Monday, 31 October 2016

የመናፍቃን የሮሜ 8፥34 የማታለያ ጥቅስ ሲጋለጥ!

የመናፍቃን የሮሜ 8፥34 የማታለያ ጥቅስ ሲጋለጥ!


ከመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ (የሐዲስ ኪዳን ትርጓሜ መምህር)
የኢየሱስን የባሕርይ አምላክነትና ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር የተካከለ መኾኑን ለማመን የተቸገሩና ፈራጅነቱን የካዱ ተጠራጣሪዎች ከሚያቀርቧቸው ጥያቄዎች አንደኛው በሮሜ 8፡34 ላይ ያለው ኀይለ ቃል ነው፡፡ ይኽ “እስመ ለሊሁ ያጸድቅ መኑ ዘይኴንን ክርስቶስ ሞተ ወተንሥአ እሙታን ወሀሎ ይነብር በየማነ እግዚአብሔር ወይትዋቀስ በእንቲኣነ” (ርሱ ሲያጸድቅ የሚፈርድ ማነው ክርስቶስ ሙቶ ከሙታን ተለይቶ ተነሥቶ በአብ ቀኝ ተቀምጧል ስለእኛም ይፈርዳል) የሚለው የጠራው የግእዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ኀይለ ቃል በተለየ መልኩ በዘመናት ኹሉ ለዚኽች ቤተ ክርስቲያን መቼም ቢኾን መልካም ዐስበው በማያውቁ ይልቁኑ ፈራርሳ ቢያይዋት ደስ በሚሰኙ የክርስቶስን ፈራጅነት በካዱ በባሕር ማዶ ቀሳጮች ብዙ ጊዜ ተሰርዞ (ይማልዳል) በሚል ተቀይሮ እናነብባለን፡፡
ለምስክርነት እስቲ እንይ፡-
በ1938 ዓ.ም ታትሞ የነበረው መጽሐፍ ቅዱስ “ክርስቶስ ኢየሱስ ሞተ ከሙታንም ተለይቶ ተነሣ፤ በአብ ቀኝ ተቀምጧል፤ ስለእኛም ይፈርዳል” ይላል።
በበ1975 ዓ.ም ታትሞ ከግእዙ ወደ ዐማርኛው የተመለሰው “ርሱ ሲያጸድቅ የሚፈርድ ማነው ክርስቶስ ሙቶ ከሙታን ተለይቶ ተነሥቶ በአብ ቀኝ ተቀምጧል ስለእኛም ይፈርዳል” ይላል፡፡
በ1980 ዓ.ም ግእዙን የሚያውቁ ዐይናማ ሊቃውንት ሳያዩት በጥቂቶች አስተባባሪነት የክርስቶስን ፈራጅነት በማያምኑ በምዕራባውያን የዶላር ድጋፍ የታተመው ደግሞ “እግዚአብሔር የመረጣቸውን ማን ይከሳቸዋል? የሚያጸድቅ እግዚአብሔር ነው የሚኰንንስ ማን ነው? የሞተው ይልቁንም ከሙታን የተነሣው፥ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው” ይላል፡፡
ይኽ ዕትም ችግሩ ይኼ ብቻ ሳይኾን የሐዲስ ኪዳን መጽሐፍ የተጻፈበትን የግሪክን ቋንቋ እና ቀደምት የተተረጎመትን የግእዝ፣ የሶርያ፣ የአርመን፣ የቅብጥ ቅጅ በተለይ በግሪክ የተጻፈውን የ1900 ዓመት እድሜ ያለውን የሐዲስ ኪዳን መጽሐፍ ከማየት ይልቅ እንግሊዞች እንዲመቻቸው አድርገው ቃላቱን በድፍረት እየጨመሩና እየቀነሱ በ1611 ዓ.ም ያሳተሙትን የ400 ዓመት ዕድሜ ያለውን የኪንግ ጀምስ ቅጂን ወደ ዐማርኛ ተርጒመው ለማቅረብ ሞክረዋል፤
በዚኹ በሮሜ 8፡27 ላይ “ወባሕቱ መንፈስ ለሊሁ ይትዋቀስ ለነ በእንተ ሕማምነ ወምንዳቤነ ወውእቱ የሐትቶ ለልብነ ወየአምር ዘይኄሊ መንፈስ ወይትዋቀስ በኀበ እግዚአብሔር በእንተ ቅዱሳን” (ርሱ ራሱ መንፈስ ቅዱስ ይመልስልናል፤ ርሱ ልቡናችንን ይመረምረዋል፤ ልብ ያሰበውን ርሱ መንፈስ ቅዱስ ያውቃል፤ በእግዚአብሔር ዘንድም ለቅዱሳን ጸሎት መልስ ይሰጣል) የሚለውን ገጸ ንባብ ለውጦ በድፍረት “ነገር ግን መንፈስ ራሱ በማይነገር መቃተት ይማልድልናል ልብንም የሚመረምረው የመንፈስ ዐሳብ ምን እንደ ሆነ ያውቃል፥ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ስለ ቅዱሳን ይማልዳልና” በሚል በድፍረት ቃሉን በመለወጥ መንፈስ ቀዱስንም አማላጅ አድርገው መንፈስ ቅዱስን በመናቅ አሳትመውት እናነብባለን፡፡
ይኽ እንደ እግዚአብሔር ቅዱስ ፈቃድ የተጻፈውን ቅዱስ ቃል ሰዎች እንደገዛ ፈቃዳቸው አጣምመው ለማቅረብ የሚሞክሩ ቢኾንም እስቲ ቅዱስ ጳውሎስ በሮሜ 8፡33-34 ላይ “እግዚአብሔር የመረጣቸውን ማን ይከሳቸዋል? የሚያጸድቅ እግዚአብሔር ነው የሚኰንንስ ማን ነው? የሞተው ይልቁንም ከሙታን የተነሣው በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው ደግሞ ስለ እኛ …… ክርስቶስ ኢየሱስ ነው” የሚለውን ኀይለ ቃል በዝርዝር ዐይተን ሰዎች በተለያየ ጊዜ የጨመሩበት በባዶ ቦታው ላይ ያለው በእውነት ስለምን እንደሚያስገነዝብ መረዳት እንችላለን እስቲ ከዚኽ በታች እንየው፡-
“እግዚአብሔር የመረጣቸውን ማን ይከሳቸዋል?”
ቅዱስ ጳውሎስ በዚኽ ምዕራፉ ላይ በትክክል እንዳስቀመጠው እግዚአብሔር መራጭ እንደኾነ ነው፤ ከላይ በትክክል እንዳየነው በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ እንደሰፈረው ኢየሱስ ክርስቶስ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር የተካከለ በእውነት እግዚአብሔር እንደኾነ የታወቀ የታመነ የተረጋገጠ ነውና ስለዚኽ “እግዚአብሔር የመረጣቸውን ማን ይከሳቸዋል?” በማለት የኢየሱስ ክርስቶስን እግዚአብሔርነት አረጋግጦ ጻፈ፤ የመረጣቸውስ ማንን ነው ቢሉ “ንዑ ትልዉኒ” (ኑ ተከተሉኝ) ብሎ የጠራቸው ብሎ ሐዋርያትን፤ ዳግመኛም 72ቱ አርድዕትን፣ 36ቱ ቅዱሳት አንስትን ነው፤ ይኽነንም ወንጌላዊዉ ማቴዎስ “ዐሥራ ኹለቱን ደቀ መዛሙርቱን ወደ ርሱ ጠርቶ እንዲያወጡአቸው በርኩሳን መናፍስት ላይ ደዌንና ሕማምንም ኹሉ እንዲፈውሱ ሥልጣን ሰጣቸው” በማለት ፲፪ቱ ሐዋያትን እንደጠራና ሥልጣንን እንደሰጣቸው በትክክል አስቀመጠ፡፡
ራሱ ቅዱስ ጳውሎስም በዚኹ ምዕራፍ ቊ፴ ላይ “አስቀድሞም የወሰናቸውን እነዚህን ደግሞ ጠራቸው፤ የጠራቸውንም እነዚህን ደግሞ አጸደቃቸው፤ ያጸደቃቸውንም እነዚህን ደግሞ አከበራቸው” በማለት ሐዋርያት ሰብአ አርድዕት እያለ የሾማቸው ስምዖን የተባለውን ጴጥሮስ ልብድዮስ የተባለው ታዴዎስ፤ ዲዲሞስ የተባለውን ቶማስ እየለ የጠራ ራሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ መኾኑን መሰከረ፡፡
“የጠራቸውንም እነዚህን ደግሞ አጸደቃቸው” በማለት የጠራቸውን የሐዋርያት ነገራቸው ወንጌልን በተአምራት እያስረዳ እያጸደቀ እውነት መኾኑን ሰዎች እንዲያውቁት ያደረገው ራሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ መኾኑን አስረዳ፡፡ ከዚያም “ያጸደቃቸውንም እነዚህን ደግሞ አከበራቸው” የጠራቸው ሐዋርያቱን በዚኽም ዓለም በተአምራት በወዲያኛውም ዓለም “እውነት እላችኋለሁ፥ እናንተስ የተከተላችሁኝ፥ በዳግመኛ ልደት የሰው ልጅ በክብሩ ዙፋን በሚቀመጥበት ጊዜ፥ እናንተ ደግሞ በአሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገድ ስትፈርዱ በአሥራ ሁለት ዙፋን ትቀመጣላችሁ” (ማቴ 19፡28) በማለት ያከበረው ራሱ ኢየሱስ ክርስቶስ መኾኑን በትክክል እንዳስተማረ በቊ 32 ላይ ላይም “እግዚአብሔር የመረጣቸውን ማን ይከሳቸዋል?” በማለት ማንም ሊወቅሳቸው የማይችለውን ቅዱሳን ሐዋርያትን የመረጠው ፍጹም እግዚአብሔር የኾነው ኢየሱስ ክርስቶስ መኾኑን ገለጸ፡፡
የሚያጸድቅ እግዚአብሔር ነው፥ የሚኰንንስ ማን ነው?
ቅዱስ ጳውሎስ በትክክል በዚኽ ላይም ማጽደቅ እና መኰነን የሚችል ርሱ ልዑል እግዚአብሔር እንደኾነ በትክክል አስቀምጧል፤ እውነት ነው ዓለምን በታላቅ ግርማ አሳልፎ መላእክቱን አስከትሎ በዙፋኑ ተቀምጦ ለኹሉም እንደ የሥራው የሚከፍለው፤ ጻድቃንን በቀኙ አቁሞ “እናንተ የአባቴ ቡሩካን፥ ኑ፤ ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ” ብሎ የሚያጸድቅ፤ በግራው የቆሙትን ኃጥኣንን ደግሞ “እናንተ ርጉማን፥ ለሰይጣንና ለመላእክቱ ወደ ተዘጋጀ ወደ ዘላለም እሳት ከእኔ ሂዱ” በማለት የሚኰንነው ኢየሱስ ክርስቶስ ፍጹም እግዚአብሔር መኾኑን በትክክል ገለጸ፡፡ ራሱ ጌታ “የሰው ልጅ በክብሩ በሚመጣበት ጊዜ ከእርሱም ጋር ቅዱሳን መላእክቱ ሁሉ፥ በዚያን ጊዜ በክብሩ ዙፋን ይቀመጣል አሕዛብም ሁሉ በፊቱ ይሰበሰባሉ፤ እረኛም በጎቹን ከፍየሎች እንደሚለይ እርስ በርሳቸው ይለያቸዋል በጎችን በቀኙ ፍየሎችንም በግራው ያቆማቸዋል” በማለት እንዳስተማረን (ማቴ 25፡31-46)፡፡ ታዲያ ማጽደቅና እና መኰነን የፍርድ ሥራ እንጂ የማማለድ ሥራ ነውን በፍጹም አይደለም፡፡
“የሞተው ይልቁንም ከሙታን የተነሣው በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው”
ቅዱስ ጳውሎስ ሐዋርያትን የጠራው፣ የሚያጸድቀው የሚኰንነው ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔር መኾኑን በትክክል ካስረዳ በኋላ በመቀጠልም ሞትን ድል አድርጎ ተነሥቶ ባባቱ በእግዚአብሔር አብ ቀኝ መቀመጡን “የሞተው ይልቁንም ከሙታን የተነሣው በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው” በትክክል አስተማረ፤ ሞትን ድል አድርጎ ስለመነሣቱም ፊተኛው እና ኋለኛው ርሱ ስለመኾኑ ራሱ ጌታ “ፊተኛውና መጨረሻው ሕያውም እኔ ነኝ ሞቼም ነበርሁ እነሆም፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ሕያው ነኝ የሞትና የሲኦልም መክፈቻ አለኝ እንግዲህ ያየኸውን አሁንም ያለውን ከዚህም በኋላ ይሆን ዘንድ ያለውን ጻፍ” በማለት ይኽነን እውነት እንዲጽፍ ለዮሐንስ እንዳዘዘው ቅዱስ ጳውሎስም እውነቱን መሰከረ፡፡
ወንጌላዊ ማርቆስም ስለዚኽ ነገር “ጌታ ኢየሱስም ከእነርሱ ጋር ከተናገረ በኋላ ወደ ሰማይ ዐረገ በእግዚአብሔርም ቀኝ ተቀመጠ” (ማር 16፡19) በማለት ባባቱ ዕሪና መቀመጡን እንደነገረን ቅዱስ ጳውሎስም በድጋሚ ይኽነን አስተማረ፡፡
ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መዝሙረኛው ቅዱስ ዳዊት አስቀድሞ፡- “እግዚአብሔር ጌታዬን፡- ጠላቶችኽን በእግርኽ መረገጫ እስካደርግልኽ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ አለው” ብሎ እንደተነበየ /መዝ.፻፱ (፻፲)፡፩/ በአብ ቀኝ ተቀምጧል፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም ይኽ ትንቢት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እንደተፈጸመ አስተምሯል /ዕብ.፲፡፲፪/፡፡
ዓምደ ሃይማኖት የተባለው ቅዱስ ቄርሎስ ዘእስክንድርያ የሉቃስ ወንጌልን በተረጐመበት ፳፬ኛው ምዕራፍ ላይ ይኽን በተመለከተ ሲናገር እንዲኽ ይላል፡- “ደቀ መዛሙርቱን ከባረካቸው በኋላ ወደ ሰማይ ዐረገ፡፡ በአባቱ ቀኝ (ዕሪናም) ተቀመጠ፡፡ የተቀመጠውም በባሕርየ መለኮቱ ብቻ አይደለም፤ በተዋሐደው ሰውነቱም ጭምር እንጂ፡፡ አካላዊ ቃል ባሕርያችንን ሲዋሐድ እኛን ወደዚኽ ክብር ለመመለስ ነበርና፡፡ … እግዚአብሔር ሲኾን ስለ እኛ ሰው ኾነ፡፡ በፍቃዱ መከራ መስቀልን በተዋሐደው ሰውነቱ ተቀበለ፡፡ በተዋሐደው ሰውነቱ ሙስና መቃብርን አጥፍቶ ከሙታን ተለይቶ ተነሣ፡፡ በተዋሐደው ሰውነቱም ዐረገ፡፡ በሕያዋንና በሙታን ላይ ይፈርድ ዘንድም ዳግመኛ በክበበ ትስብእት ይመጣል” /Commentary on Luke, Chap.24/፡፡
አኹን ለመለኮት የተገደበ የተወሰነ ቀኝ ግራ ፊት ኋላ አለው ማለትም አይደለም ቀኝ ማለት ኀይል ምልአትን በዕሪና መተካከልን የሚያመለክት ብቻ ነው ሊቁ “እስመ ብሂለ የማን ይመርሕ ኀበ ተዋሕዶቶሙ ወዕሪናሆሙ በክብር” (ቀኝ ማለት በክብር መተካከላቸውን ተዋሕዶቸውን ያመለክታል) እንዳለ፤ እንግዳን “ንበር” (ተቀመጥ)፤ ይሉታል እንጂ እንደ ባለቤት “ነበረ” (ተቀመጠ) እንዳይሉት ለዐይን ጥቅሻ እንኳን ኢየሱስ ክርስቶስ ከክብሩ አልተለየምና “ነበረ” ይለዋል፤ ለዚኽ ነው ቅዱስ ጳውሎስ በዕብ 1፡3 ላይ “በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ” በማለት የጻፈው፡፡
እስኪ እንደ መጽሐፍ ቅዱሱ ቀኝ የሚለውን ኅሊናን በመሰብሰብ እንየው፡፡
“እግዚአብሔር ጌታዬን፦ ጠላቶችህን ለእግርህ መቀመጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ አለው እግዚአብሔር የኃይልን በትር ከጽዮን ይልክልሃል በጠላቶችህም መካከል ግዛ” (መዝ 109፡1)
“እኔ ነኝ እኔ ፊተኛው ነኝ እኔም ኋለኛው ነኝ እጄም ምድርን መሥርታለች ቀኜም ሰማያትን ዘርግታለች በጠራኋቸው ጊዜ በአንድነት ይቆማሉ (መዝ 48፡12-13)
እንኪያስ ዳዊት፦ ጌታ ጌታዬን። ጠላቶችህን የእግርህ መረገጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ አለው ሲል እንዴት በመንፈስ ጌታ ብሎ ይጠራዋል? ማቴ 22፡43-44
“አቤቱ፥ ቀኝህ በኃይል ከበረ” (ዘፀ 15፡6)
“አቤቱ፥ በአማልክት መካከል እንደ አንተ ያለ ማን ነው? ቀኝህን ዘረጋህ፥ ምድርም ዋጠቻቸው” (ዘፀ 15፡11-12)
“የእልልታና የመድኃኒት ድምፅ በጻድቃን ድንኳን ነው የእግዚአብሔር ቀኝ ኃይልን አደረገች የእግዚአብሔር ቀኝ ከፍ ከፍ አደረገችኝ የእግዚአብሔር ቀኝ ኃይልን አደረገች” መዝ 117፡15-16)
“ኢየሱስም፦ እኔ ነኝ፤ የሰው ልጅም በኃይል ቀኝ ሲቀመጥ በሰማይም ደመና ሲመጣ ታያላችሁ አለ” ማር 14፡62 ይላል፡፡
በመኾኑም ቅዱስ ጳውሎስ ቅዱሳን ሐዋርያቱን የጠራው የሚያጸድቀው የሚኰንነው ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔር ስለመኾኑና ሞትን ድል አድርጎ ተነሥቶ በአብ ቀኝ (ዕሪና) እንዳለ ከገለጸ በኋላ በዕለተ ዐርብ ባደረገው የድኅነት ምስጢር ዓለምን አድኖ ዋጋችንን የሰጠን ዳግመኛም በታላቅ ጌትነት ለፍርድ ተመልሶ የሚመጣው ኢየሱስ ክርስቶስ ነውና “ደግሞ ስለ እኛ የሚፈርደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው” በማለት በትክክል ተናገረ እንጂ፤ ምክንያቱም ከላይ ዠምሮ የጥቅሱን ሐሳብ እንዳየነው ሙሉ ነገሩ የክርስቶስን እግዚአብሔርነት፣ መራጭነት፣ አጽዳቂነት፣ ኰናኝነት፣ ሞትን ድል አድርጎ መነሣት፣ በአብ ዕሪና መቀመጥ ብቻ ነው፤ ታዲያ ራሱ ክርስቶስ ፍጹም እግዚአብሔር ከኾነና በአባቱ ዕሪና ከተቀመጠ በኋላ አንሶ ወደ ማን ሊማልድ ነው ይባላል? ወደ አብ ወደ መንፈስ ቅዱስ እንዳንል በአምላክነት፣ በፈጣሪነት፣ በቅድምና፣ በእግዚአብሔርነት፣ በዕበይ፣ በመንግሥት፣ በሥልጣን፣ በመመለክ፣ በመመስገን፣ በገናንነት፣ በክብር፣ በኀይል፣ በክሂል፣ በፈቃድ፣ በትእዛዝ አንድ ናቸው፡፡
ስለዚኽ ከጊዜ በኋላ እነዚኽ ቀሳጮች ምስጢረ ሥላሴን አፋልሰው የማይለየውን አንድነት ለመበታተን እንዲመቻቸው በማድረግ አስገብተውበታል እንጂ ክብር ይግባውና ጌታስ በዘመነ ሥጋዌዉ በዕለተ ዐርብ ባደረገው ተልእኮ ዓለምን ከራሱ፣ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አስታረቀ ዳግመኛም ታረቀ ከዚያም የማስታረቅን ቃል ለሐዋርያት ሰጥቶ በክብሩ ተቀመጠ ዳግመኛም በሕያዋንና በሙታን ላይ ለመፍረድ በጌትነት ይመጣል እንጂ አኹንም እንደገና ያደነውን ዓለም እንደገና እንዳልዳነ አኹንም መልሶ ይማልዳል ማለት ሎቱ ስብሐት ጠላት ዲያብሎስ የዘራው መርዝ ኑፋቄ ክሕደት ነው፡፡
ለዚኽ ነው ቅዱስ ጳውሎስ በ2ቆሮ 5፡18-20 “ነገር ግን የሆነው ሁሉ፥ በክርስቶስ ከራሱ ጋር ካስታረቀን የማስታረቅም አገልግሎት ከሰጠን፥ ከእግዚአብሔር ነው እግዚአብሔር በክርስቶስ ሆኖ ዓለሙን ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበርና፥ በደላቸውን አይቆጥርባቸውም ነበር፤ በእኛም የማስታረቅ ቃል አኖረ እንግዲህ እግዚአብሔር በእኛ እንደሚማለድ ስለ ክርስቶስ መልክተኞች ነን፤ ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ ብለን ስለ ክርስቶስ እንለምናለን” በማለት የማስታረቅ አገልግሎት ለቅዱሳን ሐዋርያት ለቤተ ክርስቲያን አበው የተሰጠ መኾኑን ትክክለኛውን ትምህርት ያስተማረው፡፡

ከመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ

ነገረ ክርስቶስ ከሚለው መጽሐፌ የተወሰደ
ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ የቀናውን እውነት የኾነውን የሐዋርያትን ትምህርት ሳትበርዝ ሳትከልስ ሳትቈራርጥ ያስተማረችውን በደምህ የመሠረትካትን ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችንን ጠብቅልን፡
 http://orthodoxt.zetewahedo.org/2016/01/1986_38.html

ብሂለ አበው -

ብሂለ አበዉ
·         ‹‹እግዚአብሔር ሆይ አፈርና ትቢያ ሆኜ ሳለ ጻድቅ አድርገው  ከሚቆጥሩኝ ሰዎች አድነኝ›› 
አባ እንጦንስ
·         ‹‹ፍጡራንን መርምሮ ማወቅ ካልተቻልን ሁሉን የፈጠረ እርሱን መርምሮ ማወቅ እንደምን ይቻልናል››     
  ቅዱስ አትናቴዎስ
·         ‹‹ወርቅ በእሳት እንደሚፈተን ሁሉ የክርስቶስንም ፀጋና ክብር ሳይፈተኑ ማግኘት አይቻልም የዚህ ዓለም ፈተናና እሳት ቶሎ ያልፋል ይጠፋል ኃጢያተኞች የሚገቡበት የገሀነም እሳት ግን ለዘላለም እንደ ነደደ ይኖራል››             
        ቅዱስ ሚናስ
·         ‹‹በማንም ላይ ክፈትን አትስሩ አትፍርዱ ይህንን ከጠበቃችሁ ርስቱን ትወርሳላችሁና›› 
        ታላቁ አባ መቃርስ
·         ‹‹ብዙ ጊዜ ብዙ እናገራለሁ በመናገሬም አዝናልሁ በዝምታዬ ግን ያዘንኩበት ጊዜ የለም››
  ቅዱስ አርሳንዮስ
·         ‹‹ቤተክርስትያን መጠጊያችን ነች ቤተክርስትያን የኖኅ መርክብ ነች በውስጧ እንጠለላልን ከውጭዋ ግን ማዕበልና ቀላያት ተከፍተዋል››              
        ቅዱስ እንድርያስ
·         ‹‹ልባችንን ጠፊና በስባሽ ከኾነው ከምድራዊው ምኞት አርቀን ከበደል በንስሐ ነጹሕ ካደረግነው በጸጋ መንፈስቅዱስ የተሞላን እንሆናለን››                           
  አባ አብርሃም መፍቀሬ ነዳያን
·         ‹‹ስጋዊ ፍላጎቶችን ማሸነፍ ለአክሊለ ህይወት የሚያበቃ ሰማዕትነት ነው››  
  ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ
·         ‹‹የቤተክርስቲያን ህይወት በመስቀል ላይ ስለሆነ ፈተና ይበዛበታል ስለዚህ ከግል ህይወታችሁ ይልቅ የቤተክርስቲያናችሁን አቋም አጠንክሩ››    
  ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ
·         ‹‹ከመኝታህ በፊት የምታደርገውን ፀሎት ትተህ እንድትተኛ መንፈስህ ሲገፋፋህ እሺ ብለህ አትቀበለው፡፡ እንዲያውም መዝሙረ ዳዊትን ጨምርና ሌሊቱን በሙሉ ስትፀልይ እደር›› 
  ቅዱስ ይስሀቅ ሶርያዊ
·         ‹‹ኃጥያታችንን እኛ እያሰብን የምንፀፀት ከሆነ እግዚአብሔር ይረሳልናል  ኃጥያታችንን እኛ እረስትን የምንፅናና ከሆነ እግዚአብሔር ያስብብናል››
  ቅዱስ እንጦስ   

o   ለተወሰን ጊዜ ለሀይማኖት መከራከር፤ጠበቃ መሆን፤መዋጋት ብሎም መሞት አይከፋም ሁልጊዜ ለሀይማኖት መኖር ግን ከሁሉ የበለጠ መስዋእትና ክብር ያለው ህይወት ነው፡፡

o   የረብዑ ምግብ ለሀሙስ የአርብ ምግብ ለቅዳሜ ይጠቅማል ነገር ግን የማክሰኞ ምግብ ለረብዑ አይጠቅምም የሀሙስ ምግብ ለአርብ አይሆንም የነፍስና የስጋ ነገርም እዲሁ ነው፡፡


o   የነፍሳችን ነገር ትተን የስጋችንን ብቻ የምናደልብ ከሆነ ነፍስን በስጋ መቃብር እየቀበርናት መሆኑን አንርሳ

o   አንድ በርሜል ወተት በአንድ ጠብታ ኮምጣጤ የበጣጠሳል የብዙ ጊዜ ተጋድሎንም ጠብታ የሀጢያት ኮምጣጤ ያበላሸዋል


o   ራስህን በሀሰት አትውቀስ፡፡ራስህ መክሰስ ትህትና አይደለም፡፡ ታላቅ ትህትና ሰዎች ሲወቅሱህ መታገስ ነው

o   ትዕቢት ሰይጣን ያለመው ጦር ነው

o   ትህትና ህፀፅን የምታስታውቅ መስታወት ናት

o   ክርስትና ማለት የሰውን ሸክም መሸከምና እስከሞት ድረስ መፅናት ማለት ነው

o   በባልንጀራው ላይ ክፋትን የሚያስብ ሰው ያችው የሚያስባት ክፋት ራሱን ትጎዳዋለች፡፡ በየትና ምን ጊዜ እደምትጥለው ግን አያውቅም

o   ስንፍናውን ወደጥበብ፤አላዋቂነቱን ወደእውቀት ፤መጥፎ ጠባዩን ወደበጎነት የሚመልስ ሰው ብርቱ ነው

o   ፀሎት ገንዘብን ሊያመጣ ይችላል፡፡ ገንዘብ ግን ፀሎትን አያመጣም፡፡
 ብሂለ አበው
ò ራስህን በሐሰት አትውቀስ ራስን መክሰስ ትህትና አይደለም ታላቁ ትህትና ሰዎች ሲወቅሱህ መታገስ   ነው፡፡                 
   ቅዱስ ስራፕዮን
ò የማታምንበትን ነገር ለሰው ስትል አትስራው ከሰራኸው እንደምትጠፋበት እወቅ ፡፡                                
   መጽሐፈ ምክር
ò አንደበቱን ከቧልት ከሐሜት ያየውንም ሚስጥር ከመናገር የሚከለከል ሰው ልቦናውን ከኀልዮ ኃጥያት ያርቀዋል፡፡
   አረጋዊ መንፈሳዊ
ò ጸጋ ቢሰጥህ በተሰጠህ ጸጋ አመስግን ያልተሰጠህን እሻለሁ በማለት የተሰጠህን እንዳታጣ፡፡
  ማር ይስሐቅ
ò ራሱን የሚንቅ የሚያቃልል ሰው ከእግዚአብሔር ዘንድ እውቀትን ያገኛል     አዋቂ ነኝ የሚል ሰው ከፈጣሪው ጥበብ ይለየዋል፡፡                     
  አረጋዊ መንፈሳዊ

ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያናችን በአባቶች አንደበት
§  ‹‹ሰውን ብትታገልና ብትዋጋ ታሸንፈዋለህ ወይም ያሸንፍሃል ቤተክርስቲያንን ግን ለማሸነፍ አይቻልም ቤተክርስቲያን ሁል ጊዜ ትዋጋለች ተሸንፋ ግን አታውቅም ዲያቢሎስ ዝናሩን አራገፈ ቀስቱን ጨረሰ ቤተክርስቲያንን ግን አልጎዳትም፡፡››
                                  የቁስጥንጥንያው ሊቀ ጳጳስ ዮሐንስ አፈወርቅ
                                                       የቤ/ክ/ታሪክ በዓለም መድረክ ገጽ 40
§  ‹‹ቤተክርስቲያንን ከክርስቶስ የሚለይ የለም ክርስቶስ ከቤተክርስቲያን እንደማይለይ ቃል ገብቷልና ስለዚህ ማንኛውም የጉዞ አቀበትና ቁልቁለት ቢያጋጥማትም ከክርስቶስ ጋር ያለች ቤተክርስቲያን አትደነግጥም በካታኩንቦ ብትቀድስም በወርቅ በተለበጠ በሐር በተንቆጠቆጠ ቤተመቅደስም ብትቀድስ ቤተክርስቲያን የክርስቶስ ናት፡፡››
                                            ብጹዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ
                                                       የቤ/ክ/ታሪክ በዓለም መድረክ ገጽ 9

§  ‹‹እግዚአብሔር ሆይ አፈርና ትቢያ ሆኜ ሳለ ጻድቅ አድርገው  ከሚቆጥሩኝ ሰዎች አድነኝ››     
አባ እንጦንስ
§  ‹‹ፍጡራንን መርምሮ ማወቅ ካልተቻልን ሁሉን የፈጠረ እርሱን መርምሮ ማወቅ እንደምን ይቻልናል›› 
ቅዱስ አትናቴዎስ
§  ‹‹ወርቅ በእሳት እንደሚፈተን ሁሉ የክርስቶስንም ፀጋና ክብር ሳይፈተኑ ማግኘት አይቻልም የዚህ ዓለም ፈተናና እሳት ቶሎ ያልፋል ይጠፋል ኃጢያተኞች የሚገቡበት የገሀነም እሳት ግን ለዘላለም እንደ ነደደ ይኖራል››  
ቅዱስ ሚናስ
§  ‹‹በማንም ላይ ክፈትን አትስሩ አትፍርዱ ይህንን ከጠበቃችሁ ርስቱን ትወርሳላችሁና››             
ታላቁ አባ መቃርስ
§  ‹‹ብዙ ጊዜ ብዙ እናገራለሁ በመናገሬም አዝናልሁ በዝምታዬ ግን ያዘንኩበት ጊዜ የለም››
ቅዱስ አርሳንዮስ
§  ‹‹ቤተክርስትያን መጠጊያችን ነች ቤተክርስትያን የኖኅ መርክብ ነች በውስጧ እንጠለላልን ከውጭዋ ግን ማዕበልና ቀላያት ተከፍተዋል››  
ቅዱስ እንድርያስ
§  ‹‹ልባችንን ጠፊና በስባሽ ከኾነው ከምድራዊው ምኞት አርቀን ከበደል በንስሐ ነጹሕ ካደረግነው በጸጋ መንፈስቅዱስ የተሞላን እንሆናለን››
አባ አብርሃም መፍቀሬ ነዳያን
§  ‹‹ስጋዊ ፍላጎቶችን ማሸነፍ ለአክሊለ ህይወት የሚያበቃ ሰማዕትነት ነው››
ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ
§  ‹‹የቤተክርስቲያን ህይወት በመስቀል ላይ ስለሆነ ፈተና ይበዛበታል ስለዚህ ከግል ህይወታችሁ ይልቅ የቤተክርስቲያናችሁን አቋም አጠንክሩ››
ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ
§  ‹‹ከመኝታህ በፊት የምታደርገውን ፀሎት ትተህ እንድትተኛ መንፈስህ ሲገፋፋህ እሺ ብለህ አትቀበለው፡፡ እንዲያውም መዝሙረ ዳዊትን ጨምርና ሌሊቱን በሙሉ ስትፀልይ እደር››
ቅዱስ ይስሀቅ ሶርያዊ
§  ‹‹ኃጥያታችንን እኛ እያሰብን የምንፀፀት ከሆነ እግዚአብሔር ይረሳልናል  ኃጥያታችንን እኛ እረስትን የምንፅናና ከሆነ እግዚአብሔር ያስብብናል›› 
ቅዱስ እንጦስ

+    ከከመኝታህ በፊት የምታደርገውን ጸሎት ትተህ እንድትተኛ መንፈስህ ሲገፋፋህ እሺ ብለህ አትቀበለው እንደውም መዝሙረ ዳዊትን ጨምሮ ሌሊቱን በሙሉ ስትጸልይ እደር፡፡
+ አንዲት ቀዳዳ አንድን ትልቅ መርከብ ታሰምጠዋለች አንዲት ኃጢአት አንድን ትልቅ ሰው ለውርደት ልታበቃው ትችላለች፡፡
+ ኃጢአትን መደበቅ ራሱ ኃጢአት ነው፡፡       ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ
+ ንስሐ ሥጋዊውን ፍላጎት በመንፈሳዊ ፍላጎት መተካት ነው፡፡

  • በሰው እጅ ያልተፈተለና ያልተሸመነ የደጋ ልብሳችን፣ የእርቃናችን መሸፈኛ፣ ጌጥ እና ክብራችን፣ ሊጡ አእምሮ የቦካበት አዲሱ እርሾ፣ አልጫውን ያጣፈጠ ጨው እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡
/አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ/
  • በድንግልና መኖር የሚችሉ መጋባትም መውለድም የለባቸውም በሌላ በኩል ደግሞ በድንግልና መኖር የማይችሉ ቢኖሩ ነውር በሆነ መንገድ እንዳይወልዱ ወይም ለመውለድ ሳይፈልጉ ይበልጥ ነውር በሆነ መንገድ ከሌላይቱ ሴት ጋር እንዳይተኙ በሕጋዊ መንገድ ጋብቻን ይፈጽሙ ልጅ ላለመውለድ የጽንስ መከላከያን የሚጠቀሙ ባለትዳሮች ሁሉ ሥራቸው ነውር እና ስህተት ነው፡፡ ልጆች መውለድን በመከላከል ድክመታቸውን በመሸፈን መመከር አይኖርባቸውም፡፡
/ቅዱስ አውጉስጢን/
  • ሥጋን በንዳድ ሌላም ልዩ ልዩ ደዌ በያዘው ጊዜ ምንም ብርቱ ቢሆን እንደሚደክምና ከበሽታው በዳነ ጊዜ ግን ኃይሉ እንደሚመለስለትና እንዲሁ  ነፍሱም በወጣትነት ወራት በደዌ ኃጢአት ትያዛለች፡፡ ትዕቢተኛነት፣ ሥጋዬ ይድላው ማለት በጾታ መፈላለግንና ይህን በመሳሰሉ ብዙ የምኞት ጣዕም ያድርባታል የእርጅና ወራት በደረሰ ጊዜ ግን ፈቃደ ሥጋን ፈጽሞ ከሰውነቱ ይርቃል፡፡
/ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ/
  • ‹‹ሌሊት በህልም ከሴት ጋር የተገናኘህ /ዝሙት የፈጸምህ/ መስሎህ ዘር ቢወርድህ በመዓልት /በቀን/ አታስባት፡፡›› እንዲህ ማድረግህ ደግሞ በህልም የተመለከትከውን በእውን፣ እያሰብከው ደስታ ከማድረግ ይጠብቅሃል፡፡
/ከመጽሐፈ መነኩሳት/
  • ብፅዕት ማርያም፣ በእድሜ ትንሽ በመኖኗ ከሴቶች መካከል ተለይታ ቡርክት ለመሆን አልከለከላትም፡፡
/መጽሐፈ ፊልክስዮስ ክፍል 4 ተሰዕሎ 47/
  • በአፉ ከእግዚአብሔር በልቡ ከዓለም መነጋገሩ ከንጉሱ በፊት ቆሞ ሲነጋገር ዞሮ ከሌላ ቢጫወት ቅጣት እንደሚያገኘው እንዲሁም ልቡን ሳይጠቀልል የሚጸልይ ሰው አምላኩን የሚንቅ እና የሚያቃልል ስለሆነ ቅጣቱ እጅግ ያስፈራል፡፡
/ፍኖተ አእምሮ ገፅ 49/
  • ሥጋን የሚገድሉትን ነፍስን ግን መግደል የማይቻላቸውን አትፍሩ ይልቅስ ነፍስንም ሥጋንም በገሃነም ሊያጠፋ የሚችለውን ፍሩ፡፡
/ማቴ. 10፥28

  • ‹‹የማታምንበትን ነገር ለሰው ስትል አትሥራው ከሰራኸው እንደምትጠፋበት ዕወቅ››
መጽሐፈ ምክር
  • ‹‹የቤተክርስቲያን ሕይወት መስቀል ላይ ስለሆነ ፈተና ይበዛበታል፡፡ ስለዚህ ከግል ሕይወታችሁ ይልቅ የቤተክርስቲያንን አቋም አጠንክሩ፡፡››
ብጹዕ አቡነ ጎርጎሪዎስ ካልዕ
  • ‹‹የረቡዕ ምግብ ለሐሙስ የአርብ ምግብ ለቅዳሜ ይጠቅማል ነገር ግን የማክሰኞ ምግብ ለረቡዕ አይጠቅምም የሐሙስ ምግብም ለአርብ አይሆንም የነፍስና የሥጋ ነገርም እንዲሁ ነው፡፡››
አባ ጴሜን
  • ‹‹ሐዋርያት በልሳን የመናገር ጸጋ የተሰጣቸው በዓለም ዞረው ወንጌልን እንዲያስተምሩ ነው፡፡››
ዮሐንስ አፈወርቅ
http://hohitebirhan.org/index.php/kinetebeb/2010-05-30-22-42-19/115-7