Saturday, 18 June 2016
"መጥፎውን ሽሹ መልካሙን እሹ": ሎቱ ስብሐት !
"መጥፎውን ሽሹ መልካሙን እሹ": ሎቱ ስብሐት !: ©መልካሙ በየነ ግንቦት 30/2008 ዓ.ም የቅብአት እምነት ከጾም ቀናት መለያየት ውጭ ከተዋሕዶ ጋር ያለው ልዩነት ብዙ መስሎ አይታየንም ነበር አሁን ግን አምላክ የተመሰገነ ይሁን ይኼው "ወልደ አብ" ታ...
ጎጆ ቤት እና የባቄላ እሸት
ጎጆ ቤት እና የባቄላ እሸት

ንስሓ
ንስሓ

ቤተ ክርስቲያንስ ሄዋን ናት
ቤተ ክርስቲያንስ ሄዋን ናት
አንድ የተሐድሶ ሰባኪ “ያረጀችው ቤተ ክርስቲያን አሮጊቷ
ሣራ ወለደች፡፡ እኔን ወለደች፣ እገሌን ወለደች፣ እገሊትን ወለደች” እያለ ተሐድሶ የወለደቻቸውን ይዘረዝራል፡፡ ቤተክርስቲያን
አሮጌ መባሏ ያበሳጨው የተዋሕዶ ልጅ ወደ “ሰባኪው” ተጠግቶ
“መጽሐፍ ማንበብ ይቀርሃል ሣራ በእርጅናዋ ወራት የወለደችው አንድ
ልጅ ይስሐቅን ብቻ እንደነበር አላወቅህም እንዴ? አሮጊቷ ሣራ እኔን፣ እገሌን፣ እገሊትን ወለደች እያልህ የምትቀባጥር፡፡ ቤተ ክርስቲያንስ
አሮጊት ሣራ ሳትሆን ቀድሞ የነበረች መንታ መንታ የምትወልድ የብዙዎች እናት ሄዋን ናት፡፡፡ የግል ክብርህን ፈልገህ ደግ ይስሐቅን
ነኝ ለማለት ክብርት ቤተክርስቲያንን ዝቅ ዝቅ ያደረግህበት ይህ ደፋር አንደበት በደሙ በመሠረታት በክርስቶስ ፍርድ ወንበር ፊት
ስትቆም ምን ይናገር ይሆን?” በማለት ብዙ ትምህርት አስተማረው፡፡
ሥርዓቷ ሳይሆን ሕንጻዋ
አንድ መናፍቅ “ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ያረጀች
ያፈጀች ናትና በአዲስ ነገር መታደስ ይገባታል፡፡” እያለ በይፋ ይናገራል፡፡ ይህን የሰሙ አንድ የቤተክርስቲያን ሊቅ መናፍቁን
አስጠርተው “የምትለው ሁሉ ልክ ነው፡፡ መታደስ ያለበት ግን ሥርዓቷ
ሳይሆን ሕንጻዋ ስለሆነ የማሳደሻ ገንዘብ አሰባስብ” ሲሉት ያ መናፍቅ “መታደስ የሚገባው ትምህርቷ ሥርዓቷ ነው እንጅ ሕንጻዋ አይደለም” ይላቸዋል፡፡ ሊቁም “በል እንግዲያውስ የራስህን አእምሮ በመልካም ትምህርትና ሥርዓት አድስና ከዚያ በኋላ ብንገናኝ ይሻላል” ብለው
አባረሩት፡፡
እንዘምራለን ስትናፍቀን
ተሐድሶ መናፍቃን እግዚአብሔርን የሚናፍቁበትና የማይናፍቁበት ቀንና ጊዜ አላቸው፡፡ ምክንያቱም ሲፈልጉ ዘማሪ ክርስቲያን ሲፈልጉም ታዋቂ ዘፋኝ በመሆን በተደበላለቀና በተመሰቃቀለ ሕይወት ውስጥ ስለሚኖሩ ነው፡፡ በዝማሬዎቻው ውስጥ የምንሰማው
“ዛሬም የአንተ ነው አዲሱ ቀን
እንዘምራለን ስትናፍቀን”
የሚል ነው፡፡ በእውነት እግዚአብሔር የማይናፈቅበት ወቅት አለን? በዚያስ ወቅት መዘመር አስፈላጊ አይደለምን? ዝማሬን
የናፍቆት መግለጫ ያደረጉት፡፡ ወገኖቼ ሳናውቅ በተኩላ እየተበላን ስለሆነ መንቃት ያስፈልጋል፡፡
መዶሻ ያልያዘ ሠራዊት
ተሐድሶ መናፍቃን በስብከታቸው እና በመዝሙራቸው ውስጥ “መዶሻ
ያልያዘ ሠራዊት” የሚለው መሪ ቃላቸው ሆኗል፡፡ በእውነትም መዶሻ ያልያዘ ከንቱ ሠራዊት ነው፡፡ መዶሻው ቃለ እግዚአብሔር የሚገኘው ቤተክርስቲያን ውስጥ ስለሆነ በየቦታው ሲዞሩ ይህን ማግኘት ባለመቻላቸው
ቃለ እግዚአብሔርን ያልያዘ ሠራዊት ነን ሲሉ “መዶሻ ያልያዘ ሠራዊት”
ነን ይላሉ፡፡ ቃለ እግዚአብሔርን ያልያዘ ሠራዊት ደግሞ የአጋንንት ስለሆነ ከተዋሕዶ ልጆች ጋር ምንም ሕብረት የለውም፡፡
ስብከት ጋዜጠኛነት አይደለም
“እገሌ ሲናገር ሲሰብክ ልዩ ተሰጥዎና ግርማ ሞገስ አለው፡፡ስለዚህም
ተሐድሶ መናፍቅ ሊባል አይገባውም”
የሚሉ ደጋፊዎች በዝተዋል፡፡ እነዚህ ደጋፊዎች ያልገባቸው ነገር የድምፅ ማማር ወይም የንግግር ግርማ ሞገስ መኖር የሰባኪ መመልመያ
መስፈርት ማድረጋቸው ነው፡፡ ስብከት የድምፅ ግርማ ሞገስን ብቻ መሠረት ያደረገ የጋዜጠኛነት ሙያ አይደለም፡፡ ስለዚህ የንግግር
ግርማ ሞገስ ያላቸው የተሐድሶ መናፍቃን ጋዜጠኛነት መወዳደር ይችላሉ እንጅ በድምጻቸው ማማር ብቻ ተዋሕዶን ሊሰብኩ አይችሉም፡፡
ስብከት በተግባር የሚኖሩት ሕይወት እንጅ እንደ ጋዜጠኛ መናገር ብቻ አይደለምና፡፡
በጣም ይመቸኛል
“እገሌ እና እገሊት ሲዘምሩ ድምጻቸው በጣም ይመቸኛል” የሚሉ በርካታ ደጋፊዎች በዝተዋል፡፡ እነዚህ ሰዎች በመዝሙሩ ውስጥ
ምን መልእክት እንደተላለፈ አልተረዱም፡፡ እነርሱ የተማረኩት በዘማሪዎች የድምጽ ማማር ብቻ ነው፡፡የድምጽ ማማርን የሚደግፉ ሰዎች
ደግሞ ዘፋኞችንም የሚደግፉ በመሆናቸው መዝሙርና ዘፈን የተቀላቀለባቸው በመሆናቸው “ድምጻቸው ይመቸኛል” ከማለት የዘለለ ሌላ የሚደግፉበት ቃል የላቸውም፡፡ ስለዚህ መዝሙርን በዘማሪዎች ድምጽ
ማማር ብቻ ሳይሆን በውስጡ ባለው መልእክትና በዜማው የቤተክርስቲያናችን መሆን አለመሆኑን ልንገነዘበው ያስፈልጋል፡፡
የመናፍቃን እውርነት!
የመናፍቃን እውርነት!

እውርነትን በ2 ከፍለን ልንመለከተው
እንችላለን፡፡ ይኸውም፡- የዓይንና የልብ እውርነት በማለት ነው፡፡ በጣም አስቸጋሪውና ብዙዎችን ለጉዳት የዳረጋቸው የልብ እውርነት
ነው:: “ልብ ካላየ ዓይን አያይም” እንዲሉ በልባቸው መታወር ምክንያት ዓይናቸው የሚያየውን እጃቸው
የሚዳስሰውን ሁሉ ማየት መጨበጥ የተሳናቸው ብዙዎች ናቸው፡፡ ለምሳሌ፡- ድንግል ማርያም አታማልድም ምክንያቱም መጽሐፍ ውስጥ ታማልዳለች
የሚል ጥቅስ የለምና ብለው በድንቁርና ማስረጃ ይሞግታሉ:: ልብ ካላችሁ ስሙኝ ልጠይቃችሁ መልሱልኝ::
1ኛ. መጽሐፍ ቅዱስ የተደረገውን ሁሉ
አጠቃልሎ ይዟልን? አላጠቃለለም ለዚህም ማስረጃ አለኝ ቅዱስ ዮሐንስ በመልእክቱ 2ኛ
ዮሐ 1፥12 ላይ “እንድጽፍላችሁ የምፈልገው ብዙ ነገር ሳለኝ በወረቀትና በቀለም ልጽፈው አልወድም ዳሩ ግን ደስታችሁ ፍጹም እንዲሆን
ወደ እናንተ ልመጣ አፍ ለአፍም ልናገራችሁ ተስፋ አደርጋለሁ” ይላል፡፡ እንዲሁም በ 3ኛ ዮሐ1÷13 ላይም “ልጽፈው የምፈልገው ብዙ ነገር ነበር ዳሩ ግን በቀለምና በብርዕ ልጽፈው አልወድም” ይላል:: ይህ ሐዋርያ ድንግልን በመስቀሉ
ሥር የተቀበለ ነው:: /ዮሐ19÷27/ ስለድንግል አማላጅነት በይበልጥ የሚያውቀው ቅዱስ ዮሐንስ ነው:: ምክንያቱም እነኋት እናትህ ተብላ በእናትነት የተሰጠችው ለእርሱ ነውና፡፡ እኛም እናታችን የምንላት
በዮሐንስ በኩል ለሁላችንም የተሰጠችን ስለሆነ ነው፡፡ ዮሐ
21፥25 ላይ እንዲህ ይላል “ኢየሱስም ያደረገው ብዙ ሌላ ነገር ደግሞ አለ ኹሉ በእያንዳንዱ ቢጻፍ ለተጻፉት መጻሕፍት ዓለም ራሱ
ባልበቃቸውም ይመስለኛል” ይላል ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ ሁሉንም ድርጊት በሙሉ አላሰፈረልንም ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ትውፊትም ያስፈልጋል
ማለት ነው፡፡ አንዱ ለአንዱ ማለትም አባት ለልጁ ለልጅ ልጁ በቃል ያወረሰው ትምህርት አለ፡፡ ለምሳሌ ያህል በዘፍጥረት ላይ እግዚአብሔር
አዳምን በአርአያውና በአምሳሉ እንደፈጠረው ይናገራል፡፡ ከዚያም ከግራ ጎኑ ደግሞ ሔዋንን እንደፈጠረለት ይናገራል፡፡ ከዚያ በኋላ
አዳም ሔዋንን አወቃትና ቃየን ተወለደ፡፡ በመቀጠልም አቤል ተወለደ፡፡ ከዚያም ቃየን አቤልን ገደለው አዳምም ሔዋንን አወቃትና ሴት
ተወለደ፡፡ ከዚያ በኋላ ሴት ሄኖስ የተባለ ልጅን ወለደ፡፡ መናፍቃን እዚህ ላይ ይቆማሉ እንግዲህ ሴት ማን የምትባል ሴት አግብቶ
ነው ልጅ የወለደ? እንደመጽሐፍ ቅዱስ ገለጻ ከሆነ በዚያን ወቅት ያለችው ብቸኛ ሴት እናቱ ሔዋን ብቻ
ነበረች፡፡ እስከዚህ ዘመን ድረስ በሕይወት መኖር አለመኖሯ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ባይገለጥም ማለት ነው፡፡ እስደ መጽሐፉ ግን
እስከዚህ ዘመን ድረስ የተገለጠችው ሴት እሷ ብቻ ናት፡፡ ታዲያ ልጇ ሴት ከሔዋን ልጅ ወለደ ልትሉን ነውን? በፍጹም
አንቀበላችሁም፡፡ እኛ ብዙ ማስረጃዎችን በትውፊትም በመጽሐፍም እናቀርባለን፡፡ ይህንን በሚገባ የሚያብራራልን የቅዱስ ጴጥሮስ
ደቀመዝሙር እንደሆነ የሚናገረው ቀሌምንጦስ በጻፈው መጽሐፈ ቀሌምንጦስ ነው፡፡ ይህንን መጽሐፍ መናፍቃኑ አይቀበሉትም፡፡ ወደ
ቀደመ ነገራችን እንመለስና ምልጃዋንም በዮሐ2 ላይ የቃና ዘገሊላውን የመጀመሪያ ተአምር ልብ ይሏል:: መናፍቃን ይህንንም በእውርነት ያጣምሙታል “እርሱን ስሙት” ብላለችና “ኢየሱስን ብቻ ነው የምንሰማ” ይላሉ:: ወይን ማለቁን ማን ነገራት? መናፍቃን ሆይ እንደፈረስ ላይ ላዩን ሳትጋልቡ ከፊትና ከኋላ የተጻፈውን ነገር ሁሉ ተረጋግታችሁ በማስተዋል አንብቡ:: ይህ ቃል የመስማማት ነው:: ወይን ስላለቀባቸው ወይን እንዲሰጣቸው ልጇን ጠየቀች “ከአንች ጋር ምን ጠብ ምን ክርክር አለኝ ጊዜየ ገና አልደረሰምና”
አላት:: ይህ ስለብዙ ነገር ተነግሯል ሰፊ ሐተታ አለው፡፡ በቀላሉ
ለማየት ያህል፡-
v ጊዜየ ገና አልደረሰም ማለቱ፡-
1.
ይህን ተአምር የማደርግበት ጊዜ ገና ነው ምክንያቱም
በማድጋው ያለው ወይን ሙሉ በሙሉ አላለቀም ነበርና፡፡ ሳያልቅ ተአምሩን ቢያደርግ ውሃውን ወይን አደረገ ሳይሆን ጥቂቱን ወይን
አበረከተው ይባል ነበርና፣
2.
በወቅቱ ይሁዳ የለም ነበርና ውሃውን ወይን ሲያደርግ
ተአምሩን ባይመለከት ኖሮ እርሱ ተአምሩን ከሌሎች ሐዋርያት ለይቶ ስለከፈለብኝ እኔም ለአይሁዳውያን አሳይዝኩት ብሎ ምክንያት
ይኖረው ነበርና ምክንያ እንዳይኖረው ይሁዳ እስኪመጣ ድረስ ለመጠበቅ፤
3.
እግዚአብሔር ለሥራው ሁሉ ጊዜ እንዳለው ለማጠየቅ፣
4.
ዓለምን የማድንበት በመስቀል የምሰቀልበት ጊዜ ገና
አልደረሰም ለማለት ነው፡፡
ከዚህ በሗላ ነው እንግዲህ ጊዜው
ሲደርስ “እርሱን ስሙት የሚላችሁን አድርጉ” ያለቸው:: እናትና ልጅ ተስማሙ ምልጃዋ ሠራ ዶኪማስ ከማፈር ዳነ:: አንድ መናፍቅ “ድንግል ማርያም ታማልዳለች የሚል
ጥቅስ ከመጽሐፍ ቅዱስ አጣሁ” አለኝ እኔም “ዓይን ያላቸውን ጠይቅ ያሳዩሃል”
አልኩት:: ለምን እንደዚህ መለስክለት አትሉኝም መቼም ምክንያቱም የማየትና ያለማየት የማስተዋልና ያለማስተዋል
ጉዳይ እንጅ ጥቅስ ጠፍቶ አይደለም፡፡ ድንግል ማርያም በሉቃስ ወንጌል ሉቃ 1:48 ላይ “ትውልድ ሁሉ ያመሰግኑኛል” አለች:: ትውልድ የሚባለው ከ 3ቱ አይወጣም ትውልደ ሴም፣ ትውልደ
ካምና ትውልደ ያፌት ናቸው፡፡ እነዚህ ሁሉ ብጽእት እያሉ በአማላጅነቷ አምነው ይማጸኗታል ያመሰግኗታል ማለት ነው:: ድንግል ማርያም በትውልደ ሴም፣ በትውልደ ካምና በትውልደ ያፌት ብጽእት ተብላ
የምትመሰገን ናት ማለት ነው፡፡ ታዲያ የዛሬ መናፍቃን ትውልዳቸው ከየት ይሆን ምልጃዋን አንቀበልም ብጽእት አንላትም ያሉት? የሰው ልጅ የድንግልን እናትናትና አማላጅነት ቢክድ ኖሮ ዶኪማስ በቃናው
ሠርግ ልጇን ብቻ በጠራ ነበር ግን አላደረገውም:: አያችሁ ዶኪማስ ሲያከብራት:: በሉቃስ ወንጌል እንደተጻፈው መልአኩ ገብርኤል በመፍራት አምላክን
እንደምትወልድ አበሰራት:: አያችሁ የሰማይ መላእክት እንኳ ሲያከብሯት:: ኢየሱስ የተገኘው ከድንግል ማርያም ሥጋ ነው:: ኢየሱስ ክርስቶስን ያወቅነው በድንግል ማርያም ነው:: ድንግል ባትኖር ኖሮ ኢየሱስን ሥጋ ለብሶ ማየት አንችልም
ነበር :: ለዓለም መዳን ምክንያት እመብርሃን ናት:: ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ጥሬ ቃል አሳዩን የምትሉ መናፍቃን
በእርግጠኝነት ቃሉን አላጣችሁትም እውርነት ጎድቷችሁ ካልሆነ በቀር:: የጻድቅ መታሰቢያ ለዘላለም ይኖራል:: መዝ111÷6 እንግዲህ ለዘላለም ማለት እስከ መቼ እንደሆነ አስቡት:: እስከ ዓለም ፍጻሜ አይደለም ከዚያም በኋላ ጭምር እንጅ:: ድንግልንም ለዘላለም እናከብራታለን አማልጅን እንላታለን:: ምክንያቱም ቅድስት
ናትና መታሰቢያዋም ለዘላለም ነውና አምላክ ለእናትነት አክብሯታልና፡፡ አንድን ነገር ስታከብሩ የራሳችሁ
መስፈርት ይኖራችኋል ድንግል ማርያምን ስናከብር ግን የአምላክ እናት የዓለም መዳኛ ብለን ነው:: አማላጅ ጌታ ሳይሆን ተማላጅ አምላክን አስገኝታለችና እናመሰግናታለን
ከፍ ከፍም እናደርጋታለን:: ክብር ምስጋና ይግባውና ኢየሱስ
ክርስቶስ በሥጋ ማርያም ቢገለጥ ከባሕርይ አባቱ ከአብ ከባሕርይ ሕይወቱ መንፈስ ቅዱስ አላነሰም አልበለጠምም እኩል ነው እንጅ:: በሥጋዌው ወራት ሕዝቡን ከራሱ ጋር አስታርቋል አማለደ የምንለውም ከራሱ ጋር እንታረቅ ዘንድ ያደረገውን የቤዛነት ሥራ ነው፡፡ ያን የቤዛነት ሥራውን ያደረገልን ወድዶ ፈቅዶ ነውና እኛን
ለማዳን ወደደ ፈቀደ ብለን እንተረጉመዋለን:: አሁን ግን “ይማልዳል” ማለት ፍጹም ስህተት ነው:: መናፍቃን እንደ ጥያቄ የሚጠይቁት እንደመልስም የሚመልሱት እንደመከራከሪያም
የሚከራከሩበት ብቸኛ ጥቅስ ሮሜ 8÷34 “ስለእኛ የሚማልደው” የሚለው ነው፡፡ በዚህ ጥቅስ መነሻነት ኢየሱስ ክርስቶስ አሁንም ይማልዳል ይላሉ:: ቃሉ “ስለእኛ የሚፈርደው” የሚል ነው ቅርብ ጊዜ በታተሙት ላይ ግን “ስለእኛ የሚማልደው” ተብሎ ተቀይሮ ተጽፏል:: ለመቀየሩ ማረጋገጫ ቁጥር 33 ላይ ስንመለከት “የሚያጸድቅ እግዚአብሔር ነው የሚኮንንስ ማን ነው?” ይላል፡፡ ይህ ማለት አንተ ገነት ግባ ብሎ የሚያጸድቅ፤አንተ
ሲዖል ግባ ብሎ የሚኮንን እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ይህን የመጨረሻ ፍርድ
የሚሰጠው ደግሞ አምላክ ወይም ፈጣሪ እንጅ ፍጡር /አማላጅ/
አይደለም፡፡ ይህ አያሳምንም የሚል ካለ ደግሞ ለምን ወልድ ብቻ አማላጃችን ነው እንለዋለን
አብና መንፈስ ቅዱስስ አያማልዱንምን? እስኪ ጥሬ ቃላትን እንመልከት?
v ሮሜ 8÷26 “ነገር ግን መንፈስ ራሱ በማይነገር መቃተት ይማልድልናል” ይላል፡፡ ስለዚህ በዚህ ጥቅስ መሠረት መንፈስ ቅዱስም ይማልዳል ማለት ነው::
ኤር 7÷25 “አባቶቻችሁ ከግብጽ ምድር ከወጡበት ቀን ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ በየዕለቱ እየማለድሁ ባሪያዎቼን ነቢያትን ልኬባቸችሁ ነበር” ይላል፡፡ እዚህ ጥቅስ ላይ እግዚአብሔር የሚለው እግዚአብሔር አብን ነው፡፡ በኦሪት እንዲህ እንደአሁኑ በግልጥ
ሦስትነታቸው አይታወቅም ነበርና፡፡ ሦስትነትና አንድነት በሚገባ የታወቀው ኢየሱስ ክርስቶስ ከድንግል ማርያም ከተወለደ በኋላ
ነውና፡፡ በዚህ ጥቅስም መሠረት እግዚአብሔር አብ ይማልዳል ማለት ነው፡፡ ታዲያ አብ አማላጅ፣ ወልድም አማላጅ፣መንፈስ ቅዱስም
እንዲሁ አማላጅ ከተባሉ አምላካችን ማን ሊሆን ነው? የሚማለደው ማን ነው ልንል ነው? መናፍቃን ሆይ ልብ በሉ አስተውሉ ዝም ብላችሁ ቀንጭባችሁ አትከራከሩ፡፡ በርግጥ አንዴ ልባችሁ ስለጨለመባችሁ አሁንም ትከራከሩ ይሆናል:: ነገር ግን ትክክለኛና አሳማኝ
የሆነ ማስረጃ ማቅረብ የምትችሉበት ወኔ ያላችሁ አይመስለኝም፡፡ ስለዚህ ኢየሱስ ክርስቶስ ፈራጅ አምላክ እንጅ አማላጅ አይደለም:: ማስረጃ ካስፈለገ ሮሜ 9÷5 “ክርስቶስ በሥጋ መጣ እርሱም ከሁሉ በላይ ሆኖ ለዘላለም የተባረከ አምላክ ነው” እንዲሁም ሮሜ14÷10 ላይ “ሁላችን በክርስቶስ ፍርድ ወንበር ፊት
እንቆማለንና” ይላል ፈራጅነቱን ሲገልጥ፡፡Wednesday, 15 June 2016
gishen ena mesklu
የደቡብ
ወሎ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ፡-
ተልኮ
/Mission/
የዞኑን
ባህላዊ ፣ታሪካዊ ና የዱር እንስሳት ሀብቶች በዘላቂነት በመጠቀም የዞኑ ህዝብ ከቱሪዝም ልማት ተጠቃሚ የሚሆንበትንና ለዞኑ አጠቃላይ እድገት የላቀ አስተዋጽኦ እንድያበረክት ማስቻል፡፡
ራዕይ
/Mision/
በ2012
የመስህብ ሀብቶች የለሙበት፣ ከድህነት የተላቀቀና የህዝብ ተጠቃሚነት የተረጋገጠበት ዞን ማየት፡፡የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ባህልና ቱሪዝምን በማልማት ህብረተሰቡን ብሎም መንግስትን ተጠቃሚ ለማድረግ ተፈጥሯዊና ባህላዊ ቅርሶቻችንን በመጠበቅና በመንከባከብ ለተተኪው ትውልድ ለማስተላለፍ ያመቻል በሚል ባህልና ቱሪዝም ሴክተርን በማዋሀድ በህዳር 1998 ዓ/ም ባህልና ቱሪዝም ቢሮን በክልሉ ከሚገኙ ቢሮዎች አንዱ በማድረግ በስሩ የዞን መምሪያዎችንና የወረዳ ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤቶች በአዋጅ ቁጥር 120/1998 ዓ/ም አቋቁሞታል፡፡
በቅርስ
ጥበቃ ፣የመስህብ ሀብቶች ልማትና ፕሮሞሽን መሰረታዊ የስራ ሂደት የሚያከናውናቸው ዋናዋና ተግባራት
የዞኑ
የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ቅርሶች አሰሳ ያካሂዳል በአሰሳ የተገኙ ቅርሶች ላይ ጥናት ያካሂዳል፤ ለምተውና ተጠብቀው ለቱሪዝም ገበያ የሚውሉበትን ሁኔታ ያመቻቻል፡፡
የቱሪዝም
ክፍለ ኢኮኖሚ /sectoral/ ጥናት ያካሂዳል፤ ቅርስ ና የቱሪዝም አጠቃላይ መረጃዎችን ያሰባስባል፤ ይተነትናል፤ የኮምፒውተር data base ያደራጃል፡፡ መረጃዎችን በተለያዩ ዘደዎች ለተጠቃሚዎች ያደርሳል፡፡
የቅርስ
ጥበቃና የቱሪዝም ልማት ፕሮጀክቶችን ያዘጋጃል፤ የግንባታና የጥገና ስራወችን ይቆጣጠራል፤ የቅርስ ጥገናና የቱሪዝም ልማት ፈንድ ያሰባስባል፤ በጠቀሜታ ላይ ያውላል፤ አጠቃቀሙን ይቆጣጠራል፡፡
ማህብረሰብ
አቀፍና ድሀ ወገን /pro poor/ ቱሪዝም ያስፋፋል፡፡
የተንቀሳቃሽና
የማይንቀሳቀሱ ቅርሶች ምዝገባ ያካሂዳል፤ በቅርሶች ደህንነት የክትትልና የቁጥጥር ተግባር ያከናውናል፡፡
የዞኑን
የቱሪስት መዳረሻዎችና መስህቦች ያለማል፡፡ በተለያዩ የመገናኛ ዘደዎች ያስተዋውቃል፡፡
ያገር
ውስጥ ቱሪዝምን ያስፋፋል፡፡
ቅርሶችን
ከጉዳት ለመጠበቅ በሳይንሳዊ ሁኔታ ጠብቆ ለመጭው ትውልድ ለማቆየት የእንክብካቤና የጥገና ስራዎችን ይሰራል፡፡ አጠቃቀማቸውንም ይወስናል፡፡
በቱሪዝም
ዘርፍ የሙያና የስራ ፈቃድ ይሰጣል፤ ደንብና መመሪያ በማያከብሩት ላይ እርምጃ ይወስዳል፡፡
የቱሪዝም
አገልግሎቶችና መስተንግዶ ተቋማት ደረጃ ያጠናል፤ ደረጃ ይሰጣል፡፡
ለቱሪስት
አገልግሎት ሰጭ ተቀቋማት የሙያ ድጋፍና ስልጠና ይሰጣል ፤
12. በዞኑ የጉዞና
የጉብኝት ስረአት ያዳብራል፤ ኢትዮጵያዊ የመስተንግዶ ባህል እንድዳብር የበኩሉን ጥረት ያደርጋል፡፡
እሴቶች
ሀብትን
በቁጠባ መጠቀም ባህላችን እናደርጋለን፤
የሙያችን
መለያ የተገልጋይ እርካታ ነው፡፡
ለአካባቢው
ህብረተሰብ ተጠቃሚነት ቅድሚያ እንሰጣለን፡፡
የሙያ
ፍቅር ታታሪነት ውጤታማነት መገለጫችን ነው፡፡
እንግዳ
ተቀባይነት፣ ህብረተሰባዊነትእና አብሮነትን እናሰፍናለን፡፡
ለስረአተ-ጾታና ለወታጣቶች ትኩረት እንሰጣለን የዞኑን ቁሳዊ እና መንፈሳዊ ባህል እንጠብቃለን፡፡
ማ
ዉ ጫ
ርዕስ
ገጽ
መግቢያ...............................................................1
ቅዱስ
መስቀሉ ከጎለጎታ
እስከ
ግሸን ደብረ-ከርቤ..........................................1
የቅድስት
እሌኒ ምንነት.............................................2-4
የቅድስት
እሌኒ ወደ እየሩሳለም መገጓዝ
.......................5-7
የቅዱስ
መስቀሉ ወደ ኢትዮጵያ መምጣት....................7-9
ግሸን
ደብረከርቤ....................................................9-10
የሊቀ
ጳጳሳቱ የጋራ ቃለ ምእዳንና ውግዘት....................10
የግሸን
ደብረ ከርቤ ቃል ኪዳን....................................11
የግሸን
ደብረከርቤ ታሪካዊ ቦታዎች
.............................11-15
የግሸን
ማርያም ጉዞዬ ልዩልዩ ግጥሞች..........................15-17
የደመራ
በአል መቸ ተጀመረ.......................................18
የግሸን
ደብረ ከርቤ መሰረተ ልማት
.............................19-20
ዋቢ
መጽሐፍት
የአለም
የቱዝም ስነ-ምግባር መርሆዎች
አድራሻ
በደቡብ
ወሎ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ
የቅርስ
ጥበቃና ቱሪዝም ልማት የስራ ሂደት
የቱሪዝም
ልማትና ፕሮሞን የስራ ዘርፍ የተዘጋጀ
ስ.ቁ 0331125127
0333110948
0331199016
ፖ.ሳ.ቁ 1474
Email swct2007@yahoo.com
መግቢያ
ኢትዬጲያ
የዓለም የጥንታዊ የስልጣኔ መነሻ የሰዉ ዘር መገኛ በመሆኑዋ እጅግ በርካታ ተፈጥሯዊ፣ ባህላዊ(ሰዉ ሰራሽ)ና ታሪካዊ የቱሪዝም ሃብቶች ባለቤት ናት፡፡ የተባበሩት መንግስታት የትምህርት ሳይንስና ባህል ድርጅት (UNESCO) ከአፍሪካ በቀዳሚነት 23 ቅርሶችን አስመዝግባለች እነሱም አብዘሃኛዎቹ ቁሳዊ ናቸዉ፡፡
አስሩ
የተፈጥሮና ሰዉ ሰራሽ ቅርሶች፡-
ከአማራ
ክልል 4ቱ የሰሜን ተራሮች፣ የላሊበላ ዉቅር አብያተ ክርስቲያን፣ የፋሲል አብያተ ቤተ-መንግስት እና የጣና ሃይቅ እና አካባቢዉ
ከደቡብ
ክልል የጢያ ትክል ድንጋይ፣ የታችኛዉ ኦሞ ወንዝ እና የኮንሶ ባህላዊ የመሬት አቀማመጥ
ከትግራይ
ክልል የአክሱም ሃዉልት
ከሀረር
ክልል የጀጎል ግንብ
አፋር
ክልል የታችናዉ የአዋሽ ወንዝ እንዲሁም
12ቱ
የስነ-ጽሁፍና የመዛግብት ሰነዶች፡-
አርባቱ
ወንጌል በ14ኛ ክ/ዘመን፣ የሃዋሪያዉ ጳዉሎስ መልዕክት በ15ኛዉ ክፍለ ዘመን፣ ግብረ ህመማት በ15ኛዉ ክፍለ ዘመን፣ መጽሃፈ ሄኖክ በ15ኛዉ ክፍለ ዘመን፣ መዝሙረ ዳዊት በ16ኛዉ ክፍለ ዘመን፣ የቅዳሴ መጽሃፍት 17ኛዉ ክፍለ ዘመን፣ ፍትሃ ነገስት በ19ኛዉ ክፍለ ዘመን፣ የዳግማዊ አፄ ምንሊክ ታሪክ በ19ኛዉ ክፍለ ዘመን፣ ታሪከ ነገስት በ20ኛው ክፍለ ዘመን ፣የሸዋው ንጉስ ሳህለ ስላሴ ለእንግሊዝ ንግስት የጻፉት ደብዳቤ፣ አፄ ቴዎድሮስ ለእንግሊዟ ንግስት ቪክቶሪያ 19ኛው ክፍለዘመን እና አፄ ምንሊክ ለሞስኮዉ ንጉስ ኒኮላስ ቄሳር 2ኛ በ20ኛዉ ክፍለ ዘመን የጻፉዋቸው ደብዳቤዎች ናቸዉ፡፡
ከቅርብ
ጊዜ ወዲህ ዓለም ለማይዳሰሱ ቅርሶች ትኩረት በመስጠቱ ከበርካታ የህሌናዊ ቅርሶች ወይም ባህላዊ ረቂቅ ቅርስ የመስቀል ክብረ በዓል ብቻ ተመዝግቧል፡፡ ወደፊትም ለማስመዝገብ በጥናት ላይ እንገኛለን፡፡
እነዚህ
ዓለም አቀፋዊ ቅርሶች ባሉበት የሃገሪቱ ክፍሎች በርካታ የዉጭ አገር ቱሪስቶች ይመጣሉ፡፡ ይህን አጋጣሚ በመጠቀም የቱሪስቶቹን የጊዜ ቆይታ ለመጨመር ሌሎች የቱሪዝም ኃብቶችን የማልማትና የማስተዋወቅ ስራ እየተሰራ ነዉ፡፡
ደቡብ
ወሎ እስካሁን በዓለም የሳይንስ ትምህርት ባህልና ታሪክ ድርጅት የተመዘገበ ቅርስ ባለመኖሩ የዉጭ አገር ቱሪስቱ የጎላ አልነበረም፡፡ አሁን ግን የመስቀል በዓል በዓለም መመዝገቡ ለዞኑ ትልቅ ተስፋ ነዉ፡፡ ምክንያቱም የቅዱስ መስቀሉ መገኛ በዞኑ በአምባሰል ወረዳ ግሸን ደብረ ከርቤ በመሆኑ ግሸን ደብረ ከርቤ እና የመስቀል በዓል የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች በመሆናቸዉ የመስቀል በዓልን ለመጎብኘት የመጣ ቱሪስት ቅዱስ መስቀሉን (True cross) ያለበትን ግሸንን ሳይጎበኝና በረከቱን ሳያገኝ መሄድ የመስቀልን ኃይልና ታሪክ መካነ መስቀሉን ሙሉ ታሪክ ሳያዉቁ ሳይባረኩ መቅረት ነዉ፡፡
ስለዚህ
ከጭስ አልባዉ ኢንዱስትሪ ተጠቃሚ ለመሆን የቱሪዝም ኃብቶችን ማልማትና ማስተዋወቅ አብይ ተግባር በመሆኑ የመስቀልና የግሸን ደብረ ከርቤን ክብረ በዓላት ምክንያት በማድረግ የማስተዋወቅ ስራ ለመስራት ይህ ብሮሸር ተዘጋጅቷል፡፡
ቅዱስ
መስቀሉ ከጎለጎታ እስከ ግሸን ደብረ ከርቤ
ቅዱስ
መስቀሉን የቀበሩት የት ነበር? ማንስ ፈልጎ አገኘዉ? መቼስ ተገኘ? ከዚያስ ወደ ኢትዬጵያ በማን፣ እንዴት መጣ? አሁንስ የት ይገኛል? የመስቀል በዓል መከበር ምክንያት ምንድን ነዉ? መቼስ መከበር ተጀመረ? የሚሉትንና የግሸን ደብረ ከርቤ አጭር ታሪክ በዚህ ጽሁፍ ይገኙበታል፡፡
ጌታችን
መድሃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ዓለምን ለማዳን ሲል በመስቀል ተሰቅሎ፣ ሞቶ፣ ተቀብሮ በሶስተኛዉ ቀን ከሙታን ተለይቶ በተነሳ በአርባኛዉ ቀን ካረገ በኋላ፣ ተሰቅሎበት የነበረዉ የእንጨት መስቀል ተአምራት እያሳየ ሙት እያስነሳ አይሁድን ስላበሳጫቸዉ መስቀሉን በማይገኝበት ዘዴ ቀብረዉት ነበር፡፡
የጌታችን
የእየሱስ ክርስቶስ የመስቀል ፍቅር በክርስትና እምነት ተከታዮች ህሊና ዉስጥ አለ፡፡ ምክንያቱም ድህነት የተገኘዉ በእየሱስ ክርስቶስ መስቀል (መሰቀል) መሆኑን ስለምናምን በመስቀል ስም ቤተ-ክርስቲያን ሰርተን በዓለ ንግስ እናደርጋለን፡፡ ስሞችም ገብረ መስቀል ወልደ መስቀል ተብሎ ይሰየማል፤ ይጠራል፡፡ በአንገታችን እናደርገዋለን፤ በሰዉነታችን እንነቀሰዋለን፤ በአልባሳታችን እንጠልፈዋለን፤ እንሳለመዋለን፤ ከምግብ በፊትና በኋላ፣ ከጸሎት በፊትና በኋላ እናማትባለን፤ በቤተ-ክርስቲያን ጉልላት እንጠቀመዋለን፤ በተለይ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዬች ከሌሎች የክርስትና ሃይማኖት በላቀ የጠበቀ ክብር ትዉፊት አለዉ፡፡
መስቀሉም
በኢትዬጵያ ላይ በእምነታቸዉ ዋጋ ለመስጠት ተአምር በመስራት ላይ ይገኛል፡፡ ለምሳሌ ያህል በአክሱም ጽዬን ከጽላት ቤት የሚገኘዉ‹‹ነባኢት መስቀል›› እየተባለ በሴት የሚጠራዉ መስቀል እፁብ ድንቅ ተዓምር በመስራት ላይ ይገኛል፡፡ እንዲህም ትግራይ በአብረሃ ወኢብሉ ዉቅር ቤተ-መቅደስ የሚገኘዉ 25 ኪሎ ግራም የሚመዝነዉ መፆር መስቀል በየዓመቱ ጥቅምት 4 ቀን በበዓለ ንግሱ ዕለት ዲያቆኑ ‹‹ፀልዩ በእንተ ወንጌል›› ብሎ ወጥቶ ምስባክ በሚሰብክበት ዕለት መስቀሉ ማንባት ይጀምራል፤ በዚህ የተነሳም መስቀሉ ‹‹አንብር መስቀል›› በመባል ይጠራል፡፡
በቅዱስ
ላሊበላ ቤተ-መቅደስ የሚገኘዉና 8 ኪሎ ግራም የሚመዝነዉ የወርቅ መስቀል ከገባሬ ተአምራቱ የተነሳ ደግሞ ‹‹አፍሮ አይገባ›› በሚል ቅጽል የሚጠራዉ አንዱ ማስረጃ ነዉ፡፡ ለግንዛቤ ያህል እነዚህን ጠቀስን እንጂ በተለያዩ አድባራትና ገዳማት የሚገኙ ገቢረ
ተአምራቸዉ
የበዛ ክቡራን መስቀሎች አሉ፡፡ ስለዚህ መስቀል የድህነታችን አርማ በመሆኑ ከልብ እናከብረዋለን፡፡ አምላካችን በኃይለ መስቀሉ ይጠብቀን አሜን፡፡
በተለይ
በኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዬች መስቀል፣ ኃይላችን፣ መድሃኒታችን፣ ጉልበታችን፣ መመኪያችን፣ የክርስቲያን አርማ ወይም ሰንደቅ ዓላማ በአጠቃላይ በእለተ አርብ በመስቀል ላይ መከራን የተቀበለዉ የክርስቶስ ስጋና የፈሰሰዉ ደሙ ዓለምን ከመርገመ ስጋና ከመርገመ ነፍስ አድኗል፡፡
የጌታችን
ኢየሱስ ክርስቶስ ጠላቶች የሆኑ አይሁድም አዳኝነቱን ክደዉ በምቀኝነትም ተገፋፍተዉ የጌታ እግሮቹና እጆቹ የተቸነገሩበትን፣ ሰዉነቱ ተሰቅሎ የዋለበትን፣ ክቡር ደሙ የፈሰሰበትን ቅዱስ መስቀል እንደ አልባሌ ተራ ዕቃ የትም ጥለዉት በቀራኒዬ አደባባይ ለ3 ዓመት ህል ቆይቶ ሳለ ያ መለኮትን ተሸክሞ የነበረዉ መስቀል ልዩ ልዩ ተአምራትን እያሳየ በማየታቸዉ አምነዉ ለመዳን ከመሞከር ይልቅ በስህተታቸዉ ገፉበት፡፡ ክርስቶስ በህይወት ሳለ ያሳየዉ ተዓምራት ያስከተለብን ዉርደት አንሶ ዛሬ ደግሞ ይህ እንጨት ህሙማንን በመፈወስ፣ ሙታንን በማስነሳት ያስቸግር ጀመር? በማለት በጎለጎታ ጉድጓድ ቆፍረዉ መስቀሉን በመቅበር በይሁዳ ምድር ያለ ነዋሪ ሁሉ የቤቱን ጥራጊ በዚህ መስቀሉ በተቀበረበት ጉድጓድ ላይ እንዲያፈስ አዋጅ አስነግረዉ የተከመረዉ ቆሻሻ እንደከፍተኛ ተራራ ያህል ሆነ፡፡ ክቡር መስቀሉም ለ297 ዓመት ያህል ተቀብሮ ዱካዉ እንዲጠፋ ተደረገ፡፡
የቅድስት
እሌኒ ምንነት
ቅድስት
እሌኒ ግሪካዊ ስትሆን የስሟ ትርጉም ‹‹ከባህር ወደ የብስ የመጣች ማለት ነዉ›› በኑሮዋም ባለፀጋ በትዳሯም ታማኝና መልከ መልካም የቤት እመቤት ነበረች፡፡ ባለቤትዋ ተርቢኖስም ጎበዝ ነጋዴ ነበርና ከጓደኞቹ ጋር በሃገራቸዉ ባህል ሁለት ዓመት ሶስት ዓመት ነግደዉ መምጣት ልማድ ስለሆነ ባህር አቋርጠዉ የብስ ረግጠዉ ብዙ አትርፈዉ ይመጡ ነበር፡፡ እንደተለመደዉ ይህን ንግድ ለማከናወን ሂደዉ ወደ ሃገራቸዉ ሲመለሱ ብዙ የባህር ጉዞ ነበርና ከመካከላቸዉ አንደኛዉ ‹‹እንግዲህ ባህሩን ጨርሰን የብስ ረገጥን ሚስቶቻችን ሳያገቡ በሰላም ቢቆዬን ጥሩ ነዉ፡፡›› አለ፡፡ ተርቢኖስ ግን ‹‹የአንተን አላዉቅም የኔ ሚስት ግን ታማኝ ነች እኔን ትጠብቀኛለች›› አለዉ፡፡ ነጋዴዉም በተርቢኖስ ንግግር ተበሳጭቶ ‹‹ሚስትህን እኔ አዉቂያት ብመጣ ምን ትከፍለኛለህ›› አለዉ፡፡ ተርቢኖስም ‹‹ሶስት ዓመት የለፋሁበትን ወረቴን (ንግዴን) እሰጥሃለሁ›› አለዉ፡፡ በዚህም ምክንያት ነጋዴዎች ምስክር ሁነዉ ከተርቢኖስ ጋር በባህሩ ዳር ቆዩ ያ ክፉ ነጋዴ ወደ መንደሩ ሄዶ የተርቢኖስን ቤት አንኳኳ የእሌኒም ቤት አገልጋይ " ማነዉ?"
አለች፡፡
ነጋዴዉም ‹‹እሌኒን ፈልጌ ነዉ›› አላት፡፡ እሷም ‹‹የእኔ እመቤት ከባልዋ ዉጭ ሰዉ ጠርቷት ወጥታ አታዉቅም››አለችዉ፡፡
‹‹ብዙ
ወርቅ እሰጥሻለሁ ባለፀጋ ትሆኛለሽ ተርቢኖስና እሌኒ ብቻ የሚተዋወቁበትን አንድ ምልክት ስጭኝ›› አላት፡፡ አገልጋይዋም መልሳ ‹‹ሁለቱ በአንድ ጎን የእሱ ፎቶ በአንድ ጎን ደግሞ የእሷ ፎቶ ያለበት ከወርቅ የተሰራ የአንገት ሀብል ብቻ ነዉ እሱንም ከአንገቷ አድርጋዋለች›› አለችዉ፡፡ ነጋዴዉም ክፉ ነበርና ‹‹እሱማ ጥሩ ነዉ ግቢና ነጋድያን መጡ የብስ ረገጡ ሰዉነትሽን ታጠቢ ብለሺ ስታወልቀዉ አምጥተሸ ስጪኝ›› አላት፡፡
ነጋዲያን
ከንግድ ሲመለሱ የነጋዲያን ሚስቶች ደግሞ ታጥበዉ፣ ልብስ ቀይረዉ፣ ታጥነዉ፣ ሽቶ ተቀብተዉ መጠበቅ በሃገራቸዉ ልማድ ነዉና የእሌኒ አገልጋይ ገብታ እሜቴ ሆይ፡- ‹‹ነጋዲያን መጡ የብስ ዕረገጡ የነጋድያን ሚስቶች ተከናወኑ እየተባለ አዋጅ ይነገራል ሰዉነትሽን ታጠቢ›› አለቻት፡፡ እሌኒም እሽ ብላ ወርቋን አዉልቃ አስቀምጣ በአትክልቱ ስፍራ ለመታጠብ ስትገባ አገልጋይዋ ደብቃ አዉጥታ ለነጋዴዉ ሰጠችዉ፡፡ ነጋዴዉም እየተደሰተ ወደ ተርቢኖስ ሄዶ ‹‹አዉቂያት መጣሁ›› አለዉ፤ ተርቢኖስም ‹‹ምልክቱስ ምንድን ነዉ?››አለዉ፡፡ ነጋዴዉም ይኸዉ የገዛህላት የአንገት መስቀል ብሎ አሳየዉ፡፡ ተርቢኖስም እጅግ አዝኖ በነጋዴዎች ፊት ሶስት ዓመት የለፋበትን ወርቅ ሰጥቶ የሚስቱን ወርቅ ተቀብሎ ወደ ቤቱ ሆደ፡፡ ሲደርስም ታማኝ ሚስቱ እሌኒ ልትቀበለዉ ወጣች፡፡ ልትስመዉም ስትል አትንኪኝ አላት፡፡ ‹‹ምነዉ?ምን ሆነሐል?››አለችዉ፡፡ ‹‹ሶስት ዓመት የለፋሁበት ወረቴን (ወርቁን) ዉሃ በላዉ››አላት፡፡ እሷም አይዞህ ከዘመዶቻችን አምጥተን እንበላለን አለችዉ፡፡ በተከበርኩበት አገር ተዋርጄ ባገኘሁበትም አገር አጥቼ አልኖርም ብሎ ወደ ሌላ ሀገር እሔዳለሁ ብሎ ቢነሳ እሷም አብሬህ እሄዳለሁ ብላ ተነሳች፡፡ ተርቢኖስም ትልቅ ሳጥን አሰርቶ ከሚስቱ ጋር በባህር ጉዞ ጀመረ፡፡ ከብዙ ጉዞ በኋላ የአንገቷን ወርቅ ከኪሱ አዉጥቶ ይህንን ወርቅ ለማን ሰጥተሽዉ ነበር? አላት እሷም " ነጋድያን መጡ ሲባል ልታጠብ አዉልቄዉ ጠፍቶብኝ ነዉ" አለችዉ፡፡ ለአንድ ነጋዲአልሰጠሽዉምን? አላት፡፡ ‹‹ህያዉ እግዚአብሔር ምስክሬ ነዉ›› አለችዉ ‹‹አርገሽዉም ከሆነ ስራሽ ያዉጣሽ አላረግሽዉም እንደሆነ እግዚአብሔር ያዉጣሽ›› ብሎ በያዘዉ ሳጥን ዉስጥ አስገብቶ ከባህሩ ላይ ጣላት፡፡
ባህሩም
ወስዶ ‹ብራንጥያ (ሮሃ) ከሚባል አገር አደረሳት፡፡ አሳ የሚያጠምዱ የንጉስ ቁንሰጣ አሽከሮች አገኝተዉ ወርቅ መስሏቸዉ ቢከፍቱት እሌኒን በህይወት አገኝዋት፡፡ አሽከሮቹም እኔ ላግባት እኔ ላግባት እያሉ ስለተጣሉባት እኛ ከምንጣላባት ለንጉስ ወስደን እንስጣት ብለዉ ወስደዉ ሰጡዋት ‹ንጉስ ቁንስጣም› በሮም የነገሰ የአህዛብ ንጉስ ነበረና የመልኳን ዉበት አይቶ ወደዳት ታሪኳንም ጠይቆ ስሟን ዕሌኒ ብሎ ጠራት ትርጓሜዉም ከባህር የወጣች ማለት ነዉ፡፡ የመጀመሪያ ስሟ ‹‹ሄለን›› ይባላል፡፡
አንዳንድ
ታሪክ፡- ንጉስ ቁንስጣ ላግባሽ ቢላት አንተ አህዛብ /አረማዊ/ ነህ እኔ ደግሞ ክርስቲያን ነኝ እንዴት ይሆናል ብትለዉ" በሃገሬ የሚያስተምረኝ እና የሚያስጠምቀኝ ካህን የለም ክርስቲያን እንዴት ልሆን እችላለሁ" አላት፡፡ እሷም እኔ አስተምርሃለሁ ብላ እጇን በምላጭ በጥታ ደሟን ከግንባሩ ላይ በትምህርተ መስቀል ቀባችዉ ስለዚህ በደሟ ተጠምቋል ይላል፡፡ ሌላዉ ግን ፡- አርባ ቀን ሰዉነት የሚያጣራ ምግብ በቤተ መንግስቱ እየመገባት ቆይቶ እሱም አህዛብ እሷም ክርስቲያን እንደሆነች አገባት ይላል፡፡
እሌኒም
ወደ ፈጣሪዋ እንድህም አለች "ጌታ ሆይ፡- ወንድ ልጅ ሠጥተኸኝ ወደ ሃገሬ የገባሁ እንደሆነ አይሁድ በምቀኝነት የቀበሩትን ቅዱስ መስቀልህን አስወጣለሁ" ብላ ተሳለች፡፡
እግዚአብሔር
ፈቃዱ ሆኖ በሶስተኛዉ ክፍለ ዘመን መጨረሻ (284 ዓ.ም)ወንድ ልጅ ወለደች፡፡ ስሙንም "ሀመልሚል" ብለዉ ጠሩት፡፡ ትርጓሜዉም፡- የአህዛብና የክርስቲያን ልጅ ማለት ነዉ፡፡
እሌኒም
ብዙ ዘመን ሳትቆይ ንጉሱን አስፈቅዳ ልጇን ይዛ ወደ ሀገሯ ተመለሰች፡፡ የክርስትና ሃይማኖትም አስተምራ አስጠመቀችዉ፡፡ ስመ ጥምቀቱም ቆስጠንጢኖስ ተባለ ትርጓሜዉም ጠላትን የሚያሸንፍ የተለየ ህብር ያለዉ ትፍህስት ማለት ነዉ፤ አባቱም ለአቅመ አዳም እንደደረሰ ስርዓተ መንግስት ተምሮ በአባቱ ሃገር ብራንጥያ (ቁስጠንጥንያ) ዉስጥ አባቱ የባታቹ መስፍን አድርጎ ሹሞ በመንግስቱ ስራ ሁሉ ስልጣን ሰጠዉ፡፡ ከሁለት አመት በኋላ አባቱ ቁንስጣ ሰለሞተ ቆስጠንጢኖስ መንግስቱን ተረከበ፡፡
እርሱም
ከመንገሱ አስቀድሞ በዚያች አገርና በሮም ዲዩቅልጥያኖስና መክሰምያኖስ የሚባሉ ጨካኝ አረመኔ ነገስታት ይገዙ ነበረ፡፡ እነርሱም አቢያተ ክርስቲያናት እንዲዘጉ አብያተ ጣኦታት እንዲታነፁና እንዲስፋፉ በማድረግ በተለይ ክርስቲያኖችን ያሰቃዩና ይገድሉ፣ አብያተ ክርስቲያናትንም ያቃጥሉና ቅዱሳት መጽሃፍትንም ያጠፉ ስለነበር ቆስጠንጢኖስ በነዚህ ነገስታት የጭካኔ ስራ እያየና እየሰማ እጅግ በጣም ያዝን ስለነበር፤ በመጨረሻ በነዚህ ነገስታት ላይ አመፀ፡፡ ብዙ ክርስቲያኖችም ከእርሱ ጋር ተጋሩ፤ በመስቀል ቅርጽ አርማም ጠላቶቹን ሁሉ እንደሚያሸንፍ በህልሙ ተገለፀለት፡፡
ንጉስ
ቆስጠንጢኖስ የወርቅ መስቀል አሰርቶ በነገሰበት ዘዉድ ላይ አደረገዉ፡፡ መኳንቱና ወታደሩን ጭፍሮቹን ሁሉ መስቀል አሰርተዉ በጦር መሳሪያቸዉ ላይ ያደርጉ ዘንድ አዘዛቸዉ፡፡ እነሱም እንደታዘዙት አደረጉ፡፡ የፈረስ እቃ በመስቀል ቅርጽ መስራት የጀመረዉ በዚህ ጊዜ ነዉ፡፡
ከዚህ
በኋላ የሮምን ክርስቲያኖች ከደረሰባቸዉ ጽኑ አገዛዝ ለመታደግ በሚያስፈራ ግርማ ሞገስ ወደ ሮም ገሰገሰ፡፡ መክስምያኖስም በበኩሉ የራሱን ሰራዊት አዘጋጅቶ ለዉጊያ ተሰለፈ፡፡ ነገር ግን በብዛት የሚበልጠዉ የመክስምያኖስ ወታደር በመስቀል አርማ የገጠመዉን ሰራዊት ሊቋቋም ባለመቻሉ ድል ሆነ፡፡ የሮም ህዝብና ሊቃዉንት ቆስጠንጢኖስ ይህን ድል ያገኘዉ በመስቀል ኃይል እንደሆነ ስለአመኑ ‹‹መስቀል መዋዔፀር››/መስቀል የጠላት ማሸነፊያ/ መስቀል የሃገራችን መዳኛ በማለት አሞገሱ፡፡
ከዚህ
በመቀጠል የመስቀልን ምልክት (አርማ) በሰንደቅ ዓላማና በጦር መሳሪያ ላይ በመሳል የህይወቱ መመሪያና የመንግስቱ አርማ በማድረግ፤ አብያተ ክርስቲያናት ይከፍቱ አብያተ ጣኦታት ይዘጉ በማለት አዋጅ አስነግሮ ቀደም ሲል ዲዩቅልጥያኖስና መክስምያኖስ አዉጥተዉት የነበረዉን አዋጅ በአዋጅ ሻረዉ ይህም አዋጅ ከታወጀበት ጊዜ ጀምሮ ለክርስቲያኖች ሰላምና ደስታ እፎይታና ጸጥታ ሆነላቸዉ፡፡
የቅድስት
እሌኒ ወደ ኢየሩሳሌም መጓዝ
ንግስት
እሌኒ ለፈጣሪዋ የገባችዉን ቃል በማሰብ ወደ ቅድስት ስፍራ እየሩሳሌም ተጉዛ የፈራረሱትን አብያተ ክርስቲያናት ለማሳደስ እና የጠፋዉን የክርስቶስ መስቀል ፍለጋ ከንጉሱ ልጇ ብዙ ገንዘብ፣ አያሌ ሰራዊት፣ መሳፍንትና መኳንት ጋር ወደ እየሩሳሌም ሄደች፡፡
ንግስት
ዕሌኒም እየሩሳሌም እንደደረሰች ለተወሰነ ጊዜ ሱባኤ ገባች ምህላም ያዘች፡፡ ይህንንም ያደረገችዉ ከ300 ዓመት በፊት የተቀበረዉን ቅዱስ መስቀል የተቀበረበትን ቦታ ለማወቅ ስለተቸገረች እግዚአብሔር አምላክ እንዲገልጽላት ለመፀለይ ነዉ፡፡
እርሷም
ሱባኤዉን ከፈፀመች በኋላ የመስቀሉ ተቃዋሚዎች የሆኑ ግለሰቦችን ስብሰባ መስቀሉ የተቀበረበትን ቦታ እንዲያሳዩዋት ጥያቄ አቀረበችላቸዉ፡፡ እነርሱ ግን የመስቀሉ የተቀበረበትን ቦታ ሊጠቁሙዋት አልቻሉም፡፡
ንግስት
እሌኒም ተስፋ ባለመቁረጥ በእየሩሳሌም ከተማ እየተዘዋወረች ቅዱሳት መካናትን በመጎብኘት ላይ ሳለች፡- ኤጲስቆዶስ አባ መቃርዩስን አገኘቻቸዉና መስቀሉ የተቀበረበትን ቦታ እንዲጠቁሙዋት ጠየቀቻቸዉ አባ መቃርዮስም የመስቀሉ ጠላቶች በትልቅ ጉድጓድ ዉስጥ ስለቀበሩትእና በእየሩሳሌም ያለዉን ቆሻሻ እያፈሰሱበት ትልቅ ተራራ ስላከለ ቦታዉ እዚህ ላይ ነዉ ብሎ መጠቆም ያስቸግራል አለ፡፡
በእየሩሳሌም
የሚኖርና የእድሜ ባለፀጋ መጠሪያ ስሙ ኪራኮስ የሚባል አዛዉንትም ወደ ንግስት ዕሌኒ ቀርቦ መስቀሉ የተቀበረዉ ቀራራዮ በሚባል ቦታ ልዩ ቀበሌዉ ጎለጎታ መሆኑን አባቴ ነግሮኛል በማለት ለንግስት ዕሌኒ ስፍራዉን አሳያት፡፡ ንግስቷ ምንም አካባቢዉን ተዘዋዉራ ብትመለከተዉ በቦታዉ ላይ አንድ ትልቅ ተራራ ከሚታየዉ ቆሻሻ ክምር አንጻር ቦታዉን በትክክል ለማወቅ አስቸጋሪ መሆኑን ተገንዝባ በአእምሮዋ ስታወጣ ስታወርድ መላኩ ቅዱስ ሚካኤል ተገለጠላትና መስቀሉን በእጣን ጢስ ታገኝዋለሽ ብሎ ነገራት፡፡ በዚህም መሰረት መስከረም አስራ ስድስት ቀን በ326 (7) ዓ.ም በጎለጎታ ላይ ደመራ አሰርታ ብዙ ዕጣን በመጨመር በችቦ ለኮሰችዉ፡፡ ደመራዉም ከተያያዘ በኋላ የዕጣኑ ጢስ በተአምራት ወደ ሰማይ ወጥቶ እንደገና ወደ መሬት በማጎንበስ መስቀሉ በተቀበረበት ስፍራ ላይ ተተክሎ ታየ፡፡
ኢትዬጵያዊ
የቤተ-ክርስቲያኑን ሊቅ ቅዱስ ያሬድ በዜማ ድርሰቱ ላይ ‹‹ዕጣን የመስቀሉን ስፍራ አመለከተ ጢስም ለቅዱስ መስቀል ሰገደ›› በማለት አያሌ የዜማ ድርሰቶችን ሊጽፍ የቻለዉ በንግስት ዕሌኒ ዘመን የተደረገዉን የመስቀል ፍለጋ መሰረት በማድረግ ነዉ፡፡
በመቀጠልም
የዕጣኑ ጢስ ያመለከታትን ቦታ ሳትዉል ሳታድር መስከረም 17 ቀን ማስቆፈር ጀመረች፡፡ ቆፋሪዎችንም በገንዘብ ቀጠረች፡፡ ለዚህም ተግባር በብዙ ሺህ የሚቆጠር ገንዘብ መደበች፡፡ ልጇ ንጉስ ቆስጠንጢኖስም የቦታዉን መገኘት እንደሰማ መጠን የሌለዉ ወርቅና ብር ለእናቱ ላከላት፡፡ ንግስቲቱም ቆፋሪዎቹ እንዳይጎዱ የቆፈሩበትን ደመወዝ በየቀኑ ማታ ማታ እንዲከፈላቸዉ ታደርግ ነበር፡፡ ቁፋሮዉ እንዲፋጠን ማበረታቻ በሚቆፈረዉ ተራራ ላይ ልጇ ከላከዉ ወርቅ በመበተን ቀድሞ ቆፍሮ የጨረሰ የደረሰበትን ወርቅ እንዲወስድ በማድረግ የዉድድር መንፈስ በመፍጠር የቁፋሮዉን ስራ በማቀላጠፍ ቅዱስ መስቀሉ ከ6 ወር በኋላ መጋቢት 10 ቀን ከተቀበረበት ጉድጓድ ወጣ፡፡ በጉድጓዱም ዉስጥ ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበትና ሁለቱ ወንበዴዎች የተሰቀሉባቸዉ ሶስት መስቀሎች በአንድ ጉድጓድ በመቀበራቸዉ ከሶስቱ መስቀሎች መካከል ጌታ የተሰቀለበት የትኛዉ መሆኑን ለማረጋገጥ ሶስቱን መስቀሎች በየተራ በሙት ላይ እንዲያኖሩትና ሙት የሚያስነሳዉ የጌታችን እየሱስ ክርስቶስ መስቀል መሆኑን ማረጋገጥ እንደሚቻል አባ መርቆርዩስ የተባሉት ጳጳስ ለንግስት ዕሌኒ ስለነገሯት በዚህ ዓይነት ዘዴ ጌታችን የተሰቀለበትን መስቀል መለየት ተቻለ፡፡
የጌታችን
እየሱስ ክርስቶስ መስቀልም ደወይ ቢያቀርቡለት ፈዉሷል፤ በመቃብር ቦታ ላይ ቢያስቀምጡት ሙት አስነስቷል፡፡ በዚህ ምክንያት በዘመኑ የነበሩት ህዝቦች ይህንን ገቢረ ተአምር ከተመለከቱ በኋላ ከደስታቸዉ ብዛት የተነሳ ችቦ አብርተዉ የአበባ ዝንጣፊ ይዘዉ እዩሀ አበባዬ በማለት ዘመሩ፡፡ በደስታም ፈነጠዙ፡፡
መስቀል
አበራ
ፍሬ
ክብርንም አፈራ እያሉ አሸበሸቡ፡፡
የጌታችን
ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል የመገኘቱ ብስራትም ከእየሩሳሌም 1124 ኪሎ ሜትር ርቃ ወደምትገኘዉና የንጉስ ቆስጠንጢኖስ መናገሻ ከተማ ወደሆነችዉ ቁስጥንጥያ ተላልፎ ለንጉሱ ደረሰዉ፡፡ የመስቀል መገኘቱ ብስራትም ለቆስጠንጢኖስ እንዲደርሰዉ የተደረገዉ ከእየሩሳሌም እስከ ቁስጥንጥንያ ከተማ ድረስ ያሉት ህዝቦች ማታ ማታ ችቦ በማብራትና የደመራ እንጨት በየቀዬዉ በማቃጠል በሚታየዉ የብርሃን ወጋገን ምልክትም ጭምር ነበር ይባላል፡፡
ይህንንም
በማስታወስ በኢትዬጵያ አገራችን በየአመቱ መስከረም 16 ቀን ማታ የደመራና የችቦ ማብራት ስነ-ስርዓት ይፈጸማል፡፡
የጌታችን
የመድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀልም ለ292 ዓመት ተቀብሮና ዱካዉ ጠፍቶ ከኖረ በኋላ በመገኘቱ ንግስት ዕሌኒ ደስታዋ ወሰን አልነበረዉም፡፡ ከደስታዋም ብዛት የተነሳ በቅዱሳት መካናት ማለትም ጌታ በተወለደበት በቤተልሄም፣ ምስጢረ ምፅአቱ በተነገረበት በደብረ ዘይት፣ በተሰቀለበትና በተቀበረበት በጎለጎታ የእመቤታችን መቃብር በነበረበት በጌቲሴማኒ ላይ አብያተ ክርስቲያናትን አሳነፀች፡፡
የቅዱስ
መስቀሉንም ቅዳሴ ቤት መስከረም 17 ቀን በ335 ዓ/ም እንዲከበር አደረጉ፡፡ ሊቀ ጳጳሳቱም በዚሁ እለት የመስቀል ቅርጽ ያለበትን ጽንሐ ይዘዉ ቅዱሳት መካናትን በመዘዋወር ባረኩ፡፡ ቅዱስ መስቀሉም በቤተ-መቅደሱ ተቀመጠ፡፡
ንግስቷም
በደስታና በሰላም ወደ ቤተ መንግስቷ ተመልሳ አረፈች፡፡ ልጇ ታላቁ ንጉስ ቆስጠንጢኖስም በተወለደ በ54 ዓመቱ የጰራቅሊጦስ ዕለት ግንቦት 22 ቀን በ337 ዓመተ ምህረት አልፏል፡፡ ቅዱስ መስቀሉም እስከ 7ኛዉ ክፍለ ዘመን በሰላም በእየሩሳሌም ተቀመጠ፡፡
ፋርስ
እየሩሳሌምን በ614 ዓ/ም ወራ ስትመዘብር ቅዱስ መስቀሉንም አብረዉ ዘረፉት፡፡ ወስደዉም በጥንቃቄ ሸሸጉት፡፡ በ628 ዓ/ም የቅድስት ቤተ-ክርስቲያን አባቶችና ተከታዩቻቸዉ ለበዛንታይን ንጉስ ህርቃል ወደ ፋርስ ዘምተህ ጠላቶቻችንን ድል አድርገህ ቅዱስ መስቀሉን አምጣልን ብለዉ ተማፀኑት፡፡ ንጉስ ህርቃልም ክርስቲያን ነበር እና ሰዉ የገደለ ሰዉ ዘመኑን ይጹም ይላል እና እንዴት እሆናለሁ አላቸዉ እነሱም መልሰዉ አንድ ሰዉ የሚኖረዉ ሰባ ቢበዛ ሰማኒያ ዘመን ነዉ(መዝ÷10) ስለዚህ እኛ ተከፋፍለን ብለዉ ተካፍለዉ ቢጾሙት ሰባት ቀን ብቻ ሆኗል፡፡
ንጉስ
ሕርቃልም በመስቀሉ መወሰድ አዝኖ ስለእርሱም እንዲጾሙና እንዲጸልዩ ምዕመናንን አዝዞ በ628 ዓ/ም ከፋርስ ንጉስ ጋር ለመዉጋት ምታ ነጋሪት ክተት ሰራዊት ተብሎ በሚያስፈራ ግርማ ተነስቶ ወደ ፋርስ ዘምቶ ከፍተኛ ጦርነት አካሂዶ ጠላትን አሸንፎ የተወሰደዉን የቤተ-ከክርስቲያን ንዋየ ቅዱሳትንና ጌታችን መድሃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበትን ቅዱስ መስቀል በልብሰ መንግስቱ አጎናጽፎ ተሸክሞ ወደ እየሩሳሌም ይዞ ሲገባ ህዝቡ በሙሉ ወጥቶ ሆ እያሉ ችቦ እያበሩ በደስታ ተቀብለዉታል፡፡ ከዚህ የተነሳም የስሙ መታሰቢያ ይሆን ዘንድ ጾመ ሕርቃል እየተባለ በየዓመቱ ከጾመ አርባ (አብይ ጾም) ጋር በመጀመሪያ ሳምንት እንዲጾም ተደረገ፡፡ የፈረሰዉንም የንግስት ዕሌኒን ቤተ መቅደስ አሰርቶ መስቀሉን በዚያዉ አስቀመጠዉ፡፡
በ638
ዓ/ም ዓረቦች እየሩሳሌምን ወረሩ፡፡ የጌታችን መስቀልም በአረማዉያን እጅ እየተማረከ ከአንዱ አገር ወደሌላዉ ሲንከራተት ቆይቷል፡፡ በአለም ላይ የሚገኙ የክርስቲያን ነገስታትም በመስቀሉ መማረክ ያዝኑና ይበሳጩ ነበር፡፡ ጦራቸዉንም አሳልፈዉ መስቀሉ ወደ ነበረበት አገር በማዝመት የመስቀል ጦርነት ያካሂዱ ነበር፡፡ ቀድሞ ወደነበረበት ወደ ኢየሩሳሌም ለማስመለስም አያሌ መስዋዕትነት ተከፍሎበታል፡፡
በመጨረሻምበ778
ዓ/ም አራቱ ክፍለ ዓለማት ለበረከት ይሆናቸዉ ዘንድ በአራቱ የመስቀሉ ክንፍ 7
በሙሻዙር
የተያያዙ ምልክቶችን (እንጨቶችን) በማንሳት ተከፋፍለዉ የወሰዱት ሲሆን በዚያን ወቅት ከሚኖሩት ጋር በሃይማኖት እየተባበሩ እንጅ በነገድ በዘር አንድ ስለሆኑ ከእስክንድሪያዉያን አባቶች ጋር በመስማማት ጌታችን መድሃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ እጆቹና እግሮቹ ተጨንክረዉ የተሰቀሉበት ቅዱስ መስቀል በሙሉ ለአፍሪካዊቷ እስክንድሪያ ተሰጥቶ በእስክንድሪያዉ ሊቀጳጳሳት በክብር ተጠብቆ ይኖር ነበር፡፡ ከጊዜ በኋላ ግን ይህ መስቀል ወደ ኢትዬጲያ መጥቶ በግሸን ደብረ ከርቤ ማርያም መስቀለኛ አምባ ላይ እንደተቀመጠ ተረጋግጧል፡፡ በሌላ በኩል ግን አንዳንድ የቤተ-ክርስቲያን አባቶች ለአፍሪካ ክፍለ ዓለም የደረሰዉ የመስቀሉ ቀኝ ክንፍ ብቻ ነዉ በሙሉ አይደለም እያሉ ቢናገሩም ይንን አነጋገር የግሸን ደብረ ከርቤ ማርያም አለዉ ሊቃዉንት አጥብቀዉ ይቃወሙታል፡፡ የደብሩ ሊቃዉንትም እዉነተኛነዉ ብለዉ የሚያምኑበት አባባል እንደዚህ በማለት ይገልፃሉ፡፡
በ778
ዓ/ም አራቱ ክፍለ አላማት (የቁስጠንጥንያ፣ አንጾክያ፣ የኤፌሶን(ሮም) እና እስክንድሪያ) ለበረከት እንዲሆናቸዉ የተካፈሉት መስቀሉን ለአራት ቦታ ላይ ለመክፈል ወይም በመቆራረጥ ሳይሆን በአራቱ የመስቀሉ ማዕዘን ላይ ተለጥፈዉ የነበሩት ምልክቶችን ብቻ በማንሳት ሶስቱ ክፍለ አላማት ሢወስዱ መስቀሉ ግን ሳይከፈል እንዳለ ለአፍሪካዊቷ እስክንድሪያ ቤተ-ክርስቲያን ዉስጥ በክብር ተጠብቆ ቆየ፡፡ አፄ ዳዊትም መስቀሉ እንዲሰጣቸዉ በጠየቁ ጊዜ የተሰጣቸዉ ሙሉዉ መስቀል ነዉ እንጂ ግማሹ አይደለም፡፡
በአሁን
ጊዜም በግሸን ደብረ ከርቤ ማርያም ደብር በእግዚአብሔር አብ ቤተ-ክርስቲያን ስር በህቡፅ ስፍራ የሚገኘዉ ሙሉዉ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት መስቀል እንጂ ግማሹ አይደለም በማለት በልበ ሙሉነት ከሚያረጋግጡት የደብረሯ ሊቃዉንት መካከልም መሪጌታ የማነ ብርሃን አዲሴ በግንባር ቀደምነት ይጠቃሳሉ፡፡ በዚያም ሆነ በዚህ የመስቀሉ ወደ ኢትዬጲያ መምጣት የተረጋገጠ ስለሆነ የአመጣጡን ታሪክ ቀጥሎ እንመልከት፡፡
ቅዱስ
መስቀሉ ወደ ኢትዬጲያ መምጣት
የመጀመሪያዉ
የኢትዬጲያ የተጸፉ የንጉስ ዜና መዋእል (ገድል) ያለዉ የንጉስ አምዴ ጽዩን በኋላ ልጅ ሰይፈ አረዕድ (ንዋየ ክርስቶስ) በ14ኛዉ ክፍለ ዘመን ነገሰ፡፡ በዚህ ዘመን በግብፅ አገር ነግሶ የነበረዉና መረዋን አልጋዴን የተባለዉ አረማዊ ንጉስ የእስክንድሪያን ሊቀጳጳስ አባ ሚካኤልን አሰራቸዉ፡፡ እነዚህም ሊቀጳጳሳት ቀደም ሲል በእስክንድሪያ ተሹመዉ ከነበሩት ሊቀነ ጳጳሳት አርባ ስምንተኛዉ ወይም 47ኛዉ/48ኛዉ/ ነዉ ይባላል፡፡ አረማዊዉም ንጉስ በቤተክርስቲያኑ ዉስጥ ያለዉን ወርቅና ብር ለእኔ መገበር አለብህ በማለት አባ ሚካኤል አሰራቸዉ፡፡
አባ
ሚካኤልም በቤተ ክርስቲያን ዉስጥ የተቀመጠዉ ወርቅ ከጥንት አባቶች ጀምሮ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ የቤተ-እግዚአብሔር ሃብት በመሆኑ ለአንተ አልሰጥም በማለታቸዉ ምክንያት ጳጳሱን አስሮ እስክንድሪያ የሚኖሩትን ክርስቲያኖች አገዛዝ አፀናባቸዉ፤ አብያተ ክርስቲያናቱም እንዲዘጉ አዘዘ፡፡
የኢትዬጵያዊ
ንጉስ አጼ ሰይፈ አርዕድም ይህን በሰማ ጊዜ ምታ ነጋሪት ክተት ሰራዊት ብሎ ሰራዊቱን በማሳለፍ ወደ ግብጽ ዘመቱ፡፡ በአካባቢዉ ያለዉንም አገር በመዉረር ብዙ የግብጽ ወታደሮችን ማረኩ፡፡ የግብጹ አረመኔ ንጉስ የኢትዬጲያዉ ንጉስ የፈፀመዉን ጀብዲና ድል ሰማ፡፡ አባ ሚካኤልን በአስቸኳይ ካልፈታ በጦርነቱ ወደ ኋላ እንደማይሉ እና እርሱም ጋር ለዘላለም ፈቅር እንደማይገኝ የማስጠንቀቂያ መልእክት ስለላኩበት በአስቸኳይ ሊቀጳጳስ አባ ሚካኤልን በአስቸኳ ፈትቶ በመንበረ ክብራቸዉ ላይ አስቀመታቸዉ፡፡ ለንጉሱ መታረቂያም ንጉስ መርዋን አልጋዴን የእጅ መንሻ ብዙ ወርቅና ብር በሊቀጳጳሱ እጅ የላከ ሲሆን ንጉስ ሰይፈ አርዕድም
ለበረከት
እንዲሆናቸዉ በእስክንድሪያ ቤተ-ክርስቲያን ዉስጥ ተከብሮና ተጠብቆ ከተቀመጠዉ ጌታ በተወለደ ጊዜ ሰብአ ሰገል ካቀረቡት የእጅ መንሻ ወርቅ ጋር ተደባልቆ እንዲቀመጥ ለሊቀጳጳሱ ለአባ ሚካኤል በሙሉ አስረክበዉ፤ ሊቀጳጳሱንም ወደ መንበረ ክብራቸዉ መልሰዉና የክርስትና ሃይማኖትን አጽንተዉ ከተመለሱ በኋላ 28 አመት በኢትዬጲያ ነግሰዉ ሞቱ፡፡ አጼ ሰይፈ አርድም ከሞቱ በኋላ ልጃቸዉ ዉድም አስፈሪ (ንዋይ ማሪም) የተባሉት መንበረ ዙፋኑን ተረክበዉ ዐስር ዓመት ያህል ኢትዬጵያን አስተዳደሩ፡፡ በመቀጠልም አጼ ዳዊት በትረ መንግስቱን የምስር(የግብጽ) ንጉስ ቀድሞ ከአፄ ሰይፈ አርዕድ ጋር የገባዉን የሰላም እርቅ ቃሉን አፍርሶ ክርስቲያኖች እምነታቸዉን ትተዉ ወደ እኔ ሃይማኖት መግባት አለባቸዉ በሚል በመጀመሪያ አሁንም ሊቀጳጳሱን አሰራቸዉ፤ ክርስቲያኖቹንም ማሰቃየትና ይህንንም መልዕክት ለወቅቱ የኢትዬጲያ ንጉስ አፄ ዳዊት ላኩ፡፡ ንጉሱም ሳይዉሉ ሳያድሩ እኔ ከአባቴ ከአጼ ሰይፈ አርእድ ብበልጥ እጅ የማንስ መስሎት ነዉ አባቴ ያስፈታቸዉን ሊቀጳጳስ የሚያስረዉ በማለት ተቆጥተዉ ሰራዊታቸዉን አስከትተዉ ወደ ግብጽ ዘመቱ፡፡
አፄ
ዳዊትም ካርቱም እንደደረሱ እኔ ግብጽ ድረስ በመሄድ ምን ያደክመኛል? ሰራዊቴንስ ለምን አደክማለሁ? ግብጻዊያን ዘር ዘርተዉ ተክለዉ የሚመገቡት ከአገሬ በሚፈስላቸዉ የዓባይ ወንዝ አይደለምን? ስለዚህ ዉሀዬ ወደ ግብጽ መዉረዱን ባቆመዉ ለህይወቱ ሲል ይለማመጠኝ የለምን? ብለዉ ካርቱም ላይ የዓባይን ዉሀ ገድበዉ ወደ ሱዳን በረሃ እንዲፈስ አደረጉት፡፡ ካርቱም ማለት ግድብ ማለት ነዉ፡፡ ይህንንም ስም በአሁኑ ጊዜ የሱዳን ዋና ከተማ የምትጠራበት ሲሆን ከዚህ ታሪክ ጋር እንደሚያያዝ አንዳንድ አባቶች ይናገራሉ፡፡ የግብጽ መኳንትም አጼ ዳዊት ዓባይን ገድበዉ እንዳስቀሩት ባዩ ጊዜ እጅግ በጣም ደነገጡ፡፡ የአባይ ዉሀ ከተቋረጠ ህዝባቸዉ ከዉሃ የወጣ አሣ መሆኑን ያዉቁት ነበርና፡፡ በዚህ ምክንት አስረዋቸዉ የነበሩትን የእስክሳንደሪያዊያንን ሊቀጳጳስ በአስቸኳይ ፈትተዉ በመንበረ ክህነታቸዉ ላይ አስቀመጧቸዉ፡፡
የግብጹ
ንጉስም አደግድጎ ሊቀጳጳስ አባ ሚካኤልን የአባይ ዉሀ ከተቋረጠ በግብፅ ምድረ ህይወት አይተርፍምና ዉሀዉን እንዲለቁ አፄ ዳዊትን ለምኑልኝ በማለት ተማፀናቸዉ፡፡ በእየሩሳሌም፣ በሶሪያ፣ በአርመንያ፣ በሮምና በቁስጥንጥንያ ወደ አሉትም አብያተ ክርስቲያናትና የይቅርታ መልዕክት አስተላለፈ፡፡
ለሊቀጳጳሱ
12 ዕልፍ
(120000) ወቄት የሚሆን ወርቅ እጅ መንሻ ለአፄ ዳዊት ላከ፡፡ አፄ ዳዊትም ሊቀጳጳሱ ተለቀዉ መምጣታቸዉን ሲሰሙ ጥቂት የጦር ሰራዊት አስከትለዉ አስዋን ከሚባለዉ የወቅቱ የኢትዬጲያና የግብጽ ድንበር ተቀብለዋቸዋል፡፡
አፄ
ዳዊትም ከግብጽ የተላከዉን ወርቅ ከተመለከቱ በኋላ ለሊቀጳጳሱ ክብር ሲባል ለ10 ቀናት ያህል ግብር ሲያስመግቡ ቆይታዉ የዓባይን ዉሀ ወደነበረበት መለሱላቸዉ፡፡
ግብጾች
ለእጅ መንሻ የላኩትን ወርቅ ግን አልቀበልም፤ በወርቁና በብሩ ምትክ በእስክንድሪያዉ ሊቀጳጳስ እጅ ተጠብቆ የተቀመጠዉን የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን መስቀል ሰጡኝ በማለት አጥብቀዉ ጠየቁ፡፡
በግብጽ
የሚኖሩ ክርስቲያኖችም ከስቃይና መከራ የታደጉዋቸዉን አፄ ዳዊትን ለማስደሰት መስቀሉ እንዲሰጣቸዉ ከሊቀ ጳጳሱ ጋር ስምምነት ደረሱ፡፡ በሌላ በኩል የምስር መኳንት መስቀሉን ለአፄ ዳዊት ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም፡፡
አፄ
ዳዊትም የምስርን መኳንት በተረዱ ጊዜ መስቀሉን ካላካችሁልኝ አገራችሁ በድርቅ ትጥፋ እንጅ እኔም የሀገሬን ሀብት የአባይን ዉሀ በፍጹም እገድበዋለሁ በማለት የማስጠንቀቂያ መልእክት ላኩ፡፡
የግብጹ
መኳንትም ችግር ላይ ከምንወርቅ መስቀሉን ይዉሰዱ በማለት ስምምነት ላይ ደረሱ፡፡ በሊቀ ጳጳሱ አባ ሚካኤል እጅም መስቀሉን፣ ከመስቀሉም ጋር የቅዱስ ሉቃስ የሳላቸዉን የሰባቱን ስዕለ ማርያምን፣ የቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ የሳለዉን የጌታችንን ስዕል፣ ልዩ ልዩ ንዋያተ ቅዱሳትን (የመጥመቀ መለኮት ቅዱስ ዮሀንስ ራስ፣ የእመቤታችን እናት የቅድስት ሐና አጽም፣ የቅዱስ ጊዮርጊስ አፅም፣ የቅድስት አርሴማ አፅም፣ የሐዋርዉ በርቶለሚዎስ አፅም፣ የቀዳሜ ሰማእታት እስጢፋኖስ አፅም፣ ሔሮድስ በቤተልሔም ያስፈጃቸዉ ህጻናት አፅም) እና ሌሎችም በአንድነት ጽላትም ጭምር አሉበት ድረስ አምጥተዉ ለአፄ ዳዊት መስከረም 10 ቀን 1395 ዓ/ም አስረከቧቸዉ፡፡
አፄ
ዳዊትም መስቀሉን ተረክበዉ ለሁለት ቀናት ያህል ግብር በማብላት የደስታ በአል ካደረጉ በኋላ ጳጳሳቱንና ቀሳውቁስቱን መስቀሉንና ንዋያተ ቅዱሳቱን አሸክመዉ ወደ ሀገራቸዉ ሲመለሱ መሻገሪያ አጥተዉ
ባጋጠማቸዉ
ታላቅ ወንዝ ሲጨነቁ ሳሉ ቅዱስ ሚካኤል በገሃድ ተገልጦ ዉሀዉን እየከፈለ አሻገራቸዉ ይባላል፡፡ የዚህም ተአምር መታሰቢያ በየዓመቱ መስከረም 12 ቀን እስከ ዘመናችን ድረስ በቅዱስ ሚካኤል ስም ይከበራል፡፡
አፄ
ዳዊት ወደ መሀል አገር እየመጡ ጉዞ ላይ ሳሉ መስከረም 21 ቀን 1395 ዓ/ም በህልማቸዉ ‹‹ይነብር መስቀልየ በዲ በመስቀል›› ማለት መስቀሌ በመስቀል ላይ ይቀመጣል የሚል ራዕይ ታያቸዉ፡፡ እርሳቸዉም እራዕዩ ከብዷቸዉ መስቀሉን ይዣለሁ በመስቀል ላይ ይቀመጣል የሚለዉ ትርጉሙ ምን ይሆን? እያሉ በአእምሯአቸዉ በማዉጣት በማዉረድ ጉዟቸዉን ቀጠሉ፡፡ ስናር ከሚባል አገር ሲደርሱ በድንገት ጥቅምት 2 ቀን 1395 ዓ/ም መስቀሉን በተረከቡ በ29ኛዉ ቀን አረፉ፡፡ አፄ ዳዊትም ኢትዩጲያን ለ30 ዓመት አስተዳድረዉ በድንገት ሳይታሰቡ በመሞታቸዉ በተፈጠረዉ ድንጋጤ መስቀሉንና ንዋያተ ቅዱሳቱን በባለቤትነት የኢትዩጲያ ሆኖ በአደራ በግብጾች ሊቃነ ጳጳሳት ቁጥጥር ስር ለ47 ዓመታት ያህል እንዲቆይ ተደረገ፡፡
በ1427
ዓ/ም የአፄ ዘርዓ ያዕቆብ የኢትዩጲያ በትራ መንግስት ጨበጠ፡፡ እርሱም በተወለደ በ50 ዓመቱ በነገሠ በ15 ዓመቱ በህልሙ ‹‹አንብር መስቀልየ በዲበ መስቀል›› መስቀሌን በመስቀለኛ ቦታ አስቀምጥ የሚል ራዕይ ታያቸዉ፡፡
አፄ
ዘርዓያቆብ ቀደም ሲል በአባታቸዉ ሞት ምክንያት በአደራ የተቀመጠዉን መስቀል ያዉቁ ስለነበር የግብጽ ጳጳሳትን ጠየቁ፤ ሊቀጳጳሳቱም ቀደም ሲል ከአፄ ዳዊት ጋር ባደረጉት ስምምነት መሠረት መስቀሉን በአፄ ዘርዓ ያቆብ መስከረም 21 ቀን 1443 ዓ/ም አስረከቡት፡፡ በታየዉ እራዕይ መሰረት መስቀሉን በመስቀለኛ ተራራ ለማስቀመጥ 3 ዓመት በኢትዬጲያ ክፍላተ ሀገራት ዙረዋል፡፡ በመጨረሻም በወሎ ክፍለ ሀገር አምባሰል አዉራጃ ሲደርሱ አንዲት መስቀለኛ አምባ አገኙ እርሷም ግሸን አምባ ናት፡፡
ግሸን
ደብረ ከርቤ
ከደሴ
ከተማ በስተሰሜን ምዕራብ 76 ኪ/ሜ በአምባሰል ወረዳ የምትገኘዉ ዳግማዊት እየሩሳሌም በመባል የምትታወቀዉ ይች ገዳም ከእምነትና ከአስተዳደር ጋር የተቆራኙ ታሪኮችን ይዛለች፡፡
የተቆረቆረችዉ
በ517 ዓ.ም በአጼ ካሌብ የክርስትና አባት የሆኑት አባ ፈቃደ ክርስቶስ የተባሉ መናኝ ናቸዉ፡፡ አባ ፈቃደ ክርስቶስ የቅድስት ድንግል ማሪያምንና የእግዚአብሔር አብን ጽላቶች ከሃገረ ናግራን /ከዛሬዋ የመን/ ይዘዉ ረጅም ጉዞ ተጉዘዉ አቀበቱን መንገድ አጥተዉ ሲፈልጉ በገደሉ ላይ ንብ ሰፍሮ ማር ተንጣሎ በማየታቸዉ ቦታዉን ሲያደንቁ ይህስ ‹‹አምባ ሰል›› ነዉ ያሉ ሲሆን ስል ማለት በአረበኛ ማር ሲሆን ትርጉሙ የማር አምባ ማለት ነዉ፡፡ አባ ፈቃደ ክርስቶስ ሁለት ጎጆዎች አሰርተዉ ያመጡትን የአብና የድንግል ማሪያምን ጽላቶች በማስገባት እስከ ህይወት ፍጻሜያቸዉ ሲያገለግሉ እንደቆዩ ይነገራል፡፡
አምባዉ
በተፈጥሮዉ ቀራጺ ባለሙያ የሰራዉ መስቀል የሚመስል እና ወደ አምባዉ ለመዉጣት ከአንዲት በር በቀር እንደ ምሰሶ የተቀረጸ ገደል ያለበት ነዉ፡፡ ይህችም በር በአጼ ኃይለ ስላሴ በጠፍጣፋ ድንጋይ ደረጃ ከመስራቱ በፊት አምባዉን ለመዉጣትና ለመዉረድ በገመድ ወይም በመጫኛ ወገብ ታስሮ ነበር፡፡
ግማደ
መስቀሉ ተቀብሮበታል ተብሎ የሚታመነዉ የእግዚአብሔር አብ ቤተ-ክርስቲያን በአጼ ዘርዓ ያቆብ እንደገና የተሰራ ሲሆን በዳግማዊ ሚኒሊክም ታድሷል፡፡ በዉስጡ በርካታ ሃይማኖታዊ ታሪክ ያላቸዉ ስዕሎችና ቅርሶች አሉት፡፡
ደብረ
ነጎድጓድና ደብረ እግዚአብሔር በመባል ትጠራ የነበረቸዉ የግሸን ማሪያም በአጼ ዘርዓ ያቆብ እህት እማሆይ እሌኒ በኋላም በአጼ ኃይለ ስላሴ ባለቤት እቴጌ መነን ታድሳለች፡፡ከዚህ ኃይማኖታዊ እምነት በተጨማሪ የግሸን አምባ ከመካከለኛዉ ዘመን የኢትዬጵያ ነገስታት ካቋቋማቸዉ የፖለቲካ ተቋማት መካከል አንዱና ዋነኛዉ ነበር፡፡ የግሸን አምባ እንደ ቤተ-መንግስት ወህኒ ቤትነትና በተቋምነት ተቋቁሞ የነበረዉ ከአጼ ይኩኖ አምላክ በኋላ ነዉ፡፡
ግሸን
በየዓመቱ መስከረም 21 እና ጥር 21 ቀን እጅግ በጣም በርካታ ምዕመናን በተገኘበት ትከበራለች፡፡ በርካታ የዉጭ ሀገር ጎብኝዎችም በበዓሉ ይገኛሉ፡፡
አፄ
ዘረዓያቆብ መስከረም 21 ቀን 1446 ዓ/ም መስቀሉን ይዘዉ ዛሬ በልማዳዊ አጠራር የአዳል ሜዳ እየተባለ በሚጠራዉ የተራራዉ መስቀል ክንፍ በኩል አድርገዉ ወደ አምባዉ ከገቡ በኋላየጎጆ አብያተ ቤተ ክርስትያናቶችን አፍርሰዉ ሰርተዋል፡፡ ከዚህን ጊዜ ጀምሮ እስካለንበት ዘመን ድረስ በዓሉ መስከረም 21 ቀን በመከበር ላይ ይገኛል፡፡
ቦታዉም
ባለ ቃል ኪዳን መሆኑን አበዉ ሊቃነ ጳጳሳት በመሃላና በዉግዘት አረጋግጠዋል፡፡
ጌታችን
ኢየሱስ ክርስቶስ ከተቀበረበት መቃብርና ከቅዱሳት መካናት ሁሉ የሚገኘዉን አፈር በ88 ግመሎች በ1000 በቅሎዎች አስጭኖ ወደ ኢትዬጲያ በማስመጣት ይህን በክርስቶስ ደም የተቀደሰ አፈር በግሸን ደብር ላይ እንዲበተን ተደርጓል፡፡ የእግዚአብሔር አብያተ ቤተ ክርስቲያን በዚህ ቦታ ላይ ከተሰራ በኋላ በዉስጡ ቅዱስ መስቀሉን 1ኛ ክቡር መስቀሉን በወርቅ ሳጥን አድርገዉ 2ኛ የወርቁን ሳጥን በብር ሳጥን ዉስጥ አድርገዉ 3ኛ የብር ሳጥኑን በነሃስ ሳጥን አድርገዉ 4ኛ የነሃስ ሳጥኑን በመዳብ ሳጥን ዉስጥ አድርገዉ 5ኛ የመዳብ ሳጥኑን በእርሳስ ሳጥን 6ኛ የእርሳስ ሳጥኑን በእንጨት ሳጥን አድርገው 7ኛ የእንጨት ሳጥኑን በብረት ሳጥን ዉስጥ አድርገዉ አርባ ክንድ ቆፍረዉ ዙሪያዉን አስገንብተዉ ከአጽመ ቅዱሳኑ ጋር ባሰሩት ቤተ መቅደስ ዉስጥ በክብር አስቀመጡት፡፡ ከመስቀሉ ጋር የመጡትን ሰፍንግን፣ ከለሜዳን፣ የሐዋርያት፣ የሰማዕታትና ሊቃነ ጳጳሳት አጽም በወርቅ በተለበጠ የእንጨት ሳጥን እንዲያኖሩት አደረገ፡፡ በታቦቱ አንጻር ተአምርት መስቀል ያለባቸዉ 3 ድንጋይዎች በማኖር ዳግመኛ መአት እንዳይታዘዝ ሰዎች እንዳይታወኩ ከቤተ ክርስቲያኑ ዉጭ እንጂ ከዉስጥ እንዳይቀበሩ ተደርጓል፡፡
መስቀሉን
አጅበዉ ከንጉሱ ጋር ወደዚች መስቀለኛ ተራራ ያስገቡት አባቶች ብጹዕ አቡነ ሚካኤል፣ አቡነ ገብርኤልና ኤጲስቆጶስ አባ ዩሀንስ ቦታዉን ተዘዋዉረዉ ባርከዉ ቅዱስ ቤቱንም በክብር ቦታዉ ላይ አስቀምጠዋል፡፡ በኋላም የሚከተለዉን እዉነተኛ የምስክርነት ቃል አስተላልፈዋል፡፡
የሊቃነ
ጳጳሳቱ የጋራ ቃለ ምዕዳንና ዉግዘት
‹‹መስቀሉ
ያለበትን የግሸንን ደብር የተሳለመ ሁሉ ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ያስተማረባቸዉን ቀራንዩን፣ ጎለጎታን እና ደብረ ታቦርን እንደተሳለመ ይሆንለታል፡፡ የግሸን ደብር ሌላ የሚመስላት የለምና፡፡ ይህችንም የስርየት ስፍራ ያቃለላት የተጠራጠራት ዕድሉ ወልድ ፍጡር እንዳለ እንደ አርዩስ ይሁን፡፡ እኛም በማይረባ ነገር አመስግነናት፣ አወድሰናት፣ አክብረናት፣ አግንነናት ብንገኝ እግዚአብሔር ጌታዉን ከሸጠ ከይሁዳ ጋር ይቁጠረን፡፡ ይህንን ነገር ያቃለለዉን ሰዉ በማይፈታ ስልጣናችን አዉግዘናል በማለት ተናግረዋል፡፡
ስለዚህ
ሦስቱ አበዉ ሊቃነ ጳጳሳት ስለቦታዋ ኪዳን የሰጡትን ቃለ ምዕዳንና ዉግዘት ጠንቅቀን በመረዳት ይህችን ታሪካዊትና ቅድስት ቦታ በማክበር፣ በዉስጧ ያለዉንም ቅርስ በመጠበቅና በማስጠበቅ፣ ለእንክብካቤዋ የሚያስፈልገዉን ሁሉ በማሟላት የቃል ኪዳኗና የበረከቷ ተሳታፊ ለመሆን ለእያንዳንዳችን ኃላፊነትና ግደታ ተሰጥቶናል፡፡ ሁላችንም አባቶቻችን የሰጡንን የአደራ ቃል አክብረን በመፈፀም የቅዱስ አምላካችን ክብር ወራሽ እንሆን ዘንድ ፈቃዱ ይሁን፡፡ አሜን
‹‹ከሰዉ
መርጦ ለሹመት ከእንጨት መርጦ ለታቦት›› እንዲሉ የግሸን አምባ ለመስቀሉ ዙፋንነት የተመረጠቸዉ አለም ሲፈጠር ለመሆኑ ሌላ ማስረጃ ማፈላለግና መመራመር የሚያሻ አይደለም፡፡
በሜሶዞይክ
ኤራ ተር ሸሪ ፔረድ፡)
አምባዉ
በመልካም አናጺ (ጠበብት) የተቀረጸ መስቀል መስሎ መታየት የመስቀሉ ዙፋን መሆነዋን ቁልጭ አድርጎ ያረጋግጣል፡፡ ‹‹ዙሪያዋ እሳት መሀሉ ገነት›› እንዲሉ በዙሪያዋ በገደል የተከበበችና ለእይታ ዉበትን የተላበሰች የመንፈስ እርካታን የምትሰጥ አምባ ናት፡፡
ግሸን
ደብረ ከርቤ ደብረ ነጎድጓድ ትባል ነበር ይህም በሁለት መልኩ ይገለፃል፡፡ ደብሯ ደብረ ነጎድጓድ ይባል በነበረዉ በኃይቅ እስጢፋኖስ ስር ስለነበረች የሚል ሢሆን ሁለተኛዉ በአምባዋ ላይ እንደ ነጎድጓድ የሆነ የዝማሬ ድምፅ ይሰማ ስለበር ነዉ ይባላል፡፡ ቀጥሎም ደብረ ነገስት ተባለች የነገስታት ልጆች መንፈሳዊ ት/ም እየተማሩ ይኖሩባት ስለነበር በመጨረሻም ክቡር መስቀሉ ከገባባት ጀምሮ ደብረ ከርቤ ተባለች፡፡ ደብረ ከርቤ ማለት ‹‹መካነ መስቀል›› /የመስቀል ቦታ/ ማለት ነዉ፡፡ ከርቤ የተሰበረዉን እንደሚጠግን ይህችም ቦታ በሀጢያት የተሰበረዉን ሰዉ በተሠጣት ቃል ኪዳን ከእግዚአብሔር ጋር አስታራቂ አንድነት ታሰጣለችና ደብረ ከርቤ ተባለች፡፡
የግሸን
ደብረ ከርቤ ቃል ኪዳን
የእግዚአብሔር
አብ ቤተክርስቲያን ቅዳሴ ቤቱ መስከረም 21 ሲያከብሩ በእግዚአብሔር አብና በእመቤታችን ቤተ ክርስቲያናት መካከል ከጸበሉ አጠገብ ባለችዉ የወይራ ዛፍ ስር ምስጢረ መለኮት ተገለጸ፡፡ ጌታ ከእናቱ ጋር ሆኖ ተገልጾ በቦታዉ ቃል ኪዳን ሠጣቸዉ፡፡ በዚህ ቦታ መጥቶ የተሳለመ የአርባ እና የሰማኒያ ቀን ህፃን ይሁን፤ ስጋየን ደሜን የተቀበለ ሔሮድስ በቤተልሔም እንደፈጃቸዉ ህፃናት ይሁን ይህች ቦታ እንደተወለድኩባት ቤተልሔም፣ እንደተጠመኩባት ዮርዳኖስ እንደተሰቀልኩባት ቀራንዩ፣ እንደተቀበርኩባት ጎለጎታ ትሁን ብሎ ቃልኪዳን ሰጥቶአቸዉ በክብር ወደ ሰማይ አረገ፡፡
ይህንንም
አባ ሚካኤልና አባ ገብርኤል የሚባሉ ሁለቱ ሊቀነ ጳጳሳት ተቀብለዉ ‹‹ጤፉት›› በምትባለዉ የስርዓተ መጽሃፍ ላይ መዝግበዉ አስቀመጡት፡፡
የግሸን
ደብረ ከርቤ ታሪካዊ ቦታዎች
የመግቢያ
በር
የአምባዉ
የመስቀሉ አናት ወይም ጫፍ ግርማዊት እቴጌ መነን በግል ገንዘባቸዉ አሰርተዉት ዛሬ በምንገባበት በር ላይ ያለዉ ሲሆን ይህም በር ፊት በር እየተባለ ይጠራል፡፡
የመግቢያ
በር
የደላንታ
ሜዳ
የአምባዉ
እግረ መስቀል ደግሞ ዛሬ የቅዱስ ሚካኤል ቤተ-ክርስቲያን ከተሰራበት ቦታ ሆኖ ወደ ላይ ሲመለከቱት የሚታየዉ ሲሆን የደላንታ ሜዳ እየተባለ ይጠራል፡፡ ይህም ስያሜ ሊሰጥ የቻለዉ ከቀድሞ ተሳላሚዎች በተለይ የደላንታ ሰዎች በዚህ አካባቢ ያረፉበት ስለነበረና አቅጣጫዉም ከደላንታ ጋር ትይዩ በመሆኑ የደላንታ ሜዳ ተብሎ ሊጠራ እንደቻለ አባቶች ይናገራሉ፡፡
የአዳል
ሜዳ
በስተ
ምስራቃዊ ሰሜን አቅጣጫ ያለዉ የመስቀሉ ክንፍና በአሁኑ ጊዜ የቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ተሰርቶበት ያለዉ አቅጣጫ ያለዉ ቦታ አጼ ዘርዓ ያቆብ መስቀሉን ይዘዉ የገቡበት እንደሆነ ሲተረክ ቦታዉ አዳል ሜዳ በመባል ይታወቃል፡፡
መሳቢያ
በስተ
ምዕራባዊ ደቡብ በኩል የሚገኘዉ የመስቀሉ ክንፍ ያለበት ቦታ መሳቢያ በመባል ይታወቃል፡፡ መሳቢያም የተባለዉ ለደብሩና ለኗሪዉ አገልግሎት የሚዉሉ ዕቃዎች ከጥግ በገመድ እየታሰሩ በመሳብ ወደ ዉስጥ ስለሚያስገቡት እንደሆነ ነዋሪዎች ያረጋግጣሉ፡፡
የእግዚአብሔር
አብና የቅድስት ድንግል ማሪያም አብያተ ክርስቲያናት ባሉበት መካከል ያሉ ታሪካዊ ቦታዎች
የእግዚአብሔር
አብ ፀበል
የእመቤታችን
ዉሀ
1. በእግዚአብሔር
አብ ፀበል ጠርዝ ላይ የበቀለችዉ ወይራ
ታቦቱ
የሚያርፍበትና የጤፉት ታሪክ የሚተረክበት አደባባይ
በእግዚአብሔር
አብ ቤተ ክርስቲያን ግቢ በስተምዕራብ አቅጣጫ ያሉት ሶስት ድንጋዬች
የእግዚአብሔር
አብን ቅጽረ ግቢ በስተ ምዕራብ በኩል ወጣ ሲሉ ተተክለዉ የሚገኙት ሶስት ድንጋዩች
ወደ
ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አቅጣጫ ሲወርዱ ከደላንታ ሜዳ ሳይደርስ በስተቀኝ በኩል የሚገኘዉ ዋሻ ጥቂቶቹ ሲሆኑ ስያሜያቸዉም በዝርዝር ስንመለከት
የእግዚአብሔር
አብ ፀበል አፄ ፀርዓ ያዕቆብ 88 በርሜል ከዩርዳኖስ ፀበል አስመጥተዉ ከጨመሩበት በኋላ ስሙን ዮርዳኖስ ፀበል ብለዉ ሰይመዉለታል፡፡ የፀበሉም ፈዋሽነት እጅግ በጣም የተመሰከረለት በመሆኑ ባሁኑ ጊዜ ይህ ዉሀ ለፀበልነት እንጂ ለሌላ ስጋዊ ጥቅም አይጠቀሙበትም፡፡ የድሮዉ አባታችን አቡነ ሚካኤልም በየዓመቱ ከእየሩሳሌም የዮርዳኖስ ፀበል እያመጡ ይጨምሩበት እንደነበር የግቢዉ ሊቃዉንት ያረጋግጣሉ፡:
2. የእመቤታችን
ዉሀ
የቅድስት
ድንግል ማሪያም ፀበል በመሆኑ የፈዋሽነት ኃይል ቢኖረዉም በግቢዉ ሌላ አማራጭ ዉሀ ባለመኖሩ የደብሩ ግቢ ነዋሪዎች በመጠጥና በማብሰያነት ይጠቀሙበታል፡፡ የዉኃዉም ተአምረኝነት የሚታወቀዉ የኩሬ ዉኃ ሲሆን በነዋሪዉ ላይ አንድም የዉሀ ወለድ በሽታ እስካሁን ሳይከሰት ሁሉም በጤንነት የሚጠቀሙበት መሆኑ ነዉ፡፡
3. የእግዚአብሔር
አብ ፀበል ዳር የበቀለችው የወይራ ዛፍ
በስተምስራቅ
አቅጣጫ የምትታየዉ ወይራ አባ ሚካኤልና አባ ገብርኤል የተባሉ አባቶች ከአጼ ዘርዓ
ያዕቆብ
ጋር መስቀሉን ይዘዉ ገብተዉ ካስቀመጡ በኃላ የቦታዉ ቃል ኪዳን በራዕይ ተገልፆላቸዉ
ሕዝቡን
ወይራዋ ባለችበት ቦታ ላይ አሰባስበዉ ምህላ በማድረግ ይህች ቦታ ደብረ ዘይት ትባላለች፡፡
(ደብረ
ዘይት ትሁን) ብለዉ በተናገሩበት ዕለት ሌሊቱን በቅላ አድራ አድጋ እስከ ዘመናችን እንደደረሰች
ሊቃዉንቱ
ይተርካሉ የቦታዋም ስም ደብረ ዘይት ተባለ፡፡
4. ታቦታቱ
እየወጡ የሚያርፉበትና ስብሐተ እግዚአብሔር የሚነገርበት፣ ወንጌለ መንግስት ሰማያት
የሚሰበክበት፣
የጤፉት መጽሀፍ የሚተረክበት አካባቢ አባ ሚካኤልና አባ ገብርኤል ይህ ቦታ ጽርሐ
አርያም
ይባላል በማለት ስለሰየሙት የጽርሐ አርያም አደባባይ በመባል ይታወቃል፡፡
5. በእግዚአብሔር
አብ ቤተ ክርስቲያን አዉደ ምሕረት በስተ ምዕራብ አቅጣጫ ያሉት መስቀል ያለባቸዉ
ሦስት
ድንጋዬች አጼ ዘርዓ ያዕቆብ ለምልክት የተከሉዋቸዉ ሲሆን ከነዚያ ምልክቶች ወደ ዉስጥ ሴቶች
እንዳይገቡ
አስክሬን እንዳይቀበር ስርዓት ሰርተዋል፡፡
6. በእግዚአብሔር
አብ ቤተ ክርስቲን ግቢ በስተምዕራብ አቅጣጫ ባለዉ በር ስንወጣ ተተክለዉ የሚገኙትና ሰዎች በመካከላቸዉ ለማለፍ የሚታገሉባቸዉ ሦስት ድንጋዩች አንዲት ሴት በትዕቢት ተወጥራ እንደ በረያሱስና እንደ ሐናንያ (የሐሥ 5÷1-13፤13÷6-11) እግዚአብሔርን በመፈታተኗ ስለተፈረደባት ለእርሷና ለሁለት ገረዶች ማስታወሻ የተተከሉ ምልክቶች ናቸዉ፡፡ ዝርዝሩም እንደሚከተለዉ ይተረካል፡፡ አፄ ዘርዓ ያዕቆብ የእግዚአብሔር አብን በጥሩ ሁኔታ ካሳነፁ በኋላ የምልክት ድንጋዩችን አስቀምጠዉ ከዚህ ወድያ ሴቶች እንዳይገቡ በሚልም ስርዓት ደነገጉ፡፡ አባ ሚካኤልና አባ ገብርዔልም አወገዙ፡፡ በዚህ ስርዓትና ህግ መሰረት ሲፈጸም ከቆየ በኋላ አንድ ሴት ወይዘሮ የወንድ ልብስ ለብሳ ገረዶቿንም ወንዶች አስመስላ አልብሳ ሰተት ብላ እግዚአብሔር አብ ቤተክርስቲያን ገብታ ከቆየች በኋላ ቸርነቱ የማያልቅ አምላክ ታግሷት ሳትቀሰፍ ከቤተ ክርስቲያኑ ቅጥር ግቢ ወጥታ አሁን ድንጋዬቹ ከተተከሉበት ቦታ ላይ ቆማ እኔ ሴት ነኝ እግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያን አትግቡ ትቀሰፋላችሁ እያሉ ሲያታልሉ ይኸዉላችሁ እኔ ገብቸ በደህና ወጣሁ እያለች ለህዝብ ስትናገር በቆመችበት ላይ ያለዉ መሬት ተከፍቶ ወደ መሬት ሰጠመች፡፡ ሁለቱ ገረዶቿም እመቤታችን ብለዉ ግራ ቀኝ የእመቤታቸዉን እጅ ሲይዙ እነርሱም አብረዉ ወደ ተከፈተዉ መሬት ዘቅጠዉ ቀርተዋል፡፡
ከዚያን
ጊዜ ይህ ተአምር በህዝብ ፊት በመፈጸሙ እነዚህ ሶስት ድንጋዩች ለማስታወሻነት፣ ለማስተማሪያነት እንዲሆኑ መተከላቸዉን ሊቃዉንቱ ይተርካሉ፡፡
ወደ
ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ሲወርዱ ከዳገቱ ላይ በስተቀኝ በኩል የሚታየዉ ዋሻ የንጉስ ላሊበላ ከድንጋይ የተፈለፈለ ቤተ ክርስቲያን እሰራለሁ ብሎ የጀመረዉ ዋሻ ነዉ፡፡ ይህንንም ለማሰራት በጀመረበት ጊዜ በመላኩ ቅዱስ ዑራኤል ይህ የመስቀሉ ዙፋን ስለሆነ የታዘዘልህ ሌላ ቦታ ነዉ በማለት በራዕይ ስለተገለፀለት ጀምሮ የተወዉ ነዉ፡፡
የግሸን
ማሪያም ጉዞየ
ልዩ
ልዩ ግጥሞች
.........የሁሉም ልማድ
ነበርና ከመኪና ላይ መዉረዱ
እጅና
እግርን ታጥቦ በዉኃዉ ተለያየንን መራመዱ
እኛም
ከመኪናዉ ላይ ቶሎ ወርደን የበሽሎዉ ጠረን እያወደን
እድፋችንን
ልናፀዳ ሰዉነታችንን ታጠብን፡፡
ከበሽሎዉ
ቆመን ከዉኃዉ ላይ
አትኩረን
ስናይ ወደ ሰማይ
ከርቀት
ታየን ተራራ
መስቀል
ያለበት ቅዱስ ስፍራ፡፡
የመስቀልን
ቅርፅ ጥበቡን
ከእንጨት
ነበር የሚዘጋጅ
አመሰቃቅሎ
የሚበጅ
ልዩ
ነገር ሰማን ሲወራ
መስቀል
ከተራራ ሲሰራ፡፡
...... የቀንን አቀበት
ተጋፍጠን
ጠመዝማዛዉንም
መንገድ አልፈን
በመስቀሉ
አናት ስንወጣ
እኛ
የምንሰማዉ ሲባል
ለወንጀለኛ
ነዉ መስቀል
ነገር
ግን ሁሉም ወጣበት
በመስቀሉ
ሊያገኝ ድኅነት፡፡
ሰዉ
ለመግባት ሲጣደፍ
ወደ
ጠባቡ ደጃፍ
እኔም
ተራየን ጠብቄ
የዘወትር
ልብሴን አዉልቄ
ጠባቡንም
በር አልፌ
ከትንሿ
መስክ አርፌ
ግራና
ቀኝ ስቃኝ
የመስቀሉን
ክንፍ አየሁኝ፡፡
..........እግዚአብሔር አብ
ተሰቅሎበት
መስቀል
ሆነልኝ ድኅነት፡፡
እኔም
ደስ አለኝ ባለ አቅሜ
በመስቀል
ተራራ ላይ መቆሜ፡፡
ከእንግዲህ
ወድያ አከተመ
የኃጢያት
ክምር ወደመ፡፡
የጻድቅን
ስራ አገኘን
ወደ
ግሸን ማርያም መጥተን
ኃጢያታችንን
ለፋቀልን
እግዚአብሔር
አምላካችን
ከአሁን
ጅምሮ ለዘለአለም እስከዘለአለም ክብር ይሁን፡፡
የድኅነት
አዝመራ
አንቺ
ደብረ ከርቤ ኢየሩሳሌም
የለብሽ
አበሳ የለብሽ መገረም፡፡
አንቺ
የኖኃ ርግብ አማን በአማን
ጥፋቱ
ዉኃ ጎደለ በይን፡፡
የዘርዓ
ያዕቆብ የዳዊት ሙሽራ
ከደረትሽ
ያለዉ መስቀልሽ አበራ፡፡
ቃል
ኪዳንሽ አባይ ምንጩ የማይደርቅ
ሰዉ
ሁሉ ቢቀዳዉ ቢጠልቀዉ አያልቅ፡፡
ከዚያ
ከተከልሽዉ ከመስቀሉ ሾላ
ይህች
ርህብት ነፍስ ፍሬ ጽድቁን ትብላ፡፡
አዳም
የተከለዉ የዘራዉ ጸደቀ
መሬትሽ
ነዉና በጣም የታወቀ፡፡
ከቶማነዉ
እጁ የማይዘረጋልሽ፡፡
ከመንገድ
ተጣልተዉ ባንቺ ሲማማሉ
ሰ.ዉና ሀጢያት ተለያየን አሉ፡፡
እኒያ
ጉልቻዎች ወንዙን ይሻገሩ
በቃ
ተለያየን እያሉ እንዳይኖሩ፡፡
መለያየት
የለም በአንቺና መስቀል
ሁናችኋልና
አንድ አካል አንድ አምሳል
አረንጓዴ
ቢጫ ካልሆነ መልክሽ
ያቺ
የመስቀል ወፍ ማነዉ የሚልሽ፡፡
አንች
የዳዊት ቤት የሰለሞን ጓዳ
ጉልላትሽ
መስቀል ጣራሽ ካለሜዳ
በርሽ
ጠባብ ቢሆን መንገድሽ ቀጭን
መንግስተ
ሰማየት አንቺ ነሺ ግሸን፡፡
አንቺ
ደብረ ከርቤ ልበ ኢትዬጲያ
አንቺ
ደብረ ከርቤ ጦብያዊት ሮምያ
ሆነሻል
ጳዉሎስ ሐድስ ሀዋርያ
እንግዲህ
አዳምጭዉ እያለ ሲያስተምር
ማነዉ
የሚለየን ከክርስቶስ ፍቅር፡፡
ኮረብታዉ
ይደልደል መንገዱም ይሰራ
አቀበት
ደብረ ከርቤ እያልን እንድንኮራ፡፡
መስቀል
በመስቀል ላይ ተደራርቦ ሳለ
ማነዉ
የሚሰንፈዉ አቀበት እያለ፡፡
.... ሰዉ በሩቅ
ይመኛል ኢየሩሳሌም
መጓዝም
ያስባል ወደዚያች ገዳም
ነገር
ግን ቢረዳ ቢያዉቅ እዉነቱን
መስቀሉ
እኮ እዚህ ነዉ ያዉም በግሸን፡፡
ታድያ
ምን ያደክማል መጓዝ ባህር ማዶ
መስቀሉ
እያለን በሽሎዉን ተራምዶ፡፡
አባ
ገብርኤልና አባ ሚካኤል
ብፁዓን
አባቶች የአምላክ ባለሟል
ስንመረምረዉ
የሰጡትን ቃል
ግሸን
ደብረ ከርቤ ኢየሩሳሌም ናት
ከቦታዋ
ደርሶ ለተሳለማት
ግሸን
ደብረ ከርቤ ጌቲሴማኒናት፡፡
ምዕመናን
በጋራ እንድያከብሯት
ሲሉ
አስተላልፈዋል የጴጥሮስን ዉግዘት፡፡
በሽሎዉን
ተሻግረን አቀበቱን ወጥተን
ክፉዉን
ተንኮልን አምዘግዝገን ጥለን
ዉግዘቱን
አክብረን የአባቶቻችንን
በቃል
ኪዳን አምባ ግሸን ላይ ተገኝተን
ከመስቀሉ
ዙፋን ደብረ ከርቤ ደርሰን
የድህነት
አዝመራን መሰብሰብ አለብን
ይህንም
ለማድረግ አምላካችን ይርዳን፡፡
አልጋ
ባልጋ ነዉ መንገዱ
ወደ
ግሸን ደብረ ከርቤ ሲሄዱ፡፡ እያሉ በአመታዊ ክብረ በዓላቱ ከሀገራቱ አራቱም አቅጣጫ እና ከሌላዉ አለም ርቀት ሳይገድባቸዉ እጅግ በርካታ ታዳሚ ይታደምበታል፡፡
ለዚች
ቅድስት እና ታላቅ ደብር የሚጎርፈዉን የሃይማኖት ቱሪስት ማስተናገድ የሚያስችላት በርካታ መሠረተ ልማት የሚያስፈልጋት በመሆኑ የሁሉም አካል ርብርብ ተቀናጅቶ ሊሄድ ይገባል፡፡
በተለይ
አሁን የመስቀል በአል በዓለም መመዝገቡ የዉጭ ሀገር ቱሪስቱ መዳረሻ ስለምትሆን የመሰረተ ልማቱ ትኩረት ሊሰጠዉ ይገባል፡፡
የደመራ
በዓል መቼ ተጀመረ
ቀደም
ብሎ እንደተገለፀዉ ንግስት ዕሌኒ መስቀሉ ተቀብሮ የኖረበትን ትክክለኛ ቦታ ለማወቅ በራዕይ ከተገለፀላትና ከመንፈሳዊ ሰዎች በተነገራት መሰረት ብዙ እንጨት አስደምራ ብዙ እጣን ጨምራ በእሳት በማያያዝ ሲቀጣጠል የዕጣኑ ጢስ ወደ ላይ ቀጥ ብሎ ከወጣ በኋላ እንደ ቀስት ወደ መሬት ተመልሶ መስቀሉ የተቀበረበትን ቦታ አመልክቷል፡፡ በዚያዉ ቦታ ተቆፍሮ በተገኘም ጊዜ ታላቅ ደስታ ሆኖአል፡፡ ዕሌኒና ሰራዊቱ የመስቀሉን መገኘት በየሀገሩ ለመግለጽ ችቦ /ዳቦት/ በማብራት ዜናዉን አስተላልፈዋል፡፡ ይኸዉ ይኽዉ ያዉ ..ያዉ.. (ኢዩሀ.. ኢዩሀ..) መስቀሉ ተገኘ፤ መስቀሉ አበራ እያሉ ዘምረዋል፡፡
እኛም
ክቡር መስቀሉ የተገኘበትን ሃይማኖታዊ ታሪክ ለማስታወስ ደመራ እየደመርን ችቦ እያበራን"መስቀል አብረሃ በከዋከብት አሠርነዉ ሰማየ እምኩሉስ ፀሀይ አርአየ" መስቀል አበራ እንደ ከዋክብትም ሰማይን አስጌጠ እንደ ፀሀይ አሳየ" እያልን ከቅዱስ ያሬድ ጋር በዝማሬ በዕልልታ በሆታ የመስቀልን በዓል በየዓመቱ እናከብራለን፡፡
በሀገራችን
ኢትዬጲያ በየአመቱ መስከረም 16 ቀን ማታ የደመራና የችቦ ማብራት ስነ-ስርዓት ይፈፀማል፡፡ መስቀሉ የተገኘበት ቀን በአሉ መስከረም 17 ቀን ቤት ያፈራዉን ድግስ በማዘጋጀት በደማቅ ሁኔታ ይከበራል፡፡
በገጠሩዋ
የደቡብ ወሎ አካባቢ የደመራዉ ዕለት ምሽቱ መጨለም ሲጀምር 1-2 ሰዓት ቀድሞ ጅራፍ በማንጓት የቅስቀሳ መልዕክት ከተከናወነ በኋላ ደመራዉ ተለኩሶ ከቤት ሲወጣ ‹‹የስጋዉ ምንቸት ግባ የጎመኑ ምንቸት ዉጣ›› ተብሎ በየቤቱ ባሉ ልጆች ልክ ችቦ ተዘጋጅቶ ‹‹እዩሀ...... እዩሀ›› እያሉ እየተሯሯጡ ያበራሉ፡፡ የእጃቸዉ ችቦ ከማለቁ በፊት በአንድ ስፍራ ያሉት በጋራ ተሰባስበዉ ሽማግሎች ባሉበት አጋጥመዉ ያበራሉ፡፡ የደመራ ችቦዉ የወደቀበትን አቅጣጫ የቀጣዩን ዘመን የመልካም አጋጣሚ ነዉ በማለት ስለሚያምኑ የሚወድቅበትን አቅጣጫ ይከታተላሉ፡፡ በመጨረሻ በአባቶች ዓመት ያድርሳችሁ ተብለዉ ተመርቀዉሲጨርሱ ትርኳሹን ደግሞ ለከብቶቻቸዉ መልካም ተስፋ መታ መታ ለማድረግ ይጠቀሙበታል፡፡
በአጠቃላይ
እነዚህ ዕለታት የመስቀሉ በዓል የሚከበረዉ የተቀበረዉን ለማዉጣት ቁፋሮ የተደመረበትን ኃላም ለመስቀሉ መቀመጫና መታሰቢያ በስሙ የተሰራዉ ቤተ-መቅደስ ቅዳሴ ቤቱ የተከበረበትን ከጊዜም በኋላ እንደገና መስቀሉ ተዘርፎ ከተወሰደበት አገር በእግዚአብሔር ኃይልና በመስቀሉ ተአምራት የተመለሰበት የድልና የተአምራት ቀኖች ለማሰብ ነዉ፡፡
የግሸን
ደብረ ከርቤ መሰረተ ልማት በተመለከተ
የመብራት
የዉሃ
የመፀዳጃ
ቤት
ከኩታበር
እስከ ደላንታ ያለዉን መኪና መንገድ እና ከበሽሎ ወንዝ እስከ ግሸን ደብረ ከርቤ ሁለተኛው መነሀሪያ /ሀሙሲት/ በግሸን ደብረከርቤ ከሀሙሲት አስከ ደብሩ መግቢያ /አህያ መራገፊያ/ በ200ሽ ብር ውጭ በማድረግ የመንገድ ጠረጋ ስራ ተሰርቷል፡፡
የሙዚየም
ግንባታ 50 ከመቶ ደርሷል በደብሩ 4 ሚሊዮን ብር የፈጀ ሲሆን አስር ሚሊየን የሚፈጅ ሰለሆነ የሁሉንም ትብብር ይጠይቃል፡፡
በአካባቢዉ
ማህበረሰብ የማደሪያ ቤት ኪራይ የምግብና መጠጥ
የባህላዊ
የትራንስፖርት አገልግሎት፡- በጋማ ከብቶች እና በሰዉ ኃይል የሚሰጥ ሲሆን በዚህ ታላቅየቱሪዝም ሃብት የሚሰጠዉ አገልግሎት ለሃይማኖታዊ ቱሪስቱ በቂ የሆነ ነዉ ማለት አይቻልም፡፡ ምክንያቱም 400000 ለሚሆን ቱሪስቶች የሚያረካ የቱሪዝም አገልግሎት እየተሰጠ ባለመሆኑ እና ማግኘት የሚገባዉን የቱሪዝም ገቢ እየተገኘ ባለመሆኑ ነዉ፡፡ የደቡብ ወሎ ሃገረ ስብከት የቅርስ ክፍል የሆኑት መላከ ኃይል ደመቀን እንዳነጋገርናቸዉ ፡- "ይህ ደብር በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ ሳይንስና ባህል ድርጅት መመዝገብ ያለበት ትልቅ የታሪክና ቅዱስ የሃይማኖት ቦታ ነዉ፡፡ በማለት የክልሉ መንግስት ይህን ቦታ ትኩረት ሰጥቶ በተለይ መንገዱን በአስተማማኝ ሁኔታ በመስራት የዓለም የቱሪስት መዳረሻ እንዲሆን ሊሰራ ይገባል፡፡ " ብለዋል፡፡ እኛም ቦታዉ የመስቀል በዓል የዓለም ቅርስ ሆኖ የተመዘገበ መሆኑ ክቡር መስቀሉ የተቀመጠበትና በተፈጥሮዉ መስቀል የሆነ የሃማኖት፣ የታሪክ እና የተፈጥሮ የቱሪዝም ሃብትነት ያለዉ ይህ የመካነ መስቀል ተራራ ለቱሪስት መዳረሻ እንዲሆን በስፋት ቢጠናና ዘመናዊ የመሰረተ ልማት ቢሟላለት ከዞንና ከክልላችን አልፎ ለሀገራችን የላቀ የቱሪዝም ጠቀሜታ የሚሰጥ የዓለም ቅርስ በመሆኑ ሃይማኖታዊ ታቋማት፣ ህዝብ፣ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ተቀናጅተዉ ሊሰሩ ይገባል፡፡በተለይ የሚመለከታቸዉ ከወረዳ እስከ ክልል ያሉ መ/ቤቶች እና የአስተዳደር አካላት ለዚህ ቦታ ትኩረት በመስጠት የመሰረተ ልማቱን በማሟላት የዓለም የቱሪስት መዳረሻ እንዲሆን በመስራት የአካባቢዉን ማህበረሰብ ከቱሪዝም ተጠቃሚ በማድረግ የቱሪዝም ገቢዉን ማሳደግ ያስፈልጋል፡፡
በደቡብ
ወሎ ዞን የበርካታ የቱሪዝም ሀብት ያለ ሲሆን ይህን ሀብት በአግባቡ በማልማትና በማጥናት ከቱሪዝም ተጠቃሚ መሆን ይገባል፡፡ አብዛኛዉ ሰዉ የቱሪዝም ሀብት ሲነሳ ቁሳዊ የሆኑትን የተፈጥሮ፣ ሰዉሰራሽ (ባህላዊ) እና ታሪካዊ የሆኑትን ቀድመዉ ያስባሉ፡፡ ነገር ግን ህሌናዊ (የማይዳስሱ) ጥቃቀን የሚባሉ በርካታ የቱሪዝም ኃብት የሆኑ እሴቶች ባለቤት ነን፡፡
የሙዚቃ
ቅኝቶች ባቲ፣ አምባሰል፣ ትዝታ፣ አንችሆየ፣ የመንዙማ፣ የስነ-ቃል፣ የበአላት አከባበር ትርኢቶች፣ ትዉፊት ጥበባት፣ ማህበረሰባዊ ክንዋኔዎች ስነ-ስርዓቶች ፌስቲቫሎች፣ የተፈጥሮ እዉቀትንእና ትዉፊታዊ የእደ ጥበብ እዉቀቶችን ሁሉ ትኩረት ሰጥቶ በመስራት ዘርፉን በማሳደግ ተጠቃሚ መሆን ያስፈልጋል በማለት በዚሁ ለዛሬ ጨረስን፡፡
Subscribe to:
Posts (Atom)