ ፣ከቀኝ ፣ከኀላ ፣ከፊት ፣ከላይ ፣ከታች ሳይቀር ፤የቃየን
መንፈስ አለ፡፡
የእግዚአብሔር ቃልና የቃየን ድምፅ
✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿
<<እግዚአብሔርም ቃየንን አለው ፤ወንድምህ አቤል ወዴት አለ? እርሱም አለ ፤ አላውቅም ፤ የወንድሜ
ጠባቂ እኔ ነኝ? አለው ፦ምን አደረገህ? የወንድምህ የደሙ ድምፅ ከምድር ወደኔ ይጮሀል ፡፡አሁንም የወንድምህን ደም
ከእጅህ ለመቀበል አፏን በከፈተች ምድር ላይ አንተ የተረገምህ ነህ፡፡ምድርንም ባረስህ ግዜ እንግዲህ ሀይሏን
አትሰጥህም፡፡በምድር ላይ ኮብላይና ተቅበዝባዥ ትሆናለህ፡፡>> አለው ዘፍ.4÷9
<<እግዚአብሔር ተናግሮአልና ሰማያት ስሙ ፣ምድርም አድምጪ ልጆችሽን ወለድሁ ፤አሳደግሁም ፣እነሱም
አመፁብኝ፡፡>> ት/ኢ.1÷2
በአዳም፣ ሔዋንና በተተኪው ትውልድ ውስጥ የዲብሎስ አስተሳሰብ ጅማሬ
✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿
ንዴት ፦የጠብ መጀመሪያ አባት እንዲሆን በቃየን ሕይወት ዲያብሎስ ከመገለጹ በላይ ፤በወንድሙ ላይ የፊት
ማጥቆርና የመቀየር ገጽን የአካል ክፉ ጠባይ ጽንሰ ሀሳብ የሚታይበት ሆኖ ቃየን እንዲገለጥ አድርጎታል ፡፡ በቃየን
ሕይወት የተጀመረው ቅናት ፣ ንዴት ፣ክፋት ፣ተንኮል ፣ ምቀኝነት ፣ግፍ ፣ ቁጣ ፣ብስጭት ፣ቂም እና በቀል
እነዚህ ሁሉ የዲያብሎስ ሀሳቦች እስከ ዛሬ ድረስ በሰው ልጅ ልብ ውስጥ መሠረታዊ የኑሮ አካል ሆነው ከመገኘታቸው
በላይ ፤ ለዘመናት የሰው ዘርና ተፈጥሮን ሲያበላሹ የቆዩ የዲያብሎስ መርሆዎች ናቸው፡፡
በቃየን የተጀመረው
የፊት ማጥቆር ጠባይ ዛሬም ብዙ ሰዎች ክፉ መንፈስ በውስጣቸው ሲኖር ይሄው ችግር ሙሉ በሙሉ ይከሰታል፡፡ ፊታቸውና
ቋንቋቸዉ ይለወጣል ፣ይናደዳሉ ፣ይቆጣሉ ፣ ይራገማሉ ፣ያማርራሉ ፣ መንፈሱ ከተገለጠ ደግሞ ፣ ያጓራሉ ፣ወይም
በጣም ይጮኸሉ፡፡ ግልፍተኞ በሆኑ ጊዜም የሚያደርጉትን ስለማያውቁ ፣ቤተሰብንና በቅርብ ያለውን ሁሉ ሊጎዱ ይችላሉ
፡፡ደም ካላዩ የማይረኩና የማይበርዱ ይሆናሉ፡፡ ቃየንም ፣ጊዜያዊ እርካታ ያገኘው ወንድሙን ከገደለ በኀላ ነበር፡፡
የደም ፍርድና የግድያ ዛር
✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿
በቃየን የተጀመረው የግድያ ውሳኔ ለዲያብሎስ የጥፋትና የሞት አሠራር ዋና ግብ አድርጎት ፣የሰው ልጅን ወደምት
የመምራት ስልጣን የማግኘቱ ውጤት አንዱ መንገድ ሆኖአል፡፡ ቃየን ወንድሙን የሚያስገድል መንፈስ ያዘው ፣ ደምን
የሚያፈስ ፣ደም ማየት የሚወድ ከአዳም ቀጥሎ ሁለተኛ የኃጥያት የግድያ ወንጀል ጀማሪ እንዲሆን ሰይጣን ተጠቀመበት
፡፡
ስለዚህ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ደም ማየት የሚፈልጉ ዛሮች የሰውን ልጅ
በመቆራኘት ፣በዓለም የህብረተሰብ ባሕል ውስጥ በተለያየ መንገድ የደም መፍሰስ ፍላጎትን አዳበሩ በእንስሶች በዶሮ ፣
በበግ የሚረጋጉ ዛሮች በአገራችን ሰፊ ቦታ ነበራቸው፡፡ ያ ሂደት ተቀይሮ በምድራችን ላይ ለዘመናት ያልተቋረጠ
የጦርነት ደም ሲፈስ መኖሩ የዛሮቹ ዕድገት መሳያ አንዱ ምልክት ነው፡፡ በአሁኑ ዘመን ያሉ ዛሮች የቀድሞ
ጠባያቸውን ለቀው ዘመናዊ የአጠቃቀም ሥልት በመያዝ ሲማሩ መማር ፣መሪ ሲሆኑ አብሮ መሪ መሆን ፣በሥልጣን
፣በማዕረግና በሀብት አለመርካት የመሳሰሉ ጠንቆችን ሥር የሰደደ ባሕርይዎች እንዲሆኑ በማድረግ ለክፉ ተግባራቸው
መገልገያ አድርገውታል ፡፡
ከማለዳ በዓመፅ ታሪክ ውስጥ መኖር
✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿
የዓመፅ ጅማሬ ታሪክ ሲነሳ፣ የቃየን መንፈስ በአመፀኝነት የፈጸመው የግፍ ግድያ ተግባር ፣ብዙ ደም በዓለም ላይ
ላፈሰሱ ፣ግጭቶች የመጀመሪያው አባትና አስተማሪ መሆኑን መዘንጋት የለብንም፡፡ ካለፉት ብዙ ዘመኖች ውስጥ በዓለማችን
ዙሪያ የተካሄዱ ጦርነቶችና እልቂቶች የዓመፃ ግፍ የአፈጻጸሙ ማሳያ ሆነው ፣ለአሁኑ ዘመን ትውልድና ርዕዮተ -ዓለም
የሞት ማገናዘቢያ የጥፋት ልጅ ሆነው፣ዛሬ የሚረግሙት ፋሽስቶችና ናዚዎች በመባል እየታወሱ የጥላቻ ታሪክ
ማንጸባረቂያ ሆነዋል ፡፡ በቃየን ዘሮች ውስጥ የተከሰተው የጦረኝነትና የጦር መሣሪያ ፍልስፍና ዛሬ አድጎ ወደ
አቶሚክ ደምሳሽ ቦንብና ወደ ኑክሌር የጨረር ሞት የሰው ልጅ መድረስ፣ዲያብሎስን ለጥፋት ዓላማው የላቀ እርካታ
እንዲያገኝ አግዞአል፡፡ሌላው የቃየን ዘር መንፈስ ፣ወንዝን ተከትሎ መኖርንና ፣የወንዝ ውኃ መንፈስን ማምለክ
፣መጠየቅና ማማከር ፣ከወንዝ አጋንንት ጋር መዳበልና መዛመድን የጀመረ ትውልድ ነው ፡፡ይህን ሂደት ለዲያብሎስ
በሰው ልጅ ልብ ውስጥ ውጣውረድና ዓመፃ እንዲመሰረት ረድቶታል ፡፡ ስለዚህ የ21ኞው ክፍለ ዘመን ትውልድ የሰይጣን
የክብረ በዓል ቀንን ያከብራል ፡፡"ሐሎይ" በመባል የሚታወቀው የሰይጣን ቀን ዓለማቀፋዊ በዓል እንዲሆን አንዳንድ
አገሮች ወስነዋል ፡፡ስለዚህ አሰላለፉ ፣ሰይጣን ሰው ሰይጣን ሆኖአል ማለት ነው፡፡ የቃየን የመጀመሪያ ዓመፅ በብሉይ
ኪዳን ውስጥ አልፎ ፣በአዲስ ኪዳን ውስጥ ኢየሱስ ክርስቶስን በመስቀል ፤ሐዋርያትን በማሳደድና በመግደል ፣ከዛም
ቤተክርስቲያንን በማቃጠልና ክርስቲያኖችን በመውረር ፣ጣዖታትን በማምለክ የነበረው የከሃዲነት መንፈስ አድጎ ፤ዓለም
የዓመፃ ዘመን ላይ ደረሰ፡፡
ሰው እጅ ላይና ዲያቢሎስ ላይ የወደቀ ትውልድ
✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿
አቤል ያለእድሜው በወንድሙ እጅ ላይ ወድቆና ተወግሮ ደሙ ፈሶ ሞተ፡፡ በዚህም ዘመንና
ጊዜ ብዙ ሰዎች ፤ የአገር መሪዎችን ጨምሮ ፤በሰው እጅ ላይ ወድቀው መገኘት ፤የተለመደ ችግር ሆኖአል ፡፡በስራ
፣በእውቀት ፣ በሥልጣንና በመርሐ-ግብር ፣በርዕዮተ ዓለም ጫና ፣በኢኮናሚና በተመረዘ የአስተሳሰብ ተጽእኖ ሥር
መያዝ ወቅታዊ ክስተት ሆኖ ይገኛል ፡፡
የችግሩ አጣብቄም የፈቃደኝነት ግዴታና የግዴታ
ፈቃደኝነት ውስጥ የመግባቱ ጠባይ ከሕልውና ጋር የተያያዘ እንዲሆን ገና ከማለዳ ክፉው መንፈስ የሚያዘጋጀው ሴራና
ተንኮል እንደሆነ የዘመኑ ሳይንስ አልተረዳውም ፡፡ከዚህ ገጎን የማቴሪያልና የስነ-ጥበብ አምልኮት የዘመኑን ሊሕቃን
በፍልስፍና ውስጥ እንዲደበቁና የማይታየውን የክፉ መንፈስ ዓለም እንዲዘነጉት በማድረግ ዲያቢሎስ ልዩ ሚና ተጫውቷል
፡፡ ብዙ የዓለም ምሁራኖች በግሪክ ሥነ-ቃል ተዋጽዖ የሳይንሳዊ ስያሜ ላይ ዕድሜያቸውን ጨርሰ ውና እምነት
አልባ በመሆን ፤ በነፍሰ ሕይወት ተዋርደዋል፡፡ በጤናና በሕክምናውም ረገድ ተመሳሳይ ብዙ ስሕተቶች በዲያብሎስ በኩል
ተተግብሯል፡፡እንግዲህ በዓለም ላይ ያለዉ ችግር ከመነሻው ብቻ ሳይሆን ከመድረሻዉ ላይ የክፉ መንፈስ ውስብስብ
ፈተናና በሳይንስ የማይፈታ ችግር ሆኖ ይኖራል ፡፡
በቃየንና በዘሩ ውስጥ የኃጢአትና የሞት ንግስት ዛር ✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿~
"መልካም ብታደርግ ፊትህ የሚያበራ አይደለምን ? መልካም ባታደርግ ግን ኃጢአት በደጅ ታደባለች ፤ፈቃድዋም ወደ
አንተ ነው፤አንተ ግን በእርስዋ ንገሥባት፡፡ቃየንም ወንድሙን አቤልን ፤ና! ወደ ሜዳ እንሂድ አለው፡፡ሜዳም ሳሉ
ቃየን በወንድሙ በአቤል ላይ ተነሳበት ገደለውም፡፡" ዘፍጥረት .4 ፥7-8
ዛሬ መላውን ዓለምና የሰው ዘር ትውልድን እያናጋው ካለዉ ክፉ መንፈሶች አንዱ ፤የሴት ዛር
የአያያዝ እሽቅድድም እየተጠናከረ መምጣቱ ነው፡፡
በቃየን ልብ ውስጥ ንግሥናን ያገኘችው የኃጥያት ዛር የሴት
አጋንንትና ሰይጣን፤የሴትና የወንድ ግብረ-ሰዶማውያንን (የሌዝብያንና የሆሞዎችን)መብት ሕጋዊ የጋብቻ አካል እንዲሆን
በማድረግ ፤ብዙ የክርስቲያን ልጆች ፤ልብና ሕይወት አግኝታለች ፡፡
አሰላለፏን ዘመናዊ
በማድረግ እንደ ትውልዱ ጠባይና አስተሳሰብ ሥልቷን በመለዋወጥ ፤ትውልዳችን በክፉ አመልና ሱስ ከእምነትና ከአባቶቹ
የሃይማኖት ሥነ-ምግባር እንዲ መጣ በማድረግ፡ ከክህደት ርዕዮት ውስጥ ወደ ኃጢአት ምት በመምራት ላይ ትገኛለች
፡፡
ከማለዳ መበላሸት
✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿
ቃየን በኃጢአት
ላይና ሀጢያት በቃየን ላይ ከነገሰች በሁዋላ ኮብላይና ተቅበዝባዥ እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል ፡፡ዛሬ
የእያንዳንዱ ቤተሰብ ልጆች ፤በዚች የኃጢአት ንግስት ከማለዳው ስለሚያዙ የራሳቸው ፍላጎትና አስተሳሰብ እየመሰላቸው
በክፉ መንፈስ በሚከተሉት መንገድ ይመራሉ፡፡ ለምሳሌ
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ ያሉ ተማሪዎች ፤በሱስ መንፈስ ለመያዝ በጣም የቀረበና የሰፋ ዕድል ያላቸው ሲሆን
፤ይህንኑ ክፉ የሱስ መንፈስን የሚያስፋፋ ፣የንግድ ቤቶች በየትምህርት ቤታቸው መግቢያና መውጫ በር ላይ ገበያቸውን
በማደራጀት ፤ወጣቱ በዘመናዊ የጥፋት ሥልት ውስጥ እንዲገባ አድርገዋል ፡፡
ከመነሻው አዲሱን ተተኪ ትውልድ ከትምህርት ቤት ደጃፍ እየተቀበሉ ከሚያሰናክሉና ከሚያበላሹ የጥፋት መንገዶች መካከል ጥቂቶቹን እንመልከት ፤☞
♦እንሞክረው ፤እንየው ፤ለጥናት ጥሩ ነው በማለት ፤ጫት አብሮም ሲጋራ ፤በመቀጠልም ሺሻ ፣ሐሺሽ ፣መጠጥ
ወዘተ...ይጀምራል ፡፡
♦ከአደንዛዥ ዕጾች በተጓዳኝ ፣የወሲብ ፊልምችን በጋራና በተናጠል በመመልከት ፤የኃጢአት ንግሥቷ ዛር
በውስጣቸው ቤትዋን ትሠራለች፤
♦የኃጢአቷን ንግስትየሚያበረታቱ ዘፈኖች ፤ከወሲብ ቀስቃሽ አለባበስ ጋር በመታጀብ ፤ልቅ
የሆነ ጠባይ እንዲወርሱ ያደርጋል ፡፡ ♦የሚያስፈሩና የሚያሰቅቁ (ሆረር) ፊልምች ውስጥ ፣ደም የሚመጡ የሰው
ፍጡሮችን ፣ቤት ፣መንገድ ፣ ንብረት ፣በፈንጂና በሮኬት ፣በአውሮፕላን ድብደባ ሲወድም ፣የሰው ሕይወት በአሰቃቂ
ሁኔታ ሲያልፍና አካሉ ሲጓድል በማሳየት ፤ዕድሉን ከፊልሙ ጋር እንዲያያዝ አድርገው እያደር የወደፊቱ እጣ ፈንታው
በመንፈሱ ወይም በመንፈስዋ እንዲወሰን መንገድ ይጠርጋል ፡፡ከዚህ በኋላ
ትውልዱ ጥፋትን አይቶና ተምሮ በመንፈሱ ተገዶ ክፋትን ቢሰራና ቢፈፀም ፤የሚያስቆጭና የሚያስገርም አይሆንም
፡፡ ሌሎች ተመሳሳይ የጥፋት መንገዶችም እንደቀልድና እንደ ዋዛ ፤ከዘመናዊነት ውስጥ በመመንጨት ፣ትውልዱን ወደ
ተበላሸ አቅጣጫ ሲወስዱት ብዙ ጊዜ ተስተውሏል ፡፡ይህ ሁሉ የመናፍስቱ ድርጊትና የጥቃት ሥልት መሆኑ በአንክሮ
ሊታወቅ ይገባል ፡፡ ♦በኃጢአት ንግስት ዛር የተለከፉ ሰዋች ሁሉ ፤ያዩትንና የሰሙትን ፣ያደረጉትንና
የፈፀሙትን ፣ወደ ማዕረግ እና ወደ ሥልጣን በማዉጣት ፤ከመልካም ነገር ይልቅ ፤ክፋትን በማበረታታት ፤ክፉዋንና
ክፉውን መንፈስ የሚጠቅሙ አገልጋዮች ይሆናሉ ፡፡
♦ በዚህ ክፍለ ዘመን ያለው ትውልድ ፤ከትምህርትና ከእውቀት
ጋራ በተያያዘ ሁኔታ ከሚገጥሙት ፈተናዎች መካከል ፤በኢንተርኔት ላይ ያለ ስራ ተጎልቶ በሚጨርሰው ሰፊ ጊዜ
የተነሳ ፤በዓይን የሚያርፉ የሱስ መንፈሶች በላቀ ሁኔታ እየተጠቃ የመገኘቱ ሁኔታ አንዱ ነው፡፡
እነዚህ
በኢንተርኔት ማለትም በምስጢራዊ የአጋንንት አምልኮት ስር የሚለቀቁ የመንፈሱ የአስተሳሰብና የክህደት
፤ዘዴዋች፤የሳይኮሎጂ ፤የስሜት ፤የወሲብ ፤የአስትሮሎጂ ፣ወዘተ....ተዋጽኦዎችን በሙሉ የ ሚያጠቃልሉ ሲሆን
፤በምንሰጣቸው ከፍተኛ አትኩሮት እና ተመስጦ የተነሳ የሚገቡ መንፈሶች ናቸው ፡፡ብዙ ጊዜ በኢንተርኔት ላይ ያለ
ተጨባጭ ስራ ተጎልተው የሚያሳልፉ ሰዎች፤ልክ እንደ ካርታ ሱስ ውለው ቢያድሩበት አይሰለቹም ፡፡አንዳንዶች ውለው
እንዳደሩበት ምን እንዳዩ እንኳን ሲጠየቁ ፤አስታዉሰው ለመናገር ያዳግታቸዋል ፡፡
✿በዚህ በኢንተርኔ ሱስ
የተለከፉ ሰዎች ፤በሳይንሳዊ ትንታኔ ሕብረተሰቡንና ቤተሰባቸውን ግራ በማጋባትና በማስቸገር ፤ሌሎችን ከእምነት
ጎዳናና አንባ ለማስወጣት፤በንቀት ቋንቋ የሚናገሩ፣የሚተቹ፣የሚቃወሙ፣የሚያፌዙና አዋቂ ሆነው ለመቅረብ
የሚጥሩ፣በአጠቃላይ፤ክፉው መንፈስ የሚመላለስባቸው ማደሪያው ይሆናሉ ፡፡
ይህ የሚያመለክተን፤ክፉ መንፈሶች
የዘመኑን የእውቀትና የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በመጠቀም፤በረቀቀ ጥበብ፣ከእግዚአብሔር መንገድእንዴት እነደሚያርቁ፣የሞትና
የነፍስ ጉዳት በማድረስ ላይ የሚገኙ መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው፡፡ ይህ ማለት ግን፤ኢንተርኔትን ጨምሮ ሌሎች
የቴክኖሎጂ ውጤቶች በሙሉ፤ማለት ሳይሆን በዚህ ረገድ ኃጢአትን የሚያበረታታውን ፤ነዉርና ከሞራል ሥነ-ምግባር
የወጣውን፣በአጠቃላይ ክፉ መንፈስ የሚመራውንና ከእግዚአብሔር ሕግ የወጣውን፤በተለይ በኢንተርኔት የሚለቀቁትን
የክፉ መንፈስ መልዕክቶችን አሉታዊ ተፅእኖ ለማመልከት ነው፡፡በአጭሩ፤ኢንተርኔት የሚጠቅመንን ያህል፤በዚህ መንገድ
ከተጠቀምንበት ደግሞ፤ሊጎዳን እንደሚችል የሚጠረጠር መሆን የለበትም፡፡ የሚፈውስ መድኃኒት እንዳለ ሁሉ፤የሚገድልም
መድኃኒት አለ፡፡ብርሀን እንዳለ ሁሉ ጨለማም አለና !፡፡
እንዲህ አይነት ችግሮችን በዘመናዊ መንፈስ ተጽእኖ
ያዳበሩ ሰዎች ባሉበት አካባቢና መንደር የሚወለዱ ልጆች፤ወላጆቻቸውን ጨምሮ፤ጭንቀት፤መረበሽ፤የልብ መደንገጥ፣እንቅልፍ
መጣትና መቃተት፣ጠብና ሳያውቁት መነጫነጭ፣መበሳጨትና ግልፍተኛ መሆን፣እቃ መስበር፣መግዛትና ደግሞ መስበር፣በድርጊቱ
መርካት፤የባልና ሚስት መለያየት መበጣበጥና መጯጯህ፤ሌሊት ሳያውቁት በር ከፍቶ መውጣት፣ገንዘብን ከቦርሳ አውጥቶ
መጣል፣ቀንመደበትና ሌሊት መንቃት፣ሞትን መፈለግና በተቃራኒው ማማረር ወዘተ............መንፈሱና ሰዎቹ ያሉበት
አካባቢ መለያ ባሕርይ ነው፡፡
በአካባቢው የሚወለዱ ልጆች ጠባይ
✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿
በአብዛኛው ቅብጥብጥ፣ትምህርት የማይወዱ፣የአመጋገብ ፍላጎታቸው የተዘበራረቀ፣አንድ ጊዜ ከአቅም በላይ የሚበሉ
ሲሆን፤በሌላ ግዜ ደግሞ ምንም የማይቀምሱ፣ስማቸውንም ቤተሰባቸውን የሚረሱ፣ደንታ የሌላቸው፣መፍዘዝና ግራ መጋባት
የሚታይባቸው፣እንዲሁም እሺን የማያውቁ ሁል ግዜ የአፍ መፍቻቸው እንቢ ወይም ኖ(NO)ብቻን
የሚናገሩ፣የማይታዘዙ፣የማይደፈረውን የሚደፍሩና የማይናቀውን የሚንቁ፣በአንጻሩ ደግሞ፤የሚናቀዉና የሚደፈረው
የሚከብዳቸው፤ተቃራኒ ጠባዮች የሚስተዋልባቸው ይሆናሉ ፡፡
ፊልም ማየት የሚወዱ፤ለብቻቸው በህልም መንፈሱ ወሲብን ሲያስተምራቸው የሚያዩ፤ገለልተኛና ብቸኝነት የሚመቻቸው ሆነዉ፤ከነበረው ትውልድ ወጣ በማለት በአካልና በአስተሳሰብ የተለዩ ሆነው ይወለዳሉ ፡፡
ቃየንና የቃየን ቤተሰብ ውጤት
✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿
የቃየን ንፉግና በረከተ-ቢስ፣ፍቅር አልባና ፣የአስተሳሰብ ክፉነት ለራሱና ለትውልዱ ብዙ መዘዞችን አስከትሏል ፡፡
♦በቃየን ሕይወት ውስጥ ትልቁ ችግር የፍቅር መንፈስ ማጣትና አለመገለጥ ነው፡፡ለጠብና ለተንኮል፣ግፍና ግድያ ወዘተ... ለመሳሰሉት የወንጀል ጀማሪዎች መከሰቻ ሆኖአል ፡፡
♦ፍቅር መልክ የሚይዘውና ውበት የሚያገኘው ሁል ግዜ ከእግዚአብሔር ንጹህ አምልኮት ጋር ሲሆን ብቻ ነው፡፡ከዚህ
እውነት ከወጣ ግን ፍቅር ሚዛኑንና አቅጣጫውን በመሳት፤የመዘበራረቅ ዕድሉ እጅግ የሰፋ ነው፡፡በቃየን ሕይወት ውስጥ
የታየው ፤ፍቅር፤ የጦርነት የዘፋኝነትና ከቦታ ቦታ መንከራተት፣ የወንዝ ውሀ መንፈስ የተጀመረበት ፣ የባዕድ
አምልኮትና የኃይል ኑሮ ትውልድ የበቀል ሞት አስተማሪ በመሆን የአሳቹን መንፈስ አገልግለዋል ፡፡
♦በዚህም
፤አስተሳሰብ ፤ገሐዳዊውን ዓለምና የባለ አስተሳሰቡን ሕይወት ፣ኑሮና ትውልድ የሚወስን እንደሚሆን ከቃየን መገንዘብ
እንደሚቻል ግልጽ ነው፡፡ ቃየን በወንድሙ ላይ በጥላቻ በመነሳት የውስጥ አስተሳሰብ ሂደት ያመጣው ውጤት ፤ ወደ ክፉ
አምርቶ ፤ሽፍትነትን ፣ውንብድናን ፣ስደተኛነትን ፣ኮብላይነትና ክዳትን እንዲሁም ፤ከእግዚአብሔር እምነትና አምልኮት
የራቀ ትውልድ ጠባይ እንዲሆን ዓይነተኛ ገጽታ ሆኖ እየኖረ ነው፡፡ ለክፉ ተግባር በመነሳሳት ግፊት ውሰጥ ክፉው
መንፈስ በአዳም ልጅ በቃየን ላይ ዕድል በማግኘቱ ፤ጥፋትን ለመግለጥ ተጨማሪ መነሻ መንገድ እንዲያገኝ ረድቶታል ፡፡
የቃየን ገጸ ባሕርይ ለክፉው ዓለም
✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿
ዛሬ በዓለም ላይ ካለው የንፉግነት የውስጥ አስተሳሰብ በብዛት ተከስቶ የሚታየው በእግዚአብሔር ስም
የሚደረጉ ክንውኖች ናቸው፡፡ እነዚህም በጎነት ማጣትና የእምነት ዋጋን ከነ ጭራሹ በመተው ፤በመርሳትና በመዘንጋት
መካከል በሕልውና ውስጥ የበረከት ጅማሬ በአምላክ እንዳይመጣ ማገጃ እንቅፋት ከመሆኑም በላይ ፤የኑሮ ተስፋና
የትውልድ ሰማያዊ ሥጦታ ላይ ሁለንተናዊ እጦትን እንዳመጣ በቃየን ሕይወት መማር ይቻላል ፡፡
ቃየን ለእግዚአብሄር የአምልኮና የክብር መስዋዕት ለመስጠት ፈቃደኛ ያልሆነ ፤የመጀመሪያው ንፉግ ሰው በመሆን
፤የጉልበቱ ዋጋ በእምነት መስዋዕት በኩል አልተገለጠም ፡፡ስለዚህ ቃየን በየትኛውም ትውልድ ላሉ ንፉግ ሰዎች ምሳሌ
በማድረግ ፤ዲያብሎስ የመቅኖ-ቢስነትን አኗኗር በዓለም ላይ ገልጦበታል፡፡
የበረከትን ጣዕም አለማወቅ
በሰው ልጅ ዘር ውሰጥ አንድ ብሎ የጀመረው በቃየን ሕይወት ውስጥ ነው ፡፡ ቃየንና ዘሩ ዕድሜያቸው ያለቀው በረከትን
ለማግኘት በራሳቸው ዘዴና ጥበብ ሲፈልጉ ፤ በምድር ላይ ኮብላይና ተቅበዝባዥ በመሆን ፤ዕድል አግኝተዋል ፡፡
በእግዚአብሔር ያልተጠበቀ በረከት ፣ፍላጎትና ተግባር ፣ያልተቀደሰ ትውልድ ምልክቱም እነደ ቃየን በመንፈሳዊ ሕይወት መቅበዝበዝ መሆኑን ለዓለም ምልክት የጥፋት አርዓያ ሆኖአል ፡፡
የካደው ትውልድ ቋንቋ
✿✿✿✿✿✿✿✿✿
"አላውቀውም ፤የወንድሜ ጠባቂ እኔ ነኝን" የሚለው የቀደመው ቋንቋ በዚህ ዘመን
ይንጸባረቃል፡፡ ጾም ጸሎት አላውቅም ፤የአባቶቻችንን መንፈሳዊና ሥጋዊ ታሪካቸውን እንዲሁም ተጋድሎአቸውን አላውቅም
፤እኔ የነሱ ጠባቂ ነኝን? የሚለው የቃየን ቃል ፤ዛሬም ይሰራል ፡፡
ይህ የዛር እልህ
፣የደም እርግማን ፣የወንጀል ጩኸት ፤የአሁኑ ዘመናችንን እያሳየና በግልፅ እየመሰከረ ነው፡፡ጻድቃንና ቅዱሳንን
አላውቅም የሚለው የመናፍቁ መንፈስ አንዱና ዋናው የዚህ የካደው ትውልድ ቋንቋና መግለጫ ነው፡፡
የቃየን መሸበር ፤
✿✿✿✿✿✿✿
"ቃየንም እግዚአብሔርን አለው ፦ኃጢአቴ ልሸከማት የማልችላት ታላቅ ናት ፡፡እነሆ ዛሬ ከምድር ፌት
አሳደድኸኝ ፤ከፊትህም እሰወራለሁ ፤በምድር ላይ ኮብላይና ተቅበዝባዥ እሆናለሁ ፤የሚያገኘኝም ሁሉ ይገድለኛል ፤
"አለ፡፡
መላው ክርስቲያኖች ሁላችንም ፤ማስተዋልና መገንዘብ ያለብን ፤የዛሬ አብዛኛው ስራችንና ግብራችን ከሀጢአት ነጻ ስላልሆነ ይህ ድምፅና ኡኡታ ፤የቃየን ብቻ አለመሆኑ ነው፡፡
አሁን አቤል የለም ፤የማይራራውና "አላውቅም ፤የወንድሜ ጠባቂ እኔ ነኝ?"ያለው ቃየን ነው፡፡ ዛሬ
ቃየን በሕይወት ባይኖርም መጥፎ ድርጊቱ እየተወራረሰ አሁን ድረስ በምደባር ላይ ነግሦአል፡፡ዛርን መውረስ ማለት ይህ
ነው፡፡ የቃየን ዘር፤የጦርና የሙዚቃ መሳሪያዎች ጥበብ ከጦርነትና ከወንዝ አምልኮት ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ
የተከሰተበት ፤ደም አፍሣሽ ነገድ ነው፡፡የእርግማኑም ቃል ፤
"ቃየንን ሰባት እጥፍ ይቀበሉታል ላሜሕን ግን ሰባ ሰባት እጥፍ፡፡"ዘፍጥ ፤4÷24 ይህ የጦርነትና የደም ዛር ነው፡፡
"ክፉና አመንዝራ ትውልድ ምልክት ይሻል ፡፡" ማቴ 16÷4
የአካባቢ ሥሞችንና የሰዎችን መጠሪያ፤የወረሱ የዛር የንግስና ሥሞች
❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀
በደጋና በበረሀ የወደቁት የአጋንንትና የሰይጣን የዛር መንፈሶች የሰዎችንና የአካባቢ ስሞችን እየወረሱ፤በሰዉ ዘር ላይ የተሾሙ ናቸው ፡፡
ዛሮች በተለያየ አካበቢዎች የተለያዩ ስያሜዎን የያዙ ይሁኑ እንጂ ፤በያዙት ሰዉ ላይ የሚያሳድሩት ተጽእኖና ጉዳት በአብዛኛው ተመሳሳይ ነው፡፡
በአገራችን ከሚገኙ የዛር የንግሥና ስሞች መካከል ፤ሙጨ ዘሪጋ ፣አዳኝ ወርቁ ፣ሐጎስ ፣ጎለም እሸት
፣ጨንገር ፣ሰይፉ ጨንገር ፤የሚባሉት የዛር መንፈሶች በዋናነት የሚወዱት ግብር ፣እንሾሽላ ፣ወርቅ ሽቶ ፣በተመሳሳይ
ሰከት ቡና ማፍላት ፣ጌጣጌጥ ፣በጣም የደመቀ ቀለም ያለው ልብስ መልበስ ፣ዘፈንና ከበሮ መምታት ነው፡፡
ጠቋር ፣አዳል ሞቲ ፣ወሰን አጋጅ ፣ወሰን ገፊ ፣ወሰን ራሔሎ ፣ሻንቂት ፣ሻንቆ ፣ ሃደ ሐሮ ፣ሃደ
አባይ ፤አባ መጋል ፣ሼህ አንበሶ ፣ነቢ ጅላሌ ፣ብር አለንጋ ፣ገውዘ ላዝም ፣ሻንቆ አባዲና ፣አርዱላ ፣99 መሊካ
፣ሞቲ አረቢያ ፣ግራኝ አባ ጉግሳ ፣አላቲ ፣ሪሣ ፣ኦፋ አቡኮ ፣ ኦፋ ጨፌ ፣ ኦፋ ለገሰ ፣ ኦፋ ደመና ፣የታዬ
ከራማ ፣የአሩሲዋ እመቤት ፣ቡሎ ገርቢ ሣማ ቀልቢ ፣ አርሜት ፣ድማሜት ፣ሙሄት ፣አብድር ቃዲር ፣ዋቅ ፣ቦዥና ጨሌ
፣የወሎ ክብሪት ፣ቤሩድ ፣ሼህ ወልይ ፣የጠረፏ ንግስት ፣አዬ ሞሚና ፣አቴቴ ዱላ ፣አውሊያ ከራማ ፣አውሊያ ሼክ ሁሴን
፣ጅላሌ አብዱል ቃድር ፣ ተኮላሽ እያሱ ፣በረኸኛ አጋንንቶች ማለትም ፤ወሰን ገፊ ፣ አዳኝ ሱማሌ ፤ ቆሌ አዳኝ
የልክፍት ዛር ፣ቦረንትቻ ፣አሞር ፣ ውቃቢ ፣ወዘተ.......የንግሥና ስሞች ናቸዉ፡፡
የመናፍስቱ ሥያሜ ፣ ሥምሪትና ጥቃት ፤በዋነኛነት ሥያሜያቸውን ባገኙበት አካባቢ አይሎ የሚገኝ ቢሆንም ፤በተለያየ
ምክንያቶች ሰዎች ከቦታ ወደ ቦታ በመዘዋወራቸው የተነሣ ፤በሰሜን ያለው መንፈስ ፤ በደቡብ ፤በምዕራብ ያለው ፤
በሰሜን ፣ በመሐል ያለው በምስራቅ ወዘተ...ሊኖር ይችላል ፡፡
የዛር መንፈሶች ለሰዎች የሚያወርሱዋቸው አጠጠቀላይ ጠባያት
✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿
በየሰአቱ የሚቀያየር ጠባይና የተደበቀ ስውር ሰው መሆን ፤ውስጥ ውስጡን መሸመቅ ፤እልኸኝነት ፣ወይም ከሚገባው
በላይ ግልጽ መሆን ፤ብዙውን ጊዜ በንዴት በብስጭት ጊዜውን ማሳለፍ ፣በር ዘግቶ በጨለማ መቀመጥ፣ ለብቻ ማልቀስ
፣ወሬ ማናፈስ ፣ ነገር ከያዘ አለመልቀቅ ፣ የአመል ግትርነት ፣የእግዚአብሔር ሰዉ መጥላት ፣ ማሳደድ ፣ ደምን
ማፍሰስ ፣ ደም ሲፈስ ማየት ፣ ተበቃይ ፣ ቂመኛ ፣ አመፀኝነት ፣ መጋደል ፣ ሌላውን በክፉ አይን ማየት ፣
በተለይም በሌላው ኑሮና አምልኮት ፣ በእግዚአብሔር ጸጋና ሞገስ መቅናት ፣ በሌላው እድገት ፊትን ማጥቆር ፣ ስም
ማጥፋት ፣ መተቸት ፣መቃወም ፣ ማፌዝ ፣ መሳደብ ፣ መራገም ፣ሐሜት ፣አሽሙር ፣መራራ ቃል መናገርና እንደሱስ
መሆን ፣በገንዘብ ፣በሥልጣንና በጉልበት መሳሪያነት መተናኮል ፣ለሌላው ውድቀትና ሞት መመኘት ፣ለማጥፋትና ለማውደም
መቸኮል ፣የሌሎችን ኪሳራና ውድቀት በማየት መደሰት ፣ሃይማኖት መለዋወጥና የእምነት አለመኖር ፤
ወዘተ...የመሳሰሉት ሁሉ ፤ዛር ያለባቸው ሰዎች የተለመዱ ጠባያት ናቸዉ ፡፡
የዛር መንፈሶች በአብዛኛው
ተመሳሳይ ጉዳት የሚያደርሱ ቢሆንም ፤በዋነኛነት ግን ፤ ከማሕፀን ጀምሮ ለልክፍት የሚሆኑ ፣ የሰው ልጆችን ፤
ከርታታ ፣ባካኝ ፣ሰርቶ መና የሚያደርጉና የመከራ ኑሮን የሚያወርሱ ናቸው፡፡
የዛርና የውቃቢ የውርስ
መንፈሶች ፤ሌሎች ወደ ሰዎች የሚላኩ የዲያብሎስ መንፈሶችን ፤በመሳብና በፍጥነት ተቀብሎ ቦታ ሰጥቶ በማስተናገድ ፤
በውስጣችን ሰይጣንን አሰባስቦ በማደራጀት ሰፊ ጠባያቸውም ፤ይታወቃሉ፡፡ ከእነዚህ ውስጥ አንዱን አዳኝ ወርቁ
የተባለውን መንፈስ ፤ በምሣሌነት እንመልከት ፡፡
አዳኝ ወርቁ
✿✿✿✿✿✿
መልካም መዓዛ ያለው ሽቶና እጣን ፤ ከጌጣጌጥ ወርቅ በብዛት የሚወድ ሲሆን ፤ መልክና ውበት ያላትን ሴት
ከሌላ ወንድ አስቀድሞ ለራሱ እንደ ሚስት ስለሚይዝ ፤ የዚህ መንፈስ ሰለባ የሆኑ ብዙ ሴቶች ባል አያገቡም ፤
አይፈልጉም ፡፡
ስለዚህ የባል ፍቅርን ሳያዩ ፣ ልጅም ሳያምራቸው ፤ የቤተሰብ ኃላፊነት ሳይሰማቸው
ቀርቶ ፤ ዘመናቸውን ከመንፈሱ ጋር ይጨርሳሉ ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ፤ ልጅ የመውለጃ ዕድሜያቸው ካለፈ በኋላ
በተቃራኒው ፤ መንፈሱ በውስጣቸው ልጅ መውለድ እንዲያምራቸውና ፤ እንዲጓጉ በማድረግ ፤ የቁጭት ስሜት ያሳድርባቸዋል
፡፡ በዚህም የተነሣ ፤ ውስጥ ውስጡን እየተብከነከኑና ፤ በመካንነታቸው እያዘኑ ፤ ፈጣሪ አምላካቸውን እያማረሩ
እንዲኖሩ ያደርጋቸዋል ፡፡ የክፉው መንፈስ ዋንኛ አላማ ፤ ሰዎች በሕይወታቸው እግዚአብሔርን እንዲያማርሩ ስለሆነ ፤
በዚህ በኩል የሚያደርገው እንረቅስቃሴ የተቃና ይሆንለታል ፡፡
የአዳኝ ወርቁ ዛር ጠባይ ፤ ሴት
ልጁን ያኳኩላል፣ ወርቅ በጸጉርዋ ፣ በአንገትዋና በጆሮዋ ፣በእግርዋና በእጅዋ ላይ ያበዛል ፡፡ ራሱም ልዩ ውበት
የመስጠት ኃይል ያለው ሲሆን ፤በገሃዱ ዓለም ያለ ሌላ ወንድ ሲጠጋት ወይም ሲያያት ይማረክባታል ፤ የሩካቤ ፍላጎትም
እንዲሰማው ያደርጋል ፡፡ ይሁን እንጂ ፤ በአብዛኛው ሴቲቱ ከወንድ ጋር ለመሆን አትፈልግም ፡፡
መንፈሱ ከብዙ ወንዶች ጋር የሚያገናኛት ቢሆንም ፤ ከሁሉም ጋር አያግባባትም ፡፡ ምክንያቱም ፤ ደም ስለሚፈልግ ፤ ከሁለቱ አንዱን ወይም ሁለቱም በማጋጨት ብሎም ለማጋደል ስለሚፈልግ ነው፡፡
ባለጸጋዎችን ፣ ሾፌሮችን እና ነጋዴዎችን ወዘተ...በመጥለፍ ገንዘባቸውን ይሰልባቸዋል ፡፡ልባቸው ላይ
መልኳንና ውበቷን ያስቀምጣል ፡፡ እስኪያገኟትም ድረሰ ፣እንቅልፍ ይከለክላቸዋል ፤ ይረብሻቸዋል ፡፡ አንዳንዶቹ
እስኪያብዱ ድረስ ይፈትናቸዋል፡፡
ይህ እንግዲህ መንፈሱ ሴቲቱን በሃብት ለማበልፀግ የሚሄድበት መንገድና ለኃጢአት አሰራሩ የሚጠቀምበት ዘዴ ነው፡፡
እንዲህ ዓይነትዋ ሴት አንዱን ቀን ፤ ለተማረከባት ፣ ሀብቱን ላፈሰሰባት ወንድ ስትሰጥ ፤ ሁለት ወይም
ሶስት ቀን ደግሞ የመንፈሱ ተራ ይሆናል ፡፡ ይህ ፤ ከመንፈሱ ጋር የምትገናኝበት ጊዜ መሆኑ ነው ፡፡
በዚህ ወቅት ዕጣን ፣ ሉባንጃ ፣ሽቶ የመንፈሱ አልባሳት ሁሉ ሳይቀር ይዘጋጃል ፡፡ የሚጠይቃቸው የግብር
ዓይነቶች ሁሉ ከተሟላ በኋላ ፤ በነጋታው ገንዘብ የሚያፈስላትን ሰው ያዘጋጅላታል ፡፡ የሰውየውን አቋም ፣
ተክለ-ሰውነት ፤ መልክና ውበቱን ፤ በሕልሟሙዋ አስቀድሞ ሊጠቁማትም ይችላል ፡፡
ሌላው ጠባዩ
፤ዓይን ለዓይን በመተያየት ፣ በድምጽ (በስልክ ውስጥ የመሚደረግ ንግግርን ይጨምራል ) ፣ሰላምታ በመጨባበጥ ፤
በልብስ በመነካካት ወዘተ...ሁሉ ሳይቀር ፤ የፍትዎት ስሜትን ያነሣሣል፡፡
በአብዛኛው ከተለመደው የተፈጥሮ ባሕርይ ወጣ ያለ የወሲብ ስሜትን ሚፈጥረው ክፉ መንፈስ መሆኑን ብዙዎች አይገነዘቡትም፡፡
ለምሳሌ ፤ አስገድዶ የመድፈር ጠባይ ፤ የዚህ የዝሙት መንፈስ አንዱ አካልና መገለጫ ነው፡፡
ለመለያየት የሚጠቀምበት ዘዴ
✿✿✿✿❀❀❀❀✿✿✿✿❀❀❀❀
ከጊዜ በኋላ ሴቲቷን የተጠጋው ፤ ሰው የማያቋርጥ ከባድ ራስምታት ፤ ሆድ መንፋት ፣መደበት ፣ ማስጨነቅ ፣በመሳሰሉት አስቸጋሪ ጠባያት፤ አማሮ ሊያባርረው ይችላል፡፡
የተለያየ አካላዊ አደጋም ያበዛበታል ፡፡ ጠቋርን የመሰለ ዛር ከሆነ የግሞ ፤ ከቅናቱ የተነሳ ፤ሕይወቱን
ሊያጠፋው ሁሉ ይችላል ፡፡ ሌላው በመንፈሱ የመገለጫ ጊዜ ፤ ለእርስዋ በመኝታ ላይ ልታየውና ልትዳስሰው እንዲሁም
፤ ሌሊት ክንድዋ ልታገኘው ትችላለች፡፡
በዚህ መንገድ ብዙ ሴቶች የመንፈሱን ሩካቤ ያፈቅራሉ ፡፡ከባል
ጋር ግንኙነት ባያደርጉ ፈቃዳቸው ነው፡፡በተለያየ ምክንያት ግንኙነት ቢፈጽሙ እንኳን እርካታ አይኖራቸውም ፡፡በዚህ
ግንኙነት የሚፈጠሩ ልጆች ጀግም ፤ በተፈጥሮና በአስተሳሰብ የተጎዱ ሆነው ይወለዳሉ ፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ፤የቡዳ
መንፈስ አስተላላፊዎች በመሆን ፤የሌሎችን ሕይወት ይጎዳሉ ፡፡
ይሁን እንጂ አንዳንዶቹ ፤
ከተኙበት ሲነቁ ግን ፤ አቅፈዉ የተኙትን መንፈስ ገጽታ ፤ በዓይነ -ሕሊናቸው ሲያስታውሱት ፤ከባድ መንፈሳዊ
ቀውስ ውስጥ በመግባት ፤ ከፍተኛ የሆነ ፍርሀትና ጭንቀት እንዲሁም ሽብር ውስጥ ይገባሉ ፤ ይወድቃሉ ፡፡
በተለይ ይህንን ሁኔታና ሥቃያቸውን ለሌላው ሰው ለመንገር ሥለሚያሳፍራቸው ፤ ውስጣቸው እንደቆሰለ ይኖራሉ
፡፡"ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ፤ ነፍሱንም ቢያጎድል ምን ይጠቅመዋል ? ወይስ ሰው ስለነፍሱ ቤዛ ምን ይሰጣል ?"
ማቴ. 16÷26
ሾተላይ የዛር የመተናኮል የውርጃ መንፈስ ፤
✿✿✿❀❀❀✿✿✿❀❀❀✿✿✿❀❀
ብዙ ጊዜ እንዲህ አይነት ዛር ሾተላይ በመሆን ፤ እርግዝና ላይ አደጋ የመፍጠር ችሎታ የሚኖረው ሲሆን ፤ተተኪ
ትውልድን በማጨንገፍ የሚረካ ፤ የሰው ደም በማፍሰስየሚደሰትና የቤተሰብን ሐዘንና ለቅሶ ፤በልጅ ማጣት መቸገራቸውን
እያየ እንደ ድል የሚቆጥር ፤ ስውር እልኸኞ የዛር መንፈስ ነው፡፡
የዛር መንፈስ ከማህጸን ጀምሮ ያለው፤ ሌላ ጥቃት ፤
✿✿✿❀❀❀✿✿✿❀❀❀✿✿✿❀❀❀✿✿
ከማሕጸን የሚወረሱ የዛር መንፈሶች ፤ የእናትና የአባት የመንፈሰ ጉዳቶች በዋናነት ያስከትላሉ ፡፡
ሀ. መካን(መኻን) ማድረግ
ለ. በሚወለዱት ሕጻናት ላይ ፤ የአእምሮም ፣የጤና፣እንከንና የአካል ጉዳት መፍጠር ለምሳሌ ፤፦የዛር መንፈስ
አንዳንድ ሕጻናትን የአካል ጉዳተኛ ፣ የአእምሮም ዘገምተኛ ወዘተ...ከማድረጉ በተቃራኒው ፤ ያለዕድሜ ደረጃቸው
እንዲያስቡና ሥራቸው ሁሉ ፤ እንደ ትልቅ ሰው እንዲሆን ያደርጋል፡፡
ብዙ ጊዜ እንደነዚህ አይነት ሕፃናት ፤ አስተሳሰባቸው ፤ እድሜያቸው ከሚሸከመው በላይ ስለሚሆን ፤ ረዥም ዓመት በሕይወት የመቆየት ዕድላቸው የመነመነ ነው፡፡
ሐ. የሚወለዱትን ልጆች ባሕርይ ማበላሸትና መጥፎ ጠባይን ማውረስ ፤
መ. ያለዕድሜ ፤ተፈጥሯዊዉን የወር አበባ ዑደትን ማዛባት ፤ ማለትም✿ ፤ ሴት ሕፃናት ገና ለአቅመ ሔዋን
ሳይደርሱና ጡት ሳያወጡ ፤ በስምንትና በዘጠኝ ዓመት ዕድሜያቸው በሚያስደነግጥ ሁኔታ የወር አበባ እንዲያዩ ያደርጋል
፤
✿ ሴት እህቶች ደግሞ ፤ ባልተለመደና በማይጠበቅ ሁኔታ ፤በአብዛኛው በሰላሣና በሰላሣ አምስት ዓመት ፤
እንዲሁም አስከ አርባ ዓመት ዕድሜ ክልል ላይ ሲደርሱ ፤ የወር አበባ ማየት እንዲያቆሙና ያለጊዜያቸው እንዲያርጡ
ያደርጋል፡፡
✿ አንዳንዶቹም በዚሁ መንፈስ ጥቃት ተነሳ ፤ ከሃያ ዓመት ዕድሜያቸው ጀምሮ ፤ ለአንድ ወይም
ለሁለት ዓመት ፤ወይም ከዚያም በላይ ለሚሆን ጊዜ ፤ ወር አበባቸውን ሊያጠፋው ወየይም ሳያዩ እንዲቆዩ ሊያደርግም
ይችላል፡፡ ከዚህ በተቃራኒ በአንድ ወር ውስጥ በተደጋጋሚ የወር አበባ እንዲፈሳቸው ያደርጋል ፡፡
በሕክምናው በኩል ሐኪሞች እንደሚገልፁት " እንደዚህ ዓይነት ክስተቶች አዲስ አይደሉም ፡፡በተለያየ ምክንያት
አልፎ አልፎ ሊፈጠሩ ይችላሉ ፡፡ ሆኖም ፤ በብዙ ሴቶች ላይ የመታየቱ ጉዳይ ግን ፤ ያልተለመደና ራሱን የቻለ ጥናት
የሚያስፈልገው ነው፡፡" ይላሉ ፡፡
ነገር ግን ፤ በርካታ ሰዎች ከላይ የተገለፁት ችግሮችና
እንከኖች በአንድ በኩል በዲያብሎስ ምሪት በክፉ መንፈሶ ተፅዕኖም ሊመጣ እንደሚችል ፤ ገና መረጃው የላቸውም
፡፡በተደጋጋሚ እንደተገለጠው ፤ ዲያብሎስ በዛር መንፈሶች በኩል ከሰዎች ጋር አብሮ እየተወለደና እየተወራረሰ ፤ ዘሬ
አድርጌያቸዋለሁ እያለና መንፈሱን ከማሕፀን ጀምሮ እያስቀመጠ ፣ ከፍ ብሎ የተጠቀሱትን ጉዳቶች የሚያደርስ ቢሆንም ፤
በእግዚአብሔር መንፈስ የሚሸነፍና ወደ ሲኦል ወርዶ የሚታሰር ጠላት መሆኑን ለአፍታም ያህል ፤ መጠራጠር የለብንም
፡፡
ለምሳሌ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በማርቆስ ወንጌል 9÷29 "ይህ ወገን በጸሎትና በጦም ካልሆነ
በምንም ሊወጣ አይችልም " ይላል ፡፡ ይህ ማለት ወገን ሆኖ አብሮት ስለተወለደ በአካላዊ ተፈጥሮው ላይ ደንቆሮና
ዲዳ በማድረግግ የእናቱና የአባቱ ሕልውና እንደጎዳ መመልከት ይቻላል ፡፡
☞ሴት ዛር በወንድ ላይ ስትኖር ፤ የምታመጣው ጉዳት
❀✿❀✿❀✿❀✿❀✿❀✿❀✿❀✿❀✿❀✿❀
ሴት ዛር ወንድን በምትይዝበትና አብራ ተወልዳ በምታድግበት ወቅት ፤ ሕይወቱን ትለማመድና ልክ እንደሴት ልጅ በመቀመጫው በኩል በየወሩ የወር አበባ እንዲመጣበት ታደርጋለች ፡፡
ይህ ፈፅሞ ያልለተለመደ ሁኔታ በሕክምናው በኩል፤ የአንጀት ጉዳት ወይም የኪንታሮት ችግር መስሎ
እንዲታይ፤ መንፈሱ ማሳሳቻውን ያቀርባል ፡፡ምንም ይባል ምን፤የሚገርመው ግን፤በሰውየው ላይ የወር አበባ ዑደቱ ልክ
እንደሴቶች ቀን እየጠበቀ ለዓመታት ያህል ያለማቋረጥ የመታየቱ ጉዳይ ነው፡፡
ይህ የተዛባ ተፈጥሮ ፤የዛር መንፈስን የሚያመልኩና የሚገበሩ ሰዎች የበዙበት አካባቢ በሚገኙ ቤተሰቦችና ማህበረሰብ ውስጥ በስፋት የሚገጥም ክስተት ነው፡፡
☞ዝብረቃ
✿❀✿❀✿❀
በማይጠበቅ ሁኔታ ድንገት አስደንጋጭ የሆነ ቃል፤በንግግር መሐል ላይ ዝብርቅ ማድረግ የተለመደ የዘመናችን ስልጡን
ሕብረተሰብ ዋና ችግር ነው፡፡ይህ፤ የዛር መንፈስ ሌላው ጥቃት ነው፡፡ዝብረቃ በሁለት መልኩ ይከሰታል፡፡
ሀ.☞የተሰወረ ዝብረቃ ፤
✿❀✿❀✿❀✿❀✿❀
የመንፈሱ ሚስጥራዊ አሰራር በሥራ፣ በትምህርት ፣በንግድ ሥራና ሙያ በዕቅድና በፖሊሲ ንድፈ ሐሳብ እንዲሁም
በጸሎት ጊዜ ሁሉ ጣልቃ በመግባት፤ አደገኛ ነገርን የሚያመጣ የመሪዎችና የኃላፊዎች የዝብረቃት ዕዛዝን
ጨምሮ የዓለማችን ትልቁ በሕይወታችን ውስጥ የሚገኙ የመንፈስ ውጥረት ነው፡፡
ለምሳሌ ዘብረቅ ያለ ዳኛም ይሁን መሪ ቶሎ ከእስር ቤት ሃምሳ ሰዎች ይረሸኑ ብሎ ከተናገረ ፤ ሰውየው ሳያውቀው በዝብረቃ መንፈስ ሃምሳ ሰዎች ተገደሉ ማለት ነው፡፡
በሕክምናውም በመድኃኒት ምርምሩም በተለያየ ኃላፊነትና የሥልጣንና የማዕነግ እርከን ያሉ ሰዎች ላይ የጦር መሪዎችንም ጨምሮ እስካልተወሰነ ሰዓት ድረስ ፤ የዝብረቃ መንፈስ ያጠቃቸዋል ፡፡
ለ. ☞ግልጽ ዝብረቃ ፤
✿❀✿❀✿❀✿❀✿❀
ከፍሬ ነገሩ ጋር የማይገናኝና የማይያያዝ ሐሳብማስገባት ፣በጨዋታ መካከል ከመልካም ሥነ-ምግባር
የወጣና የወረደ ቋንቋ መጠቀም ፣ መሳደብ ፣ ማዋረድ ፣ወይም ማልቀስ ፤በተቃራኒው ፤ ከልክ በላይ መሳቅ ፤በሙሉ
ሰውነት ድንገት ብድግ ብሎ መዝለልና ወዲያውኑ የመቃተት ድምፅ ማሰማት ፣በእጅና በከንፈር ለብቻ ማውራት ፣ቁጭ ብሎ
መዋተት ፣ሰዎችን ያለስማቸው አጠገባቸው ባለ ሰው ስም መጥራት ፣ ልዩ ልዩ ቁሳቁሶችን አለስማቸው መጥራት ፤ለምሳሌ ፤
እንጀራ ለማለት ፤በቆሎ ፣ውኃ ለማለት ፤ እንጨቱን አምጣና እንጠጣ ወዘተ.....ሁሉ ማለት ፤ የዚዙ ክፉ መንፈስ
የሚታይና የሚሰማ የዝብረቃ አካል ነው፡፡
ያለ ዕድሜ መጃጀት
✿❀✿❀✿❀✿❀✿❀✿
የዛር መንፈስ ከሚያስትለው ጉዳቶች መካከል ፤ ያለ ዕድሜ መጃጀት ፣ መርሳትና ሠዘንጋት አንዱ ነው፡፡ ይህ
፤ በተለይ በአሁኑ ዘሠን ትልቅ ችግር ሲሆን ፤ ጥቃቱን በብዛት የሚያሳርፍባቸው ፤ ሳይንቲስቶች ፣ፖለቲከኞች ፣
ምሁራኖችና በኃላፊነትና ስልጣንና ማዕረግ የሚገኙ ሰዎች ፣ ሴቶችን ጭምር መርሳትና መዘንጋት ከክፉው መንፈስ አንዱ
መሰረታዊ ችግር ነው፡፡
በሕክምናው (ዲያሜንሺያ) ብለው ስም ስለሰጡት ፤ በሳይንሳዊ ስያሜው መንፈስነቱን መደበቂያ ምሽግ አድርጎታል ፡፡
ለጸሎት ፣ ለአምልኮትና ለእግዚአብሄር ቃል ጊዜና ቦታ የሌላቸው ሁሉ ፤ በዚህ ክፉ መንፈስ ይጠቃሉ ፡፡
☞መሰረታዊ ምልክቶቹ ፤
❀✿❀✿❀✿❀✿❀✿
☞ያወጡትን ዕቅድና ፕሮግራም መርሳት፣ወይም ሐተው፤
☞ከሕሊናቸው ዕውቀታቸውና ልምዳቸው መጥፋት ወይም መሰወር ፤
☞ገንዘባቸውንና ንብረታቸውን አለመቀቆጣጠር ፤
☞ከቤታቸው ወጥተው ፤ የሚኖሩት መንደር ፣ መንገድና መኖሪያ ቤታቸው ጠፍቶአቸው ሌላውን ሰው እስከ መጠየቅ መድረስ፤
☞ምሳ ወይም እራት በልተው ፤ አልበላሁም ብለው መጣላት፣ ማኩረፍ ፣ መናደድና መጮኽ ፤
☞ሚስታቸውንና ልጆቻቸውን መርሳት ፤ አለ ዕድሜ በዚህ መንፈስ የመጠቃት ልዩ ምልክቶች ናቸው፡፡
☞አዋቂው ሰው እንደ ሕጻን መሆን
✿❀✿❀✿❀✿❀✿❀✿❀✿❀
ከዚህ በተቃራኒው ፤ የዛር መንፈስ በዕድሜ ከፍ ያሉና የገፉ ሰዎችን ፤ እንደ ሕጻን እንዲያስቡና እንዲሰሩ
በማድረግ ፤ መካሪና አስታራቂ በመሆኛ ዕድሜያቸው ፣ እንዲሁም ጧሪና ቀባሪ በሚያስፈልጋቸው ሰዓት ፤ እንደ ልጅ
አድርጎ ቅሌትና ውርደት ውስጥ ይከታቸዋል ፡፡
☞ሾፌሮችንና ተሳፋሪዎችን በመንገዳቸው ላይ የሚያጠቁ ክፉ መንፈሶች
✿❀✿❀✿❀✿❀✿❀✿❀✿❀✿❀✿❀✿❀✿❀✿ይቀጥላል .
No comments:
Post a Comment