Tuesday, 22 March 2016

ቅድስት

ቅድስትአትምኢሜይል
ዲያቆን መስፍን ኃይሌ
መጋቢት 4 ቀን 2008 ዓ.ም

የቤተክርስትያናችንን መዝሙር ንባቡን ከዜማው አስማምቶ አጠናክሮ ያስተላለፈልንኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ በጾመ ድጓው በዓ ጾም ለሚገኙትን እሑዶች ሁሉ የተለየመዝሙር ስለሠራላቸው እያንዳንዱ እሑድ በመዝሙሩ ስም ይጠራል  በዚህም መሰረት የዚህታላቅ ጾም ሁለተኛው እሑድ ቅድስት ተብሎ ተሰይሟል። ቅድስት የሚለው ቃል ግሱ"ቀደሰ"ሲሆን ለየ አከበረ መረጠ የሚል ትርጉም ይይዛል። ቅድስት ማለት የተየች የተመረጠች የከበረችማለት ነው። ቅዱስ የሚለው ቃል እንደ የአገባቡ ለፈጣሪም ለፍጡርም ያገለግላል። ለፈጣሪሲነገር እንደ ፈጣሪነቱ ትርጉሙ ይሰፋል ይጠልቃል ለፍጡር ሲነገር ደግሞ እንደ ፍጡርነቱ እናእንደ ቅድስናው ደረጃ ትርጉሙ ሊወሰን ይችላል። እግዚአብሔርን ቅዱስ ስንል የባህሪ የሆነ፣ኃጢአት የማይስማማው ፣ለቅድስናው ተወዳዳሪ ካካሪ የሌለው፣ ወደር የማይወጣለት፣ዘለዓለማዊ የሆነ ማለታችን ሲሆን ፍጡራንን ግን ቅዱሳን ስንል ቅድስናቸው የጸጋ የሆነ፤ከእግዚአብሔር ያገኙት ፤እንደነጭ ልብስ ጽድቁም ኃጢአቱም እንደ ዝንባሌአቸውየሚስማማቸው፤ ለቅድስናቸው ማዕረግ ደረጃ የሚወጣለት እንደ ገድል ትሩፋታቸው መጠንሊጨምርም ሊጎድልም የሚችል ማለታችን ነው። ከፍጡራን መካከል ለእግዚአብሔር የተለዩ ሁሉበጸጋ የቅድስናው ተሳታፊ ሊሆኑ ይችላሉ። መላእክት፣ ሰዎች፣ መካናት፣ ዕለታት ፣አልባሳት፣ንዋያት ሁሉ ለእግዚአብሔር እስከ ተለዩ ድረስ ከቅድስናው በረከት ይሳተፋሉ እንደ የደረጃቸውቅዱሳን ተብለው ይጠራሉ።
በዚህ ዕለት ስለ ቅድስና እንዲሁም ዘወትር በዕለተ ሰንበት ከሌሎች ቀናት በተለየ ሁኔታ ለጽድቅስራ እንድንበረታ፣ ለቅድስና እራሳችንን እንድንለይ ስለ ዕለተ ሰንበት ቅድስና ይሰበካል ይነገራልየሚዘመረውም መዝሙር " ግነዩ ለእግዚአብሔር ወጸውዑ ስሞ ወንግርዎሙ ለአሕዛብ ምግባሮሀቡ ስብሐተ ለስሙ አክብሩ ሰንበተ ተገበሩ ጽድቀ ዝግቡ ለክሙ መዝገበ ዘበሰማያት  ፃፄኢያማስኖ ወኢይረክቦ ሰራቂ ድልዋኒክሙ ንበሩ ዘበላዕሉ ጸልዩ ኀበ ሀሎ ክርስቶስትርጉም፦"ለእግዚአብሔር ተገዙ ስሙንም ጥሩ ሥራውንም ለአሕዛብ ንገሯቸው ለስሙም ምስጋናንአቅርቡ ሰንበትን አክብሩ እውነትንም አድርጉ ብል የማያበላሸው ሌባም የማያገኘው በሰማያት ያለመዝገብን ለእናንተ ሰብስቡ፤ ተዘጋጅታችኹም ተቀመጡ ክርስቶስ ወዳለበት ወደላይ አስቡ፡፡"
በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝቶ ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ያሬድ እንደ ዘመረልን በተለይ ሰንበት ነገረእግዚአብሔር በተለየ ሁኔታ የሚዘከርባት፤ ኅሊናችን ከምድራዊው ሃሳብ ወጥቶ ወደ ሰማይያዊውየሚነጠቅባት፤ ለቅድስና የተለየች ቅድስት ዕለት መሆኗን ይጠቁማል። በቅዱስ መጽሐፍም"የሰንበትን ቀን ትቀድሰው ዘንድ አስብ" ዘፀ. 208 ተብሏል የሰንበትን ቀን አስቀድሞ የቀደሰየባረከ እራሱ እግዚአብሔር ነውእግዚአብሔርም ሰባተኛውን ቀን ባረከውቀደሰውምእግዚአብሔር ሊያደርገው ከፈጠረው ሥራ ሁሉ በእርሱ ዐርፎአልና"ዘፍ.2፥3 እንግዲህ"የሰንበትን ቀን ትቀድሰው ዘንድ አስብ " የተባለው እግዚአብሔር አስቀድሞ የባረከውንየቀደሰውን እኛ ድጋሚ የምንቀድስ የምንባርክ ሆነን ሳይሆን በዕለተ ሰንበት እራሳችንን በተለየሁኔታ ለቅዱስ ተግባር እንድንለይ ለሥጋችን ከምንፈጽማቸው ተግባራት ይልቅ ለተግባረ ነፍስእንድናደላ ያስረዳናል። ምንም እንኳን ለስጋችን ስንባክን ጊዜ ቢያጥረን በዕለተ ሰንበት ግን ቅዳሴከማስቀድስ ቅዱስ ቃሉን ከመስማት ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ከመቀበል እንዳናስታጉልበስር ቤተክርስትያን ታዘናል።
ሊቃውንቱ በፍትሐ ነገሥት «ተጋብኡ ኩሎ ዕለት ኀበ ቤተ ክርስቲያን ወፈድፋደሰ በዕለተ ሰንበትወበበዓላት ወበዕለተ ትንሣኤ ዘውእቱ ዕለተ እሑድ፡፡" ትርጉም፦ " ሁልጊዜ በቤተ ክርስቲያንተሰብሰቡ፤ ይልቁንም በዕለተ እሑድ፣ በዕለተ ቀዳሚት፣ በጌታ በዓላት ወደ ቤተ ክርስቲያንተሰብሰቡ፡፡" /ፍትሐ ነገሥት ገጽ 254/ ብለው ለመንፈሳዊ ሕይወታችን ከሌሎች ቀናት በተለየሁኔታ ትኩረት የምንሰጥበት የምንቀደስበት ዕለት ቅድስት ሰንበት እንደሆነች ተናግረዋል ሐዋርያዊው ቅዱስ አትናቴዎስም በቅዳሴው ላይ ሰንበት የተቀደስች እና ሕይወታችንእንዲቀደስባት የተለየች ቀን መሆኗን ሲያስረዳ እንዲህ ይላል "ወንበል ዛቲ ዕለት እንተ ገብረእግዚአብሔር ንትሣሕ ወንትሐሰይ ባቲ" ትርጉም "ይህች ዕለት እግዚአብሔር የሠራት ያከበራትዕለት ናትና በእርሷ ፈጽሞ ደስ ይበለን" ሰንበት ለክርስትያኖች ለመንፈሳዊ ደስታ የተለየች ቀን ናት የመንፈሳዊ ደስታ ምንጩ በነፍስ የሚገኝ መንፈሳዊ በረከት ነው  ሰው የኃጢአትን ሸክምበንስሃ ሲያራግፍ፤ ነፍሱ በጸጋ እግዚአብሔር ስትቃኝ የሚሰማውን ደስታ በሌላ በምንም መንገድሊያገኘው አይችልም። ቅዱስ አትናቴዎ ሐዋርያዊ ሰንበት ቅድስትና ለቅድስና የተለየች ቀንመሆኗን ያስተማረን አስቀድሞ በነብያት ትንቢት ያናግር የነበረ መንፈስ ቅዱስ አነሳስቶት ነው 
ስለ ሰንበት መለየትና መቀደስ እንዲሁም የመንፈሳዊ ሐሴት ቀን ለመሆኗ  ቅዱስ ዳዊትመዝሙሩ እንዲህ ብሎ ነበር "እግዚአብሔር የሠራት ቀን ይህች ናት፤ ሐሤትን እናድርግ፥በእርስዋም ደስ ይበለን።" መዝ. 11724 ቅዱስ ዮሐንስም ራእዩ ሰንበት የጌታ ቀን ስለመሆኗእንዲህ ይላል "በጌታ ቀን በመንፈስ ነበርሁ" ራእ. 110 ሰንበት የእኛ ቀን ሳትሆን ለጌታችንየምንሰራባት የምንለይባት ፣የምንቀደስባት፣ ነገረ እግዚአብሔርን የምንዘከርባት የጌታ ቀን ናት ለቅድስና የተለየች ቅድስት ቀን ናት  በተለይ የክርስቲያን ሰንበት እሑድ " በዓላት"ትባላለች  ታላቅ እና መጀመርያ ማለት ነው የመዳናችን መሰረት የተወጠነባት የጌታ የጽንሰቱቀን ዕለተ ሰንበት ናት ፤የመዳናችን ማረጋገጫ ፣የእምነታችን መሰረት ፣የበዓላት ሁሉ ዓቢይትንሳኤው የተፈጸመው በዕለተ ሰንበት ነው። እንግዲህ በዚች ቅድስት ዕለት፥-ለቅድስና በተለየችዕለትስ ሥጋውንም ነፍሱንም በሚያርያረክስ ተግባር የተሰማራስ ለነፍሱ ምን ዋስትና ይኖረዋል?
ቅድስት በተባለች በሰንበት እሑድ ማንም በምንም ምክንያት ወደ ቤተ እግዚአብሔር ከመሄድእንዳያስታጉል በስርአተ ቤተክርስትያን ተቀምጦልናል። ሌላው ቀርቶ በዕዳ በብድር በቀረጥበግብር በአስራት በበኩራት ይሉንኝታ ፈርቶ ማንም ቅድስት በምትባል በእሑድ ሰንበት ቅዳሴእንዳያስታጉል ማንም ማንንም በዚህች ቅድስት ዕለት ምንም አይነት እዳ እንዳይጠይቅ ታዟል።"ወኢይኅሥሥ መኑሂ በይእቲ ዕለት ንዋዮ እምካልኡ ወኢይጽሐቅ አሐዱሂ እምእመናን በእንተኃሥሠ ዕዳ  አው ተጻልኦ አው በዘይመስሎ ለዝንቱ። ወይሑሩ ቦቱ ኩሉሙ ሰብእ  ቤተክርስቲያን ወይምጽኡ ኲሉ ለለ   እምእመናን ኅቤሃ በንጽሕ ወበትህትና ዘእንበለ ፍርሃት እምነመኮንን ወእም በዓለ ዕዳ አው እምፈታሒ አው ዘይመስሎ። ወእመሰ ተሀበለ ፩ሂ ክርስቲያንምክዕቢተ ይፍዲ " ትርጉም፦ "ከምእመናን ወገን አንድስ እንኳ በእሑድ ቀን ለገንዘብ መትጋት፤ገንዘቤን አምጣ ብሎ መጣላት፣ ዋስ መያዝ አይገባውም  ሁሉም ምእመናን ወደ ቤተክርስቲያንበንጽሕና በትሕትና ሆነው ይምጡ እንጂ  ዳኛ ግብሬን፣ አበዳሪ ብድሬን ፣ኤጲስቆጶስ ዐሥራትራት  ነጋ ድራስ ቀረጥ አምጡ ይሉናል ብለው ሳይፈሩ ይምጡ። ከነጋድራሶች አንዱ እንኳወደ ቤተክርስትያን ከሚሄዱ ሰዎች ቀረጥ ይቀበል ዘንድ የድፍረት ሥራ የሠራ ቢሆን እጽፍአድርጎ ይክፈል። " ፍትሐ ነገሥት ገጽ 258-259
ቅድስት ቤተክርስቲያን ይህን ያህል ጥንቃቄ የምታደርገው ሰዎች በተለያየ ምክንያት ከቤተእግዚአብሔር እንዳይርቁ ከዛም አልፎ ተበዳይም ሆነ በዳይ ፣በዕዳ የሚጠየቅም ሆነ የሚጠይቅሁለቱም በአንድነት ቅዱስ ቃሉን ሲሰሙ ዋሽቶ የሰው ዕዳ ያልከፈለውም ተጸጽቶ ይክሳል ወራትብሶበት ቀን ጥሎት መክፈል ላልቻለውም ምህረት ይቅርታ እንዲያገኝ ቅዱስ ቃሉ ጸሎቱምክንያት ይሆነዋል  በዚህም የተነሳ ሁለቱም ወገኖች በክፉ ከመፈላለግ ይልቅ የይቅርታየምህረት ሰዎች ይሆናሉ። እንግዲህ በዚህች  በዓላት በምትሆን በቅድስት በዕለተ ሰንበትየምእመናን መንፈሳዊ ሕይወት ይባረካል ይቀደሳል በዚህ ታሳቢነት ዕለቱም ዕለተ ቅድስና መሆኑንለማጠየቅ ቅድስት ተብሏል 
ቅድስና የተፈቀደልን ብቻ ሳይሆን የታዘዝነውም ጭምር ነው "እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁቅዱስ ነኝና እናንተ ቅዱሳን ሁኑ" ዘሌ.19በዚህ ኃይለ ቃል ውስጥ ቅድስና እንደ ፈቃድምእንደ ትእዛዝም ሆኖ ተሰጥቶናል እግዚአብሔር ያልፈቀደውን ነገር አድርጉ ሁኑ ብሎ አያዝም የቅድስና ሕይወት መሰረቱ የእግዚአብሔር ፈቃድና ትእዛዝ ሆኖ ሳለ ለመቀደስ የእኛ መሻትመፈለግ ዝንባሌም ወሳኝ ነው። ለዚህም ነው ሐዋርያው እንዲህ ሲል የጻፈልን "ትቀደሱም ዘንድፈልጉ፥" ዕብ 1214 ምንም እንኳን ቅድስና የተፈቀደና የታዘዘ ቢሆንም የውዴታ እና የነጻፈቃድ ውጤት እንጂ የምንገደድበት አይደለም። እግዚአብሔር ፍቅሩ ገብቶን ወደን እና ፈቅደንበፈቃዱ እና በትእዛዙ ስንመራ ያስደስተዋል እንጂ ተገደን ፈርተን ተንቀጥቅጠን እንድንገዛለትአይወድም 
ወደ ቅደመ ነገራችን ስንመለስ ዕለተ ሰንበትም ቅድስት መባሏ ከላይ ያብራራነውን መሰረታዊሃሳብ በተከተለ መልኩ ነው። ዕለቲቱ ቅድስት መባሏ ዋና ዓላማ በሰዎች እና በእግዚአብሔርመካከል ለቅድስና ሕይወት ምልክት ማስታወሻ እንድትሆን ነው። በባህሪው ቅዱስ የሆነ አምላክዓለምን የማዳን ስራውን የጀመረበትን ጽንሰቱን እንዲሁም የማዳን ስራውም አጠናቆ ሙስናመቃብርን አጥፍቶ ዘላለማዊ ሕይወትን ያበሰረበትን ትንሳኤውን የምናስብበት በመሆኑ የዕለቱቅድስና የፈጣሪን ቅዱስ ተግባር የምናደንቅበት ከማንኛውም የሥጋ ሥራ ተለይተን የዋለልን ሁለታከፍ ከፍ እያድረግን እርሱን የምናመሰግንበት ዕለት ነው። ይህም እኛን ወደ በለጠ የቅድስናሕይወት የሚያሸጋግረን ከመሆኑም በላይ የእግዚአብሔርን ጥልቅ ፍቅር በየጊዜው እንድናስብናበፍቅሩም እንድንኖር ያግዘናል።
ከጾሙ በረከት ያሳትፈን!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር።

ምኵራብ

ቀሲስ ኃይለኢየሱስ ተመስገን
ምኵራብ
መጋቢት 10 ቀን 2008 ዓ.ም
ከሁሉ አስቀድሞ ሃይማኖትን መመስከር እንዲገባ ቅድመ ዓለም ከእግዚአብሔር አብ ያለ እናት አካል ዘእምአካል ባህርይ ዘእምባህርይ የተወለደ ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው አካላዊ ቃል ድህረ ዓለም ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም መለወጥ ሳያገኛት ዘር ምክንያት ሳይሆን ከስጋዋ ስጋ ከነፍነፍስ ነስቶ የተወለደ ወልደ እግዚአብሔር ወልደ ማርያም በተዋህዶ ከበረ“ይደልዎነ ንምን ከመ ቦቱ ለወልደ እግዚአብሔር ክልኤቱ ልደታት ቀዳማዊ ልደቱ እም እግዚአብሔር አብ እምቅድመሉ መዋዕል ወዳግማዊ ልደቱ እም እግእዝትነ ቅድስት ድንግል ማርያም በደራዊ መዋዕል”ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ ፴፬ ቁጥር  ክፍል  ብለን በማመን እንደ አባቶቻችን ረድኤተ እግዚአብሔርን አጋዥ አድርገን ስለ ምኵራብ እንማራለን የምናነበውን ለበረከት ያድርግልን አሜን።
የእስራኤል ልጆች መቅደስ(Temple) እና ምኵራብ የሚባሉ ሁለት መንፈሳዊ መገናኛዎች ነበሩአቸው፤ ምራብ [በጽርዕ (Synagogue/ συναγωγή)፡ በዕብራይስጥ (Beyth Kenesset/בית כנסתይባላል። መቅደስ የሚባለው በኢየሩሳሌም ብቻ የሚገኝ ስለ ኃጢአት ስለ ምስጋና መሥዋዕት የሚቀርብበት የብሉይ ኪዳን ማዕከል ነው። ምራብ የቦታ ወሰን የሌለው በየአቅራቢያው የሚገኝ አጥቢያ ቤተ ጸሎት ነው።የምኵራብ መታነፅ ከባቢልን ምርኮ (exile in Babylon 538 A.D.) ጋር የተያያዘ ታሪክ አለው። በባቢሎን ምርኮ በባእድ ሀገር በዚያው ባሉበት ስርተ አምልኮ ለመፈፀም ዳግመኛም ይህ ሁሉ መከራ በአባቶቻችን የተደረገባቸው ቤተመቅደስን ባይሰሩ ነው እኛ ሚጠት የተደረገልን እንደሆነ ቤቱን እንሰራለን በሚል ዋናውን ቤተ መቅደስም ሆነ ብዙ ምኵራባት ሰርተዋል። 10 አባወራዎች ባሉበትም ምኵራብ እንዲሰራ ህጋቸው ያዝ ነበር። በምኵራብም የሚደረገው መንፈሳዊ አገልግልት የብይ ኪዳን መጻሕፍትን ማንበብ መስማትና መተርጎም ንዑሳን በዓላትንም ማክበር ነበር።ማንኛውም እስራኤላዊ በዓመት ሦስት ጊዜ ለበይት በዓላት በኢየሩሳሌም መቅደስ ተገኝቶ አምልኮን መፈጸም ግዴታው ነበር። በምኵራብ ግን በየዕለቱ እየተገኙ ቅዱሳት መጻሕፍትን በንባብ በትርጓሜ ይሰማሉ።
በቃል መነገሩ በልብ መታሰቡ ከፍ ከፍ ይበልና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምኵራብ ተገኝቶ እንዳስተማረ ለመግለጥ ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅደስ ያሬድ ማሕሌታዊ የዓቢይ ጾም ሦስተኛውን ሰንበት ምኵራብ ብሎ ሰይሞታል። ቅዱስ ያሬድ በመዝሙሩ፡- “ ቦኦ ኢየሱስ ምኲራበ አይሁድ ወመሐረ ቃለ ሃይማኖት ወይቤሎሙ ምጽዋት አበድር እመስት አነ ውእቱ እግዚአ ለሰንበት ወአቡሃ ለምሕረት ኢትግበሩ ቤተ አቡ ቤተ ምስያጥ ቤትየ ቤተ ጸሎት ትሰመይ . . .”ትርጓሜው፡- “ኢየሱስ ወደ አይሁድ ምኵራብ ገባ። የሃይማኖትን ቃል አስተማረ። ከመሥዋዕትም ምጽዋትን እወዳለሁ አላቸው። የሰንበት ጌታዋ የምሕረት አባቷ እኔ ነኝ አላቸው የአባቴ ቤት የንግድ ቤት አታድርጉት ቤቴ የጸሎት ቤት ይባላል። ምኵራብ ገብቶ ተቆጣቸው ዝም ይሉ ዘንድ ትምህርቱን የቃሉን ሞገስ፣ የነገሩን መወደድ፣ የአፉን ለዛ አደነቁ” በማለት ቅደስ ያሬድ ዘምሯል።
ቅዱስ ያሬድ በሰዓታት በወራት እና በዘመናት የተከፋፈሉ ድንቅ ምሥጢር የያዙ መዝሙራትን(ምስጋና) ከብሉያትና ከሐዲሳት ለቤተክርስቲያን እንደ ንብ ቀስሞ እንደ ሰምና ወርቅ አስማምቶ የአገልግሎት ሥርዓትን የሠራ የቤተ ክርስቲያን ሊቅ ነው።ለምኵራብ የሚሆነውንም ዝማሬ ከዮሐ 2፡12-25 ላይ ወስዶ አመስጥሮ እስማምቶ ጾመ ድጓ በተባለ ጽሐፉ አዘጋጅቶልናል። ይህንን የመጽሐፍ ክፍል እንደሚከተለው እናየዋለን።
ቁ.12 ከዚህ በኋላ ከእናቱና ከወንድሞቹ ከደቀመዛሙርቱም ጋር ወደ ቅፍርናሆም ወረደ፣ በዚያም ጥቂት ቀን ኖሩ” ከቃና ዘገሊላው የዶኪማስ ቤት ሰርግ ውሃውን ወይን አድርጎ ታምራቱን ካሳየ በኋላ ወደ ቅፍርናሆም ከእናቱና ከወንድሞቹ ደቀመዛሙርት ጋር ሄደ በዚያም ጥቂት ቀን (11 ቀን ይላል በወንጌል አንድምታ) ተቀመጡ። ቁ.13 የአይሁድ ፋሲካም ቀርቦ ነበር ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳም ወጣ።” ይህም የመጀመሪያ ፋሲካ ነው ጌታ የተሰቀለው በአራተኛው ነውበምስጢርም ኢየሩሳሌም ወጣ መባሉ ጌታ ከሕይት ወደመስቀል ምእመናንም ወደ ሕይት የሚሄዱበት ዘምን በደረሰ ጊዜ ጌታ ገረ ሰላም ኢየሩሳም ወደተባለ መስቀል ሄደ ማለት ነውቁ.14 በመቅደስም በሬዎችንና በጎችን ርግቦችንም የሚሸጡትን ገንዘብ ለዋጮችንም ተቀምጠው አገኘ፤” ለስም አጠራሩ የክብር ክብር ይግባውና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምኵራብ በተገኘ ጊዜ በሬዎችንና በጎችን ርግቦችንም የሚሸጡትን ገንዘብ ለዋጮችንም ተቀምጠው ከሚነበበው እና ከሚተረጎመው ከሚፀለየውም ይልቅ የሚሸጠውና የሚለውጠው በዝቶ ተመለከተ ውንብድና ቢሉ ፈሪሳዊያን የሚያንፀባርቅ እና የሚያንሽዋሻ ልብስ ለብሰው በውጭ ከብቱን ያስደነብሩና ወደምኵራብ ያስገቡታል ከዚያም ከል የገባ አይነጣም ቤተመቅደስ የገባ አይወጣም እያሉ የህዝቡን ገንዘብ ይቀሙታል።መለወጥ ቢሉ ህዝቡ መባ ሊያስገቡ ቀይ ወርቅ ይዘው ሲመጡ እግዚአብሔርማ የሚሻው ነጭ ወርቅ እንጅ ቀይ ወርቅ ነውን ይሉታል እነርሱም በትህትና እውነት ነው ብናጣ ነው እንጅ ለእግዚአብሔርማ ንፁህ ማቅረብ ይገባል ይላሉ ከልብ ካለቀሱ እንባ አይገድም ሁለት ቀይ ወርቅ ብታመጡ ባንድ ነጭ ወርቅ እንለውጣችኋለን እያሉ ይበዘብዟቸዋል።ከብቱን ከስቷል ጥፍሩ ዘርዝሯል ፀጉሩ አሯል ለእግዚአብሔርማ የሰባውን ማቅረብ ይገባል ይሏቸዋል እነርሱም በትህትና እውነት ነው በመንገድ ደክሞብን ከስቶብን እንጅ ለእግዚአብሔርማ የሰባውን ማቅረብ ይገባል ይላሉ ከልብ ካለቀሱ እንባ አይገድም ሁለት የከሳ ከብት ብታመጡ ባንድ የሰባ እንለውጣችኋለን ይሏቸዋል መሸጥም ቢሉ የከሳውን ከብት አወፍረው አድልበው ይሸጡ ነበር
ቁ.15-16 የገመድም ጅራፍ አበጅቶ ሁሉን በጎችንም በሬዎችንም ከመቅደስ አወጣቸው የለዋጮችንም ገንዘብ አፈሰሰ፣ ገበታዎቻቸውንም ገለበጠ፣ ርግብ ሻጪዎችንም ይህን ከዚህ ውሰዱ። የአባቴን ቤት የንግድ ቤት አታድርጉት አላቸው፡” በቤተ ፀሎት ይህን ያልተገባ ነገር ሲፈፅሙም የገመድ ጅራፍ አበጅቶ ሁሉን በጎችንም በሬዎችንም ከመቅደስ አወጣቸው ይላል ይህንም ጅራፍ ሐዋርያት አዘጋጅተው ሰጥተውታል የጭፍራውን ለአለቃው መስጠት ልማድ ንውና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ገበያውን ፈታ። ለሰውነታቸው ቤዛ የሚሆናቸው ስለሆነም የለዋጮችንም ገንዘብ አፈሰሰ፣ ገበታዎቻቸውንም ገለበጠ፣ በትር አይችሉምና ርግብ ሻጪዎችንም ይህን ከዚህ ውሰዱ አላቸው። የአባቴን ቤት የንግድ ቤት አታድርጉት አላቸው። በተአምራትም ገንዘብ ገንዘባቸውን ለይቶ ከዛፍ ላይ እንደሰፈረ ንብ ከቃ ከቃቸው ላይ አስቀምጦላቸዋል። ቁ.17 ደቀ መዛሙርቱም የቤትህ ቅናት ይበላኛል ተብሎ እንደተጻፈ አሰቡ።ነቢየ እግዚአብሄር ቅዱስ ዳዊት በመዝ 68፡9 በቤተ መቅደስ ስዕለ ፀሀይ አቁመውበት መስዋእተ እሪያ ሰውተውበት ገበያ አድርገውት ሲሸጡበት ሲለውጡበት በመንፈሰ ትንቢት ተመልክቶ ለቤተ እግዚአብሄር የቀናውን ቅናት እንደ እሳት አቃጠለኝ ይላል።
እስመ ቅንዐተ ቤትከ በልዐኒ ትዕይርቶሙ ለእለ ይትዔየሩከ ወድቀ ላዕየ ወቀጻዕክዋ በጾም ለነፍስየ። ትርጉም የቤትህ ቅንዓት በልታኛለችና የሚሰድቡህም ስድብ በላዬ ወድቆአልና ነፍሴን በጾም አስመረርኋት። 
ይህ ትንቢት ለጊዜው ለመቃቢስ ፍፃሜው ለጌታ የተነገረ ነው። በመቃቢስ ጊዜ አንያኮስ በቤተመቅደሱ አምልኮ ፀሀይ አግብቶ እሪያ ሰውቶ ነበርና፤መቃቢስ ያንን አጥፍቶ ለቤተመቅደሱ የቀናውን ቅንዓት ያመለክታል። በልዑል እግዚአብሔር ላይ በስህተትም ሆነ በድፍረት የሚቀርብ ተግዳሮት በቅዱሳንም ይደርሳል። ልዑል እግዚአብሔር ባህርዩ ደርሶ የሚገዳደር የለም እርሱ ነገሥታት የማይነሣሡበት መኳንንትም የማይበረታቱበት አምላከ አማልክት ወንጉሠ ነገሥት ነው። ነገር ግን የአምልኮቱ መገለጫ በሆኑት በቤተመቅደስ ውስጥ ባሉት ታቦታት፣ንዋያተ ቅደሳት፣በዓላትና ሥርዓቶች እንዲሁም እርሱ የላካቸውን ቅዱሳን መግፋት መገዳደር ጌታ እግዚአብሔርን መገዳደር ነው። ነቢየ እግዚአብሄር በቤተመቅደስ ገበያ አቁመው የሚገዳደሩትን ባየሁ ጊዜ ተግዳሮታቸው በእኔ ላይ ወደቀ ነፍሴንም በጾም አስመረርኋት ይላል። በደብተራ ኦሪት ሁለት እጓላተ ለህም አቁመው እንደተገዳደሩት፣መና ከደመና አውርዶ ቢመግባቸው ምንት ጣዕሙ ለዝ መና ብለው እንደተፈታተኑት ፣ በኋላም ወልደ እጓለ እምሕያው ስጋየን የበላ ደሜን የጠጣ የዘላለም ህይወት አለው ቢላቸው እፎ ይክል ዝንቱ የሀበነ ሥጋሁ ንብላዕ ብለው እንደተገዳደሩት በመንፈሰ ትንቢት ተመልክቶ ሰውነቴን በርሃብ በቀጠና አደከምኩዋት እያለ ነቢየ እግዚአብሔር የተናገረውን ደቀመዛሙርቱ አስበው እነሱም ለቤቱ ቀኑ በዚህ ዘመን እኛም ለቤተክርስቲያን ቅናት ሊኖረን ይገባል ለክብሩ መቅናት ለገዳማቱ ለአብነት ትምህርት ቤቱ መፈታት ለሊቃውንቱ መታረዝ ልቡናችን ሊቃጠል ይገባል። ኢየሱስም መልሶ ይህን ቤተመቅደስ አፍርሱት በሦስት ቀንም አነሣዋለሁ አላቸው ስለዚህ አይሁድ ይህ ቤተ መቅደስ ከአርባ ስድስት ዓመት ጀምሮ ይሠራ ነበር፣ አንተስ በሦስት ቀን ታነሣዋለህን አሉት። እርሱ ግን ስለ ሰውነቱ ቤተመቅደስ ይል ነበር። ስለዚህ ከሙታን ከተነሣ በኋላ ደቀመዛሙርቱ ይህን እንደተናገረ አሰቡና መጽሐፍንና ኢየሱስ የተናገረውን ቃል አመኑ።” ቁ.19 እና 20 በ46ቱ የብሉይ ኪዳን መጽሐፍት የተነገረውን ልደቱን ሞቱን በሶስተኛው ቀን መነሳቱን ሁሉ ስለ ሰውነቱ አስረዳቸው። እሠራዋለሁ አላለም አነሣዋለሁ እንጂ። በዚህም የሞቱንና የትንሣኤውን ነገር ገለጠ።
አንጽሆተ ቤተመቅደስ
ይህም ቀን የማንጻት ቀን አንጽሆተ ቤተመቅደስ ይባላል።ኦሪት ወንጌልን፣ ምኵራብ ቤተክርስቲያንን አስገኝተዋል ጌም የበግ የፍየል መስዋእት መቅረቱን ለቤዛ ዓለም መምጣቱን አስተማሯቸዋል አስጠንቅቋቸዋል። ምኵራብ ሁሉ የማይገባባት ነበረች በመጽሐፈ ነህምያ ምዕ 13፡1 “አሞናውያንና ሞዓባውያንም ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ ለዘላለም እንዳይገቡ የሚል በዚያ ተገኘ።” ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው የማይመረጥባት አንተ አይሁዳ አንተ ሮማዊ የማትል አንዲትት ቤተመቅደስን ሰጠን
ምኵራብ /ቤተ መቅደስ/ የሰውልጅ ምሳሌ ነው ምኵራብ የእግዚአብሔር ማደሪያ ነው። የሰው ልጅም የእግዚአብሔር ማደሪያ ነው ሸቀጡም የኃጢአት ምሳሌ ነው ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ ሰውነትን ስለማንፃት እና እራስን ከሸቀጥ ስለማራገፍ ለቆሮንቶስ ክርስቲያኖች ያስተማረውን ማሰብ ያስፈልጋል እኛም የህያው አምላክ የጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቤተመቅደስ ነንና ሰውነታችን ሽያጭ የሚፀናበት እንዳይሆን ልንጠነቀቅ ያስፈልጋል
1ኛቆሮ ምዕራፍ 3-17 “የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ቅዱስ ነውና፥ ያውም እናንተ ናችሁ።”
1ኛቆሮ ምዕራፍ 6-20 ላይ “ሥጋችሁ ከእግዚአብሔር የተቀበላችሁት በእናንተ የሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንደ ሆነ አታውቁምን? በዋጋ ተገዝታችኋልና ለራሳችሁ አይደላችሁም፤ ስለዚህ በሥጋችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ።”
2ኛቆሮ ምዕራፍ 2-17 የእግዚአብሔርን ቃል ቀላቅለው እንደሚሸቃቅጡት እንደ ብዙዎቹ አይደለንምና፤ በቅንነት ግን ከእግዚአብሔር እንደ ተላክን በእግዚአብሔር ፊት በክርስቶስ ሆነን እንናገራለን።
በቅዳሴ ያዕቆብ ዘስሩግ “ተንስኡ በፍርሃተ እግዚአብሔር ከመ ታፅምኡ አርኅው መሳክወ አእዛኒክሙ ወአንቅሁ ልበክሙ” እግዚአብሔርን በመፍራት ተነሱ የጆሮቻችሁን መስኮቶች ክፈቱ ልቦናችሁን አንቁት እንደተባልን ሳንዝ ማን አዚም አደረገባችሁ ተብለንም እንዳንወቀስ የእግዚአብሔርን ተግሳፅ የአበውን ምክር ሰምተን አሁን ሰውነታችን በንስ ለማንጻት እንነሳ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊትም በመዝ 94፡8 “ዮም አመ ሰማዕክሙ ቃሎ ኢታፅንኡ ልበክሙ ዛሬ የእግዚአብሔርን ቃል ስትስሙ ልባችሁን አታፅኑት እንዳለ ይህን በምኵራብ አምላካችን ያደረገውን ስንሰማ የዘረኝነት የፍቅረ ንዋይ የተንኮል የትዕቢት ሸቀጣችን ትተን ቤተመቅደስ ሰውነታችን በንስ አጥበን ልባችን በትህትና ሞልተን በቤቱ ለበለጠው ጸጋ ቀንተን ቅንነትንም አክለን በቤቱ ለመኖር አምላካችን ይርዳን አሜን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!

Tuesday, 15 March 2016

Dn Henok Haile ኃጢአቱን የሚሰውር እይለማም

An Ethiopian Orthodox Church {KEDASSE} Ceremony

ቅዳሴ ማለት ምንም ማለት ነው???

ቅዳሴ ማለት ምንም ማለት ነው???
+
በቅዳሴ ጊዜ 5ቱ ምሥዋዕቶች ምን ምን ናቸው?
14ቱ ፍሬ ቅዳሴያት እነማን ይሆኑ?
ካህናት በቅዳሴ ወቅት 2: 3: 4: 5: 7: 12: ወይም 24: ሆነው ከቀደሱ ምሳሌነቱ ምን ምን ይሆን?
እኛ ክርስቲያኖች ቅዳሴን ባስቀደስን ቁጥር 4 ነገሮች እናገኛለን ምን ይሆኑ?
አምስቱ የስሜት ሕዋሳት በፀሎተ ቅዳሴ ጊዜ ያስቀድሳሉ እንዴት?
አውቀነው እንጠቀምበት ዘንድ ይነበብ.....ለሌሎች ሰማያዊ ምሥጢርን አካፍለን የተሰጠንን መክሊት እናተርፍበት ዘንድ እንትጋ
‪#‎ቅዳሴ‬
ቅዳሴ በሥርዓተ ቤተክርስቲያናችን ሥርዓት መሠረት በኅብረት የሚጸለይ የኅብረት ጸሎት ነው፡፡ ከፀሎቶች ሁሉ የላቀ የፀሎት ክፍል ነው፡፡ በቅዳሴ ጊዜ ፭ቱ ምሥዋዕቶች ተሞልተው ይገኙበታል እዚህንም ፭ቱን መሥዋዕቶች ማንኛውም ክርስተያን ለፈጣሪው የሚያቀርበው ነው፡፡
፩. የቁርባን መስዋዕት፡-
+
በፀሎተ ቅዳሴ ጊዜ ውስጥ ኅብስቱ ተለውጦ ሥጋ መለኮት ወይኑ ተለውጦ ደመ መለኮት የሚሆነው በቅዳሴው ፀሎት ነው ሳናስቀድስ አንቆርብምና የቁርባን መስዋዕት የሚፈጸመው በሥርዓተ ቅዳሴ ብቻ ነው፡፡ መስዋዕቱም በቤተልሔም ይዘጋጃል በቤተክርስቲያን ውስጥ በቤተ-መቅደስ ውስጥ ደግሞ ይቀርባል ወይም ይታደላል፡፡ ጌታችን ሲወለደ በቤተልሔም ተወልዶ ቀራንዮ ለዓለም ሁሉ መስዋዕት ሆኗልና ቀራንዮ በተባለች በቤተክርስቲያን ቅዱሱ መስዋዕት ለሕዝብ ይታደላል፡፡
፪. የከንፈር መስዋዕት፡-
+
ካህኑ፣ ዲያቆኑና ሕዝቡ በመቀባበል በአንድነት ምስጋና ለፈጣሪያቸው የሚያቀርቡበት የከንፈራችን ፍሬ የሚሰዋበት የፀሎት ክፍል ፀሎተ ቅዳሴ ነው፡፡
፫. የመብራት መስዋዕት፡-
+
በቅዳሴ ጊዜ የሚበራው ጦፍ ለእግዚአብሔር
የሚቀርብ የሚሰጥ የመብራት መስዋዕት ነው፡፡ ምሳሌነቱም የጌታችን
የኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ነው ይህውም ጌታችን ጨላመ ለሆነ ዓለም
ብርሃን ሆኖ ብርሃንን ሊያበራ ወደ ዓለም መቷልና ነው፡፡
፬. የዕጣን መስዋዕት፡-
+
የዕጣን ፀሎት ካህኑ ብቻ የሚያጥነው ሲሆን ይህውም በማዕጠንቱ አማካኝነት ቅዱሱን እጣን በመንበሩ፣ በቅዱሳን ስዕላቱ፣ በሕዝቡ መካከል ያጥናል ይህውም የሕዝቡን ፀሎት ወደላይ በደሥላሴ መንበር ይዞ ይወጣል በሰማይም ያሉ ቅዱሳን መላእክት ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እያሉ የሥላሴን መንበር እንደሚያጥኑ ሁሉ በምድርም ያለው ካህን የሰማያዊው ምሳሌ ነውና በምድር ያውን መንበር በማጠን ለእግዚአብሔር የዕጣን መስዋዕት ያቀርባል፡፡
፭. የሰውነት መስዋዕትነት፡-
+
በቅዳሴ ጊዜ አብዛኛውን ሰዓት ሙሉውን ማለት ይቻላል በመቆም የሚፀለይ የፀሎት ክፍል ነው፡፡ በመሐል 2 ጊዜያት ብቻ የስገዱ ትዕዛዝ ሲተላለፍ ሕዝቡ ሁሉ ፊቱን ወደ ፈጣሪው አዞሮ እራሱን አዋርዶ ይሰግዳል በእግዚአብሔር ፊት መቆምም ሆነ መስገድ ለእግዚአብሔር የሚሰጥ የሰውነት መሥዋዕት ነው፡፡

ይህ የፀሎት ክፍል (ቅዳሴ) በሦስት ዋና ዋና ክፍሎች ይከፈላ
፩. የዝግጅት ክፍል
፪. የንባብና የትምህርት ክፍል
፫. ፍሬ ቅዳሴ
እዚህ ፍሬ ቅዳሴያት እንደየበዓሉ ይለዋወጣተሉ ብዛታቸውም ፲፬ (14) ናቸው እነዚህም፡-
፫.፩. ሥርዓተ ቅዳሴ
፫.፪. ቅዳሴ ዘሐዋርያት
፫.፫. ቅዳሴ እግዚእ
፫.፬. ቅዳሴ ማርያም
፫.፭. ቅዳሴ ዘዮሐንስ ወልደ ነጓድጓድ
፫.፮. ቅዳሴ ዘሠለስቱ ምዕት
፫.፯. ቅዳሴ ዘአትናቴዎስ
፫.፰. ቅዳሴ ባስልዮስ
፫.፱. ቅዳሴ ጎርጎርዮስ
፫.፲. ቅዳሴ ዘኤጲፋንዮስ
፫.፲፩. ቅዳሴ ዘዮሐንስ አፈወርቅ
፫.፲፪. ቅዳሴ ዘቄርሎስ
፫.፲፫. ቅዳሴ ዘያዕቆብ ዘሥሩግ
፫.፲፬. ቅዳሴ ዘዲዮስቆሮስ


-የጌታችን በዓል ከሆነ … (ቅዳሴ እግዚእ)
-የጌታችን ምጽአት፣ ጶጉሜ እሁድ ቀን ከዋለች ሰንበት … (ቅዳሴ አትናቴዎስ)
-የእመቤታችን በዓል ከሆነ ቅዳሴ ማርያም … (ጎሳ ልብየ ቃለ ሰናየ)
-የመላእክትና የሐዋርያት በዓል ከሆነ … (ቅዳሴ ዘያዕቆብ ዘሥሩግ)
-ከዘመነ ልደት እስከ ዘመነ ግዝረት … (ቅዱስ ጎርጎርዮስ ካልዕ)

ቅዳሴን ለመቀደስ ብዙ ጊዜ ፭ሆነው ይቀድሳሉ ይህው የአምስቱ አዕማደ ምሥጢራት ምሣሌ ናቸው፡፡ ነገር ግን ከዚያም በሚያንስም ሆነ በሚበዛ ሰው ቅዳሴን መቀደስ ይቻላል ለምሳሌ ፯ ሰባቱ ምሥጢራተ ቤተክርስቲያን ይመስላሉ ፲፫ በ12ቱ ሐዋርያት እና በጌታችን ምሳሌ ሆነው ይቀድሳሉ፤ 24 በሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ይህ የሚሆነው እንደ ካህናቱ ብዛት ነው ጭራሽ ካህን ከጠፋ ደግሞ 1 ቄስና 1 ዲያቆን ሆነው መቀደስ ይችላሉ ሁለትነታቸው የመለኮትና የትስብዕት (የሥጋ) ምሳሌ ሆነው ይቀድሳሉ በሦስት ከሆነ በሦስቱ ሥላሴዎች አራት ከሆኑ በ4ቱ ወንጌላውያን ይመሰላሉ ከሁለት ባነሰ ግን 1 ሆኖ ግን ቅዳሴ አይቀደስም ቀኖናው የቤተክርስቲያኒቱ ሥርዓት ይከለክላል፡፡

“ጸልዩ” ይህ የቅዳሴው የፀሎት ዓይነት ሲሆን ለ13 ጊዜያት ይባላል፡፡
በሦስተኛው ክፍለ ቅዳሴ 4 ጊዜ ይባላል ፀልዩን ዲያቆኑ ሲያውጅ ፊቱን ወደ ህዝቡ ይመልስና እንዲጸልዩ ያውጃል፡፡ በዚህ ጊዜ ተሰጥዖ ካለ ተሰጥዖ ይመለሳል ከሌለ ግን “አቡነ ዘበሰማያት” ሕዝቡ እንዲደግሙ ያውጃል፡፡
+
ለምሳሌ፡-
ንፍቁ ዲያቆን “ፀልዩ በእንተ እለያበዕኡ መባዕ … መባን ስለሚያገቡ
ሰዎች ፀልዩ” ሲል በዚህ ጊዜ አቡነ ዘበሰማያት አይደገምም ምክንያቱም
የራሱ ተሰጥዖ ስላለው “ተወከፍ መባዖሙ ለአሃው ወተወከፍ መባዖን…”
ይህ አቡነ ዘበሰማያት የሚተካ ፀሎት ነው፡፡
ድርገት ሲወርዱ “ፀልዩ በእንቲአነ” በሚባልበት ጊዜ እንድንጸልየው
የሚያዘው የዳዊትን መዝሙር 150ኛውን መዝሙር ነው፡፡ ፀልዩ ብሎ
ያዘዘው በዚህ ክፍል ያለ የዳዊትን 150ኛውን የመዝሙር ክፍል ነው
ማለት ነው፡፡

• ☆
እኛ ክርስቲያኖች ቅዳሴን ባስቀደስን ቁጥር
1ኛ የኃጢአት ሥርየት ይገኛል ምክንያቱም በአንቃዕዶ ሕሊና ይቅርታን ስለሚጠይቅ፣
2ኛ በነፍስም በስጋም በረከትን ያገኛል፣
3ኛ ጸሎቱም ይደመጣል፣
4ኛ የመላእክትን በረከት በቀጥታ እንሳተፋልን ቅዳሴን አስቀድሶ ሥጋ ወደሙ ሲቀበል የዘለዓለምን በረከት ያገኛል፡፡
+
በተጨማሪም ቅዳሴ በማስቀደስ
4 ነገሮች ይገኛሉ እነዚህም፡-
፩. ትምህርት
+
የቤተክርስቲያኒቱን ዶግማ እና የሥርዓተ ቤተክርስቲያን ትምህርት በቅዳሴ ገዚ ያገኛል፡፡ ለምሳሌ የማርያምን ቅዳሴ አባ ሕርያቆስ የደረሰውን ይህን ቅዳሴ ሲቀደስ በውስጡ ምሥጢረ ሥላሴ፣ እና ምሥጢረ ሥጋዊ እና ነገረ ማርያምን አምልቶ ይነግራል፡፡
፪. ታሪክ
+
14ቱንም ቅዳሴ የሚያስቀድስ ሰው የቤተክርስቲያንን ታሪክ በቅዳሴ ውስጥ እንማራለን፡፡
፫. ምክር
+
በቅዳሴ ውስጥ ተፋቀሩ፣ መጽውቱ፣ ተስማሙ፣ ጹሙ፣ ጸልዩ እየተባለ በቅዳሴ ውስጥ ሰፋ ባለመልኩ ምክር ይሰጣል ስለዚህ ቅዳሴን በማስቀደስ ምክርን ማግኝት ይቻላል ማለት ነው፡፡
heart emoticon
፬. ተግሣጽ
+
ቅዳሴ ውስጡ ተግሣጽን ይዞ እናገኝዋለን ለምሳሌ በቅዳሴ እግዚእ ላይ ከወንድሙ ጋር የተጣለ ቢኖር ይተውለት ይላል በዚህ የቅዳሴ ክፍል ውስጥ ራሳችንን ምን ላይ እንደቆምን ከሰዎች ጋር ያለንን ኅብረት ስምምነት ለፈጣሪ ራሳችንን ማስገዛታችንን እየገሠፀ ይነግረናል፡፡ እነዚህን መሠረታዊ የሆኑትን ለሰው ልጆች ጠቃሚ የሆኑ ነገሮችን ቅዳሴ በማስቀደስ እናገኛቸዋለን፡፡
-ቅዳሴ ንባብም ዜማም የሚቀርብበት የፀሎት ክፍል ነው፡፡ ሁላችንም የምንሳተፍበት ቄሴም ዲያቆኑም ምእመኑም የሚሳተፉበት ነው፡፡
“ኢትቁም እራቀከ ቅድመ ነቢየ እግዚአብሔር … በእግዚአብሔር ነብይ ፊት ራቁትህን አትቁም” ይህ ማለት በቅዳሴ ጊዜ ሰው ካለ መባ፣ ካለ እጅ መንሻ በእግዚአብሔር ፊት ሳይዙ መቆም እንደሌለበት ያጠይቃል፡፡ ምንም ባይኖረን እንኳን ያለንን አነሰ ብለን ሳንሳቀቅ ደግሞም ሳንንቃት ይዘን በፊቱ መቅረብ አለብን ከቻልን እጣኑን፣ ዘቢቡን፣ ጦፉን ሌላም ሌላም ይዘን መሄድ ተገቢ ነው፡፡ ምክንያቱም ካህኑ በቅዳሴው መሃል ምዕናን ስለሚያስገቡት መባ የሚፀልየው ፀሎት አለ ምዕመኑም መባን ይዞ የማይመጣ ከሆነ ይህ ፀሎት ለማን ነው? ብሎ መጠየቅም ይገባል፡፡
-ስለዚህ ቅዳሴን የምናስቀድሰው አስቀድመን ተዘጋጅተንበት መሆን አለበት፡፡ ለሌሎች መንፈሳዊ አገልግሎቶች ጊዜ ባይኖረን ለቅዳሴ ግን ጊዜ መድበንለት ልናስቀድስ ይገባል፡፡ ቅዳሴ ለማስቀደስ ወደ ቤተክርስቲያን ስንመጣ ራሳችን
+
1ኛ ቆምን ለማስቀደስ
2ኛ የሚነበቡትን መጻሕፍቶች ከሕይወታችን ጋር እያዛመድን ለማዳመጥ ለመስራት
3ኛ ቅዱስ ቁርባን ለመውሰድ የዘለዓለም ሕይወትንም ለማግኝት አምኖ መምጣት አለበት
-በቅዳሴው የመግቢያ ክፍል ይህንኑ በዜማ “እስመጨረሻው ቅዳሴውን ያላስቀደስ ቅዱሳን መጻሕፍትን ሲነበቡ ቆሞ ያላዳመጠ በመጨረሻም ቅዱስ ቁርባን ያልተቀበለ ከቤተክርስቲያን ኅብረት ልጅነት ይሰደድ” ይላል ስዚህ ራሱን አዘጋጅቶ መምጣት ይገባል፡፡
☆•♥• ☆ •♥• ☆•♥• ☆
-በተጨማሪም ሰው ለቅዳሴ ሲቆም 5ቱን የሥሜት ሕዋሳቶቹን ሰብስቦ ወደ ቅዳሴው ትኩረት ሰጥቶ በንቃት ለቅዳሴ መቆም አለበት ለዚህም ዲያቆኑ በመሃል በመሃል “ለፀሎት ተነሱ” እያለ ያውጃል ምዕመኑም ራሱን በእግዚአብሔር ፊት አዋርዶ ይቅርታን በመጠየቅ “አቤቱ ይቅር በለን” ይላል፡፡ አምስቱ የስሜት ሕዋሳት የሚባሉት አይን፣ ጆሮ፣ አፍንጫ፣ እጅ እና ምላስ በአንድት በፀሎተ ቅዳሴ ጊዜ ያስቀድሳሉ
ለምሳሌ፡-
heart emoticon
ዐይን፡-
ካህኑ ቅዳሴን ሲቀድስ በመንበሩ አጠገብ ቆሞ ብቻ አይደለም የተለያዩ ዓይነት እንቅስቃሴዎች አሉ እነዛን እንቅስሴዎች ደግሞ ራሳቸውን የቻሉ መንፈሳዊ ምሥጢራዊ ትርጓሜዎች አሉዋቸው እነዚህን እንቅስቃሴዎች አይን ያያል ስለዚህ ዐይን ያስቀድሳል ማለት ነው፡፡
heart emoticon
ጆሮ፡-
ካህኑም ዲያቆኑም ምእመኑም በአንድትም ሆነ በተናጠል የሚያዜሙትን ዜማ፣ የሚያነቡትን ንባብ ይሰማል በዚህ ጊዜ ጆሮአችን ያስቀድሳል ማለት ነው፡፡
heart emoticon
አፍንጫ፡-
የዕጣኑን መዓዛ በማሽተት አፍንጫችን ያስቀድሳል
heart emoticon
ምላስ፡-
ቅዱስ ቁርባን በመውሰድ፣ የቅዳሴውን ፀበል በመጠጣት በዚህ ጊዜ የመቅመስ ስሜታችን ያስቀድሳል፡፡
heart emoticon
የመዳሰስ፡-
የመዳሰስ ስቀሜታችንም ስግዱ በተባለ ጊዜ፣ ወንጌል ከተነበበ በኋላ ወንጌሉን ሲስም በመጨረሻም ሰዓት የካህኑን እጅ ለመባረክ ስንስም የመዳሰስ ስሜታችን ያስቀድሳል ማለት ነው፡፡
♥♥♥
ስለዚህ አምስቱም የስሜት ሕዋሶቻችን በተሟላ መንገድ ከእግዚአብሔር ጋር የሚገናኙበት መንገድ ምንድን ነው ቢባል ቅዳሴ ነው። በቅዳሴ ውስጥ የምናገኘው ትምህርት በአውደምህረት በኮርስ ከምናገኝው ትምህርት የተለየ ነው ይኽውም በዜማ የታሸ ብዙ ሊቃውንት የደከሙበት መንፈስ ቅዱስ እንደገለፀላቸው ለሰው በቀላሉ የሚገቡ ትምህርቶች ናቸው ሌላው ደግሞ ወንጌል ይነበባል መልዕክታት፣ የሐዋርያት ሥራ፣ ከዓለም አቀፍ ከሆኑ ሁሉ እና በዜማ ስለሆነ ነው እንጂ (ምስባክ) የምንለው ከመዝሙረ ዳዊትም ውስጥ ይነበባል።
+ስለዚህ 1 ሰው ቅዳሴን ሲያስቀድስ ሙሉ መጽሐፍ ቅዱስን ከብሉይ እስከ ሐዲስ ድረስ ይማራል ማለት ነው። ረጅም ዘመን ያስቀደሰ በሕይወቱ ውስጥ ምሁር ማለት እርሱ ነው ማለት ነው፡፡ ምክንያቱም ከላይ እንዳልነው ነው፡፡ የመላእክትን ህይወት በምድር ላይ መኖር ማለት ነው፡፡
በቤተክርስቲያናችን ትልቁ ሱታፊ ቅዳሴን ማስቀደስ ነው ይህንንም ከራስ አልፎ ወገኖቻችን ይህን ምሥጢር እንዲሳተፉ ማድረግ ይገባል ልጆቻችን ከቅዳሴው እንዲሳተፉ ተሰጥዖ እንዲመልሱ፣ መባን ይዘው እንዲመጡ፣ ቅዳሴ ለማስቀደስ ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ፣ ቅዱስ ቁርባን እንዲቀበሉ ማድረግ ተገቢ ነው ያለበለዚያ የምሰጠውን የምናጣበት ደረጃ ላይ እንዳንደርስ የቀደመውን ሥርዓተ አምልኮ የሚፈፀምበት ሥርዓት እንዳይጠፋ የሚረከበን እንዳናጣ የቀደመው ለተተኪው ትውልድ ማስረከብ መቻል አለበት ሰማያዊ ምሥጢር በምድረ ከተሰራባት ከመላእክት ጋር አንድ ሆነን ፈጣሪን ከምናመሰግንባት ከቅድስት ቤተክርስቲያን ሳያናውጥ ያኑረን አሜን፡
♥♥♥
ለአባ ሕርያቆስ ፤ለቅዱስ ኤፍሬም ፤ለቅዱስ ያሬድ ፤
ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ የተገለጸች ዕመቤታችን እኛንም
በበረከት እና በረድኤት ትጎብኘን ፤ ከልጅዋ ከወዳጅዋ
ከመድኃኔዓለም ዘንድ ታማልደን ፤ ጾሙን ጾመ ሥርየት ፤ጾመ
መድኃኒት ያድርግልን- አሜን ፡፡
†♥† †♥† †♥† †♥† †♥†
ወ ስ ብ ሐ ት ለ እ ግ ዚ አ ብ ሔ ር
ወ ለ ወ ላ ዲ ቱ ድ ን ግ ል
ወ ለ መ ስ ቀ ሉ ክ ቡ ር
†♥† †♥† †♥† †♥† †♥†