እመቤታችን የት ተወለደች?
እመቤታችን ስለተወለደችበት ስፍራ በዓለም የተለያዩ ሀሳቦች ሲሰነዘሩ ቆይተዋል፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ሁለት ሀሳቦች የሚያነሡ ሲሆን አንደኛው “ድንግል ማርያም ብስራተ መልአክ በሰማችበት ናዝሬት ተወልዳለች” የሚል ነው፡፡ ሁለተኛው ሀሳብ ደግሞ “ከሦስተኛው ክ/ዘመን ወዲህ የማርያም መግቢያ ተብሎ በሚታወቀው ከኢየሩሳሌም የቅድስት ሀና የክሩሲድ ቤተ ክርስቲያን በታች ነው የተወለደችው” የሚል መላ ምታዊ አመለካከት ነው፡
የኮፕቲክ (ግብጽ) ስንክሳር “የእመቤታችን የትውልድ ስፍራ በናዝሬት ነው”
ይላል፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስንክሳር ግን በቀደምትነታቸው ተጠብቀው የቆዩ ከመሆናቸው
አንጻር ተአማኒነታቸው የጎላ መሆኑን ያሳያል፡፡ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን መጻሕፍት የእመቤታችን የትውልድ ስፍራ
ሊባኖስ የተባለው ተራራማ ሀገር ነው፡፡ ሊባኖስ ከገሊላ በስተ ሰሜንና ከፍንቄ በስተ ምስራቅ ይገኛል፡፡ “ሙሽራየ ሆይ ከሊባኖስ ከእኔ ጋር ነይ” የሚለው ቃለ ትንቢት ምስጢርም የአመቤታችን መካነ ልደት የሊባኖስ ተራራ ስለመሆኑ የሚያጠይቅ እንደሆነ ምስክርነታቸው የታመነ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ያስረዳሉ፡፡ /መኃ 4፥7/፡፡

የእመቤታችን የትውልድ ሀረግ
በእግዚአብሔር ፊት የተወደዱ በምግባር በሃይማኖት ጸንተው ይኖሩ
የነበሩ የእመቤታችን ቅድመ አያቶች ቴክታና በጥሪቃ ይባላሉ፡፡ ይህ ቀራቸው የማይባሉ ባለጸጎች ነበሩ፡፡ የሃብታቸው
ብዛት ሥፍር ቁጥር አልነበረውም፡፡
ከዕለታት ባንደኛው ቀን ቴክታ ወደ ቤተ መዛግብቱ ገብቶ የገንዘቡን ብዛት ሲያይ “እኔ መካን አንቺም መካን ይህ ሁሉ ገንዘብ ለማን ይሆናል?” አላት፡፡ “እግዚአብሔር ከእኔ ልጅ ባይሰጥህ ሌላ አግብተህ ትወልድ ዘንድ ፈቅጄልሃለሁ” አለችው፡፡ “ይህን እንዳላደርገው አምላከ እስራኤል ያውቃል”
አላት፡፡ በዚህ እያዘኑ ሳለ ወዲያው ራእይ ታያቸው፡፡ ይህም ነጭ እንቦሳ ከበረታቸው ስትወጣ እንቦሳይቱ እንቦሳ
እየወረደች እስከ ስድስት ስትደርስ ስድስተኛይቱ ጨረቃን፣ ጨረቃ ፀሐይን ስትወልድ አይተው በሀገራቸው ወደ ነበረው
ሕልም ፈቺ ሔደው ነገሩት፡፡ በእግዚአብሔር መንፈስ የተቃኘው ሕልም ፈቺም ‹‹ደግ ልጅ ትወልዳላችሁ፡፡ ጨረቃይቱ
ከፍጡራን በላይ የምትሆን ልጅ ነች፡፡ የፀሐዩ ነገር ግን አልተገለጸልኝም›› አላቸው፡፡ እነሱም ይህንን ጊዜ ይፍታው
ብለው ወደ ቤታቸው ሔዱ፡፡ ከዚህ በኋላ በጥሪቃ ፀነሰች፤ ወለደችም፤ ሄኤሜን አለቻት፡፡ ሄኤሜን ዴርዴን፣ ዴርዴ
ቶናን፣ ቶና ሲካርን፣ ሲካር ሄርሜላን፣ ሄርሜላ ሐናን ወለደች፡፡
ሐና ማለት በሃይማኖት በምግባር የጸናች፤ በንጽሕና በቅድስና
የተሸለመች ቡርክት ክብርት ደግ ፍጥረት ማለት ነው፡፡ ይህችን በምግባር በሃይማኖት ተኮትኩታ ያደገች ሴት አካለ
መጠን ስትደርስ ከቤተ ይሁዳ ለተወለደው ኢያቄብ ለሚባል ደግ ሰው አጋቧት፡፡ ሐናና ኢያቄብ በፍቅርና በደስታ
ኑሮአቸውን ቢመሩም በአያታቸው የደረሰው መካንነት በእነሱም ላይ ደረሰ፡፡ በተሰበረ ልብ እግዚአብሔር የሐናን ማሕፀን
ይከፍት ዘንድ በጸሎት ይማጸኑት ጀመር፡፡ የሐና ጎረቤት የሆነች በዝሙት ሥራ የምትኖር አንዲት ሴት ነበረች፡፡
ሐናም ቀረብ ብላ “ዛሬ ቤተ እግዚአብሔር ስስማለሁ ብዬ ነበር፤ ነገር ግን የምለብሰው ልብስ የለኝም” አለቻት፡፡
ይቺም ሴት መልሳ “ካንድም ሁለት ሦስት የእኔ ልብስ አለልሽ፤ ያን ለብሰሽ ለምን አትሔጅም?” ብትላት ሐና ግን “በኃጢአት ሥራ የተገኘ ልብስ ነው፡፡ እግዚአብሔር ንጹሐ ባሕርይ ስለሆነ ይህ አይሆንልኝም” ብላ
መለሰችላት፡፡ ይህቺ ሴት ከኃጢአት ሥራዋ ታርማ የጽድቅ ሥራ ለመሥራት ለማሰብ ይልቅ ልብ የሚነካ ነገር
ተናገረቻት፤ “በምን ምክንያት ልጅ ነሳሽ ብዬ ሳዝን ነበር፤ ለካ እንደ ድንጋይ አድርቆ ያስቀረሽ ይህ ክፋትሽ
ነው!” በዚህ ንግግሯ ሐና እጅግ አዘነች፡፡

በሌላ ጊዜም ከቧላ ከኢያቄም ጋር ቤተ መቅደስ ሔደው መስዋዕት ለማቅረብ ሲሔዱ ሊቀ ካህናቱ ሮቤል “የመካኖች መስዋዕት አትቅበል ይላል፤ እናንተ ብዙ ተባዙ ምድርንም ሙሏት ያለውን የአዳምን ቃል ያስቀረባችሁ አይደላችሁንም? እግዚአብሔር ቢጠላችሁ እንጂ ቢወዳችሁማ ልጅ በሰጣችሁ፤ መስዋዕቱንም ለማቅረብ እድል ባገኛችሁ” ብሎ መለሳቸው፡፡ በዚህ አዝነው ዛፍ ሥር ተቀምጠው ሳለ ርግቦች ከልጆቻቸው ጋር ሲጨዋወቱ ዕፀዋት አብበው አፍርተው አዩ፡፡ በዚህን ጊዜ እንዲህ ብለው ጸለዩ “ርግቦችን እንዲራቡ ዕፀዋትም እንዲያብቡና እንዲያፈሩ የምታደርግ የእኛ ተፈጥሮ ከድንጋይ ስለሆነ ነው ልጅ የነሳኸን?”ብለው
አዘኑ፡፡ ከዚህ በኋላ ሐናና ኢያቄም የለመኑትን ለማይነሳ የነገሩትን ለማይረሳ አምላክ ብትአታቸውን (ሥለታቸውን)
አስነቡና ‹‹ወንድ ልጅ ብንወልድ ወጥቶ ወርዶ አርሶ ቆፍሮ ይርዳን አንልም ለቤተ እግዚአብሔር አንጣፊ ጋራጅ
ይሆናል፡፡ ሴት ብንወልድ እንጨት ሰብራ ውኃ ቀድታ ትርዳን አንልም ለቤተ እግዚአብሔር መሶበ ወርቅ ሰፍታ መጋረጃ
ፈትላ ትኑር›› በማለት ለመኑ፡፡ ሐምሌ 30 ቀን ድንቅ ሕልም ተመለከቱ ከአንድ ሱባኤ በኋላ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል
“ደግ ልጅ ትወልዳላችሁ” በማለት አበሠራቸው፡፡ በፈቃደ እግዚአብሔር በቅዱስ ገብርኤል አብሣሪነት እመቤታችን ነሐሴ ሰባት ቀን ተፀነሰች
አይሁድ ለምቀኝነት አያርፉምና ከዚህ ቀደም ከነሱ ወገን የሚሆኑ
ዳዊትና ሰሎሞን አርባ አርባ ዘመን እንሰም አቅልጠው እንደገል ቀጥቅጠው ገዙን፤ ከእነሱ ደግሞ የሚወለደውን እንደምን
ያደርገን ይሆን? ብለው በጠላትነት ተነሱባቸው፡፡ በመልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ትእዛዝና መሪነት ቅዱስ ኢያቄምና
ቅድስት ሐና ወደ ሊባኖስ ተራራ ወጡ፡፡ ቅዱስ ዳዊት በመዝሙሩ “መሠረቶቹ በተቀደሱ ተራሮች ናቸው” ብሎ እንደተናገረው ከተቀደሱ ወላጆቿ ግንቦት 1 ቀን በተራራው ላይ ሳሉ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተወለደች /መዝ. 86፥1/፡፡
ቅዱስ ያሬድ በአንቀጸ ብርሃን ጸሎቱ “ጸጋን የተመላሽና የደስታ መገኛ ሆይ ዓይኖቻቸው ብዙዎች ከሚሆኑ ከኪሩቤልና ክንፎቻቸው ስድስት ከሆኑ ከሱራፌል ግርማ የሚበልጥ የመወደድ ግርማ አለሽ፡፡ እነዚያ ፊታቸውን ይሸፍናሉ… ከልጅሽ መለኮት ከሚወጣው እሳት ይድኑ ዘንድ፤ አንቺ ግን የመለኮት ማደሪያ ሆንሽ፤ የመለኮት ባሕርይም ሥጋሽን አላቃጠለውም፤ የእሳት ነበልባልን ተሸከምሽ” ብሏታል፡
በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት መሠረት ሃና እና ኢያቄም ከአይሁድ ለማምለጥ ተሰደው በአድባረ ሊባኖስ ሥር እመቤታችንን ወለዱ በወቅቱ ከቤት የወጡት ለሽሽት ነበርና ስንቅ ስላልያዙ ምግባቸው “ንፍሮና ጥራጥሬ”
ነበር፡፡ይኼንን ትውፊት በመያዝ በዓሉ ከቤት ውጭ ንፍሮ እየተበላ ይከበራል፡፡ ሆኖም በበጎ ነገሮች ሰበብ ክፉ
ዓላማውን ማስፈጸም የሚፈልገው ዲያብሎስ በማር መሃል መርዝን ከሚጨምርባቸው መንፈሳዊያት በዓላት አንዱ የግንቦት
ልደታ የእመቤታችን በዓል ነው፡፡ አንዳንዶች በድፍረት ለአድባር ለውጋር ነው፣ቆሌውን ለመለመን ነው፣ እያሉ ንፍሮ
የሚበትኑ፣ቡና የሚረጩ፣ቂቤ የሚቀቡ፣የከብት ደም የሚያፈሱ፣ እነዚህ በእርግጥም ጣዖት አምላኪዎች ናቸው፡፡
ሃይማኖታዊ ሥርዐት እያደገ ጠቃሚ ባህል ወደ መሆን ለመወጡ ደስ
ያሰኛል፡፡ ወገኖቻችንም በእመቤታችን የልደት ቀን የተቸገረውን በመርዳት በዓሏን ለማክበር ሚያደርጉት ጥረት መልካም
በመሆኑ ሊበረታታ ይገባዋል፡፡ በልደታ ማርያም በዓል ሰበብ የሚደረግ ጣዖት የማምለክ ሥርዐት ካለ ደግሞ የቤተ
ክርስቲያናችን ትውፊት አይደለምና እናውግዘው፡፡ ስለሆነም ይኼንን ታላቅ በዓል በተገባና በተረዳ ነገር እንድናከብረው
የእመቤታችን ረድኤት በረከት አይለየን፡፡ አሜን!!
በእግዚአብሔር ፊት የተወደዱ በምግባር በሃይማኖት ጸንተው ይኖሩ
የነበሩ የእመቤታችን ቅድመ አያቶች ቴክታና በጥሪቃ ይባላሉ፡፡ ይህ ቀራቸው የማይባሉ ባለጸጎች ነበሩ፡፡ የሃብታቸው
ብዛት ሥፍር ቁጥር አልነበረውም፡፡
ከዕለታት ባንደኛው ቀን ቴክታ ወደ ቤተ መዛግብቱ ገብቶ የገንዘቡን ብዛት ሲያይ “እኔ መካን አንቺም መካን ይህ ሁሉ ገንዘብ ለማን ይሆናል?” አላት፡፡ “እግዚአብሔር ከእኔ ልጅ ባይሰጥህ ሌላ አግብተህ ትወልድ ዘንድ ፈቅጄልሃለሁ” አለችው፡፡ “ይህን እንዳላደርገው አምላከ እስራኤል ያውቃል” አላት፡፡
በዚህ እያዘኑ ሳለ ወዲያው ራእይ ታያቸው፡፡ ይህም ነጭ እንቦሳ ከበረታቸው ስትወጣ እንቦሳይቱ እንቦሳ እየወረደች
እስከ ስድስት ስትደርስ ስድስተኛይቱ ጨረቃን፣ ጨረቃ ፀሐይን ስትወልድ አይተው በሀገራቸው ወደ ነበረው ሕልም ፈቺ
ሔደው ነገሩት፡፡ በእግዚአብሔር መንፈስ የተቃኘው ሕልም ፈቺም ‹‹ደግ ልጅ ትወልዳላችሁ፡፡ ጨረቃይቱ ከፍጡራን በላይ
የምትሆን ልጅ ነች፡፡ የፀሐዩ ነገር ግን አልተገለጸልኝም›› አላቸው፡፡ እነሱም ይህንን ጊዜ ይፍታው ብለው ወደ
ቤታቸው ሔዱ፡፡ ከዚህ በኋላ በጥሪቃ ፀነሰች፤ ወለደችም፤ ሄኤሜን አለቻት፡፡ ሄኤሜን ዴርዴን፣ ዴርዴ ቶናን፣ ቶና
ሲካርን፣ ሲካር ሄርሜላን፣ ሄርሜላ ሐናን ወለደች፡፡
ሐና ማለት በሃይማኖት በምግባር የጸናች፤ በንጽሕና በቅድስና
የተሸለመች ቡርክት ክብርት ደግ ፍጥረት ማለት ነው፡፡ ይህችን በምግባር በሃይማኖት ተኮትኩታ ያደገች ሴት አካለ
መጠን ስትደርስ ከቤተ ይሁዳ ለተወለደው ኢያቄብ ለሚባል ደግ ሰው አጋቧት፡፡ ሐናና ኢያቄብ በፍቅርና በደስታ
ኑሮአቸውን ቢመሩም በአያታቸው የደረሰው መካንነት በእነሱም ላይ ደረሰ፡፡ በተሰበረ ልብ እግዚአብሔር የሐናን ማሕፀን
ይከፍት ዘንድ በጸሎት ይማጸኑት ጀመር፡፡ የሐና ጎረቤት የሆነች በዝሙት ሥራ የምትኖር አንዲት ሴት ነበረች፡፡
ሐናም ቀረብ ብላ “ዛሬ ቤተ እግዚአብሔር ስስማለሁ ብዬ ነበር፤ ነገር ግን የምለብሰው ልብስ የለኝም” አለቻት፡፡
ይቺም ሴት መልሳ “ካንድም ሁለት ሦስት የእኔ ልብስ አለልሽ፤ ያን ለብሰሽ ለምን አትሔጅም?” ብትላት ሐና ግን “በኃጢአት ሥራ የተገኘ ልብስ ነው፡፡ እግዚአብሔር ንጹሐ ባሕርይ ስለሆነ ይህ አይሆንልኝም” ብላ
መለሰችላት፡፡ ይህቺ ሴት ከኃጢአት ሥራዋ ታርማ የጽድቅ ሥራ ለመሥራት ለማሰብ ይልቅ ልብ የሚነካ ነገር
ተናገረቻት፤ “በምን ምክንያት ልጅ ነሳሽ ብዬ ሳዝን ነበር፤ ለካ እንደ ድንጋይ አድርቆ ያስቀረሽ ይህ ክፋትሽ
ነው!” በዚህ ንግግሯ ሐና እጅግ አዘነች፡፡
በሌላ ጊዜም ከቧላ ከኢያቄም ጋር ቤተ መቅደስ ሔደው መስዋዕት ለማቅረብ ሲሔዱ ሊቀ ካህናቱ ሮቤል “የመካኖች መስዋዕት አትቅበል ይላል፤ እናንተ ብዙ ተባዙ ምድርንም ሙሏት ያለውን የአዳምን ቃል ያስቀረባችሁ አይደላችሁንም? እግዚአብሔር ቢጠላችሁ እንጂ ቢወዳችሁማ ልጅ በሰጣችሁ፤ መስዋዕቱንም ለማቅረብ እድል ባገኛችሁ” ብሎ መለሳቸው፡፡ በዚህ አዝነው ዛፍ ሥር ተቀምጠው ሳለ ርግቦች ከልጆቻቸው ጋር ሲጨዋወቱ ዕፀዋት አብበው አፍርተው አዩ፡፡ በዚህን ጊዜ እንዲህ ብለው ጸለዩ “ርግቦችን እንዲራቡ ዕፀዋትም እንዲያብቡና እንዲያፈሩ የምታደርግ የእኛ ተፈጥሮ ከድንጋይ ስለሆነ ነው ልጅ የነሳኸን?”ብለው
አዘኑ፡፡ ከዚህ በኋላ ሐናና ኢያቄም የለመኑትን ለማይነሳ የነገሩትን ለማይረሳ አምላክ ብትአታቸውን (ሥለታቸውን)
አስነቡና ‹‹ወንድ ልጅ ብንወልድ ወጥቶ ወርዶ አርሶ ቆፍሮ ይርዳን አንልም ለቤተ እግዚአብሔር አንጣፊ ጋራጅ
ይሆናል፡፡ ሴት ብንወልድ እንጨት ሰብራ ውኃ ቀድታ ትርዳን አንልም ለቤተ እግዚአብሔር መሶበ ወርቅ ሰፍታ መጋረጃ
ፈትላ ትኑር›› በማለት ለመኑ፡፡ ሐምሌ 30 ቀን ድንቅ ሕልም ተመለከቱ ከአንድ ሱባኤ በኋላ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል
“ደግ ልጅ ትወልዳላችሁ” በማለት አበሠራቸው፡፡ በፈቃደ እግዚአብሔር በቅዱስ ገብርኤል አብሣሪነት እመቤታችን ነሐሴ ሰባት ቀን ተፀነሰች
አይሁድ ለምቀኝነት አያርፉምና ከዚህ ቀደም ከነሱ ወገን የሚሆኑ
ዳዊትና ሰሎሞን አርባ አርባ ዘመን እንሰም አቅልጠው እንደገል ቀጥቅጠው ገዙን፤ ከእነሱ ደግሞ የሚወለደውን እንደምን
ያደርገን ይሆን? ብለው በጠላትነት ተነሱባቸው፡፡ በመልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ትእዛዝና መሪነት ቅዱስ ኢያቄምና
ቅድስት ሐና ወደ ሊባኖስ ተራራ ወጡ፡፡ ቅዱስ ዳዊት በመዝሙሩ “መሠረቶቹ በተቀደሱ ተራሮች ናቸው” ብሎ እንደተናገረው ከተቀደሱ ወላጆቿ ግንቦት 1 ቀን በተራራው ላይ ሳሉ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተወለደች /መዝ. 86፥1/፡፡
ቅዱስ ያሬድ በአንቀጸ ብርሃን ጸሎቱ “ጸጋን የተመላሽና የደስታ መገኛ ሆይ ዓይኖቻቸው ብዙዎች ከሚሆኑ ከኪሩቤልና ክንፎቻቸው ስድስት ከሆኑ ከሱራፌል ግርማ የሚበልጥ የመወደድ ግርማ አለሽ፡፡ እነዚያ ፊታቸውን ይሸፍናሉ… ከልጅሽ መለኮት ከሚወጣው እሳት ይድኑ ዘንድ፤ አንቺ ግን የመለኮት ማደሪያ ሆንሽ፤ የመለኮት ባሕርይም ሥጋሽን አላቃጠለውም፤ የእሳት ነበልባልን ተሸከምሽ” ብሏታል፡
በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት መሠረት ሃና እና ኢያቄም ከአይሁድ ለማምለጥ ተሰደው በአድባረ ሊባኖስ ሥር እመቤታችንን ወለዱ በወቅቱ ከቤት የወጡት ለሽሽት ነበርና ስንቅ ስላልያዙ ምግባቸው “ንፍሮና ጥራጥሬ” ነበር፡፡ይኼንን
ትውፊት በመያዝ በዓሉ ከቤት ውጭ ንፍሮ እየተበላ ይከበራል፡፡ ሆኖም በበጎ ነገሮች ሰበብ ክፉ ዓላማውን ማስፈጸም
የሚፈልገው ዲያብሎስ በማር መሃል መርዝን ከሚጨምርባቸው መንፈሳዊያት በዓላት አንዱ የግንቦት ልደታ የእመቤታችን
በዓል ነው፡፡ አንዳንዶች በድፍረት ለአድባር ለውጋር ነው፣ቆሌውን ለመለመን ነው፣ እያሉ ንፍሮ የሚበትኑ፣ቡና
የሚረጩ፣ቂቤ የሚቀቡ፣የከብት ደም የሚያፈሱ፣ እነዚህ በእርግጥም ጣዖት አምላኪዎች ናቸው፡፡